የየካቲት 10/2011 ዓ.ም ሰንበት ዘአስተርእዮ 5ኛ የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ
ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ተወሰደ
በእለቱ የተነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
1. 1 ጢሞ 5፡5-10
2. ያዕ. 5:3-20
3. ሐዋ 3፡17-26
4. ሉቃስ 2:22-34
የእለቱ ቅዱስ ወንጌል
በሙሴም ሕግ መሰረት የመንጻት ሥርዓት የሚፈጸምበት ጊዜ ደረሰ፥ ስለዚህ ሕጻኑን ለእግዚኣብሔር ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት ሄዱ። ይህንንም ያደርጉበት ምክንያት በእግዚኣብሔር ሕግ “ወንድ የሆነ የበኩር ልጅ ሁሉ ለእግዚኣብሔር ተሰጥቶ የተቀደሰ ይሆናል” የሚል ትዕዛዝ ተጽፎ ስለነበረ ነው። እንዲሁም በኣግዚኣብሔር ሕግ “ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ለመሥዋዕት ማቅረብ አለበት” የሚል ትዕዛዝ ነበረ።
በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበረ፥ ይህም ሰው የእስራኤልን መጽናናት ይጠባበቅ ነበር፤ ጻድቅና ትጉህም ነበረ፥ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበረ። እርሱ የእግዚኣብሔርን መሲሕ ሳያይ እንደ ማይሞት በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ ነበር።
በዚያን ቀን መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶት ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ዮሴፍ እና ማርያምም የሕጉን ስነ-ስርዓት ለመፈጸም ሕጻኑን ይዘው ወደ ቤተ መቅደስ ገቡ። በዚያን ጊዜ ስምዖን ሕጻኑን አቅፎ እግዚአብሔርንም እየባረከ እንዲህ አለ
“ጌታ ሆይ፥ አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ፤ ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና፤ ይህም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው”።
ዮሴፍና እናቱም ስለ እርሱ በተባለው ነገር ይደነቁ ነበር። ስምዖንም ከባረካቸው በኋላ በተለይም የሕጻኑ እናት ማርያምን እንዲህ አላት “እነሆ ይህ ሕጻን በእስራኤል ውስጥ ለብዙዎቹ መጥፋት፣ ለብዙዎቹ ደግም የመዳን ምክንያት ይሆናል፣ እርሱም ብዙዎቹ የማይቀበሉት ምልክት ይሆናል። በዚህም በብዙዎች ልብ ውስጥ ያለው ስውር ሐሳብ ይገለጣል፣ ያንቺንም ልብ የሐዘን ስይፍ ሰንጥቆ ያልፋል።
የእልቱ ቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ
የኢየሱስ ወላጆች በሕግ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ በወሰዱት ወቅት ስምዖን “በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ” (ሉቃስ 2.22-40) ሕፃኑን ኢየሱስን አቅፎ “ማዳንህን በዐይኖቼ አይቻለሁ እርሱም በሕዝቦች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኽው፣ እርሱም ለአረማዊያን እውነትን የሚገልጥ ብርሃን ይሆናል። ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው!” በማለት እግዚኣብሔርን አመስግኑዋል። ስምዖን ኢየሱስን በዐይኑ ብቻ ሳይሆን ያየው ለብዙ ጊዜ በተስፋ ሲጠባበቅ የነበረውን ሕፃኑን ኢየሱስ በእጆቹ አቅፎ ይዞም ነበር። ይህም በታላቅ ደስታ እንዲሞላ አድርጎት ነበር። እግዚኣብሔር በሕዝቦቹ መኋል ለማደር በመምጣቱ የተነሳ ልቡ በደስታ ተሞልቶ ነበር የእርሱም በሥጋ በሕዝቦቹ መኋል መገኘቱም ተሰምቶት ነበር።
የዛሬ ስርዓተ አምልኮ እንደ ሚያስረዳን ኢየሱስ ከተወለደ ከአርባ ቀናት ቡኋላ “በሙሴ ሕግ የተፃፈውን ለመፈጸም ብቻ ሳይሆን ወደ ቤተ መቅደስ የተወሰደው በእርግጠኛነት ተወዳጅ የሆኑ ሕዝቦቹን ለመገናኘት ፈልጎ ነው። ይህም ግንኙነት እግዚኣብሔር ከሕዝቡ ጋር በመገናኘቱ የተነሳ የመጣውን ደስታ እና ተስፋን የሚያድስ ነው።
ስምዖን ያቀረበው የውዳሴ መዝሙር አማኞች ሁሉ በሕይወታቸው ማብቂያ ጊዜያት ሁሉ “በእውነት በእግዚኣብሔር ተስፋ ማድረግ መቼም ቢሆን የማያሳፍር መሆኑን” እንዲረዱት ያደርጋል። እግዚኣብሔር መቼም ቢሆን አያታልለንም። ስምዖን እና ሐና በስተርጅናቸው ውጤታማ ሆኑ ውጤታማ መሆናቸውንም በዘመሩት የደስታ መዝሙር አረጋግጠዋል። ጌታ የገባውን ቃል የሚጠብቅ በመሆኑ ሕይወታችንን በተስፋ መኖር ጠቃሚ ነው። ኢየሱስ ራሱ ከጊዜ በኋላ በናዝሬት ምኩራብ ውስጥ ይህን ተስፋ ያብራራል: የታመሙትን፣ እስረኞችን፣ ብቻቸውን የቀሩትን አረጋውያን፣ ኃጢአተኞችን እና ድኸ የሆኑ ሆኑ ሰዎች ሁሉ ይህን ተመሳሳይ የተስፋ መዝሙር እንዲዘምሩ ይጋብዛል። ኢየሱስ ከእኛ ጋር ነው፣ ኢየሱስ ከእነሩስ ጋርም ነው (ሉቃስ 4.18-19)።
እኛ ይህንን የተስፋ መዝሙር ከአረጋዊያን ወርሰናል። የእዚህም ሂደት አካል እንድንሆንም አድርገውናል። በፊቶቻቸው ላይ፣ በሕይወታቸው ውስጥ፣ ዕለታዊ በሆነ መሥዋዕትነት ሳይቀር ይህን ምስጋና ከነርሱ ጋር እንዴት እንደ ነበረ ማየት ይቻላል። እኛ የቀድሞ አባቶቻችን፣ ወንድሞችና እህቶች ያላፈሩበት ሕልም ወራሶች ነን። እኛም ከእኛ በፊት ያለፉት ሰዎች ቃል ወራሾች ነን። እኛንም እንደ እነርሱ “እግዚአብሔር አያታልለንም። በእርሱ ተስፋ ማድረግ አያሳፍርም” ብለን ልንዘምር ይገባል። አምላክ ሰዎችን ለማግኘት ይመጣል። እኛም ከኢዩኤል ትንቢት በማንሳት እና ይህንን ትንቢት የራሳችን በማድረግ “ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ መንፈሴን አፈሳለሁ፣ ወንዶች እና ሴቶች ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፣ ትንቢት ይናገራሉ፣ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ” ብለን ልንዘምር ይገባል (ት. ኢዩኤል 2,28)።
እስቲ ወደ ዛሬው የወንጌል ክፍል በመመለስ አንድ ጊዜ ይህ ሁኔታ በማሰላሰል እንመልከት። በእርግጥም የስምዖንና የሐና መዝሙር በራስ ወዳድነት ወይም የግል ሁኔታቼው ትንተና እና የግምገማ ፍሬ አልነበረም። እነርሱ በራሳቸው ሕይወት ውስጥ መጥፎ ነግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ የሚል ስጋት አድሮበባችው ሳይሆን በውስጣቸው የነበረው ስሜት ወደ ውጭ ገንፍሎ በመውጣቱ የተነሳ የዘመሩት መዝሙር ነው። የእነርሱ መዝሙር ከተስፋ የተወለደ መዝሙር ነው። ይህም ተስፋ እስከ እርጅናቸው ወቅት ድረስ አብሮዋቸው የዘለቀ ተስፋ ነው። የእዚህ ተስፋቸው ሽልማት ኢየሱስን መገናኘት ነበረ። ማሪያም ስምዖን ሕፃኑን ኢየሱስን እንድያቅፍ በፈቀደችበት ወቅት አዛውንቱ ስምዖን ሕልሙን መዘመር ጀመረ። እርሷ ኢየሱስን በሕዝቡ ማኋል በምታኖርባቸው ጊዜያት ሁሉ ሕዝቡ ደስታን ይጎናጸፋል። በእዚህም መንገድ ብቻ ነው እኛ ደስታን እና ተስፋን መጎናጸፍ የምንችለው፣ እየሱስ በሚገባው ቦታ በሕዝቡ መኋል ሲኖር ብቻ ነው እኛ የመኖር ጉጉት ልያድርብን የሚችለው።
ኢየሱስን በሕዝቡ መኋል ማኖር ማለት እግዚኣብሔር እንዴት በከተሞቻችን መንግድ ላይ እና በጎሬቤቶቻችን መካከል እንዴት እየተመላለሰ እንድሚገኝ የሚያሰላስል ልብ ማለት ነው። ኢየሱስን በሕዝቡ መካከል ማኖር ማለት የወንድሞቻችንና የእቶቻችንን መስቀል መሸከም ማለት ነው። ኢየሱስን በሕዝቡ ማካከል ማኖር ማለት ፈውስን በመሻት እያለቀሰ ለሚገኘው የዓለማችን ቁስል መንካት ማለት ነው። ይህም የኢየሱስን ቁስል እንደ መንካት ይቆጠራል።
ራሳችንን ከኢየሱስ ጋር በሕዝቡ መካከል እናኑር! ራሳችንን እንደ የሐይማኖት ጉዳዮች “ተሟጋች” አድርገን ሳይሆን መቁጠር የሚገባን ነገር ግን በቀጣይነት ይቅርታ የሚደረግልን፣ በጥምቀት የተዋጀን፣ ይህንንም ቅዱስ ቅባት እና የእግዚኣብሔር መጽናናት ከሁሉም ጋር መካፈል ይኖርብናል። ይህንንም መንገድ የምንከተል ከሆንን በጣም ጥሩ ነው በጣም ነፃ እና በተስፋ የተሞላን እንሆናለን። ከራሳችን በመውጣት ሌሎችን መቀላቀል ለራሳችን ብቻ መልካም እንደ ማድረግ የሚቆተር ሳይሆን ሕይወታችንን የሚቀይር እና የተስፋ መዝሙር እድንዘምር ይረዳናል።
ሕዝቦቹን ለመገናኘት ከሚሄደው ከኢየሱስ ጋር እንቀናጅ። ወደ ፊት እንሂድ፣ ወደ ፊት ስንሄድ በማጉረምረም ወይም ደግሞ የአባቶቻቸውን ሕልም ሳይከተሉ ቀርተው በመጨነቅ ላይ እንዳሉ ሰዎች ሳይሆን ነገር ግን በግልጽነት እና በውዳሴ መዝሙ ሊሆን ይገባል። በፍርሃት ሳይሆን ነገር ግን በትዕግስት እና በመንፈስ ቅዱስ፣ የሕልማችን ባሌበት በሆነው በጌታ በመታመን መኖር ይገባል።
ምንጭ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር 26/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ካደርጉት ስብከት የተወሰደ።
አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን