ፈልግ

ማንኛውም ዓይነት ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ሳይደርስ እንዲሁ በከንቱ አይቀርም! ማንኛውም ዓይነት ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ሳይደርስ እንዲሁ በከንቱ አይቀርም! 

ማንኛውም ዓይነት ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ሳይደርስ እንዲሁ በከንቱ አይቀርም!

አባታችን ሆይ” ጸሎት  

ክፍል አራት

በእለቱ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል

ስለዚህ እኔም እናንተን የምላችሁ ይህን ነው፣ ለምኑ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙኛላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፍትላችሁማል።  የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልግም ያገኛል፥ መዝጊያውንም አንኳኩ ይከፈትላችኋል። ምክንያቱ የሚለምን ሁሉ ይቀበላል፣ የሚፈልግም ሁሉ ያገኛል፣ መዝጊያ ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።  ከእናንስ አባት ሆኖ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይ የሚሰጠው ማነው? ዓሣ ቢለምነው በዓሣ ፋንታ እባብ ይሰጠዋልን? ወይስ እንቍላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ነገር መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባታችሁማ  ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም! (ማቴ 7፡ 7-11)

የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ የምናደርገው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አሰትምህሮ በሉቃስ ወንጌል ላይ ያተኩራል። በመሠረቱ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክ ከሕጻንነቱ ጀመሮ ጥልቅ የሆነ የጸሎት ሕይወት እስከ ጀመረበት ጊዜ ድረስ ያለውን ታሪክ በመግለጽ ደረጃ ይህ የሉቃስ ወንጌል ከሁሉም ወንጌሎች የተሻለ ነው። በውስጡም  ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፥ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና” (ሉቃስ 1፡68-79) በማለት የጸለየው ጸሎት (The Benedictus)፣ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች” (ሉቃስ 1፡47-55) በማለት ማርያም ያቀረበችው የምስጋና ጸሎት (il Magnificat ) እና በመጨረሻም ጌታ ሆይ አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም አሰናብተው” (ሉቃ. 2፡29-32) የተሰኘው የስምዖን ጸሎት (il Nunc dimittis) ያካተተ ቤተ ክርስቲያኑን በእየቀኑ የምትጸልያቸውን ሦስት ጸሎቶች በውስጡ አቅፎ ይዙዋል።

ከሁሉም በላይ ኢየሱስ የጸሎት ሰው ነው። ለምሳሌም “ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ” (ሉቃ 9፡29) በማለት በሉቃስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው እና ኢየሱስ ተአምራዊ በሆነ ሁኔታ መልኩ መለወጥ የጀመረው ጸሎት በማድረግ ላይ በነበረበት ወቅት ነው። ነገር ግን በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ በእያንዳንዱ ደረጃ የእርሱ እንቅስቃሴ ሁሉ የሚመራው በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ ተነሳስቶ ነው። ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጠመቅ ላይ በነበረበት ወቅት ጸልዩዋል፣ በጣም አስፈላጊ ውሳኔዎችን ከማድረጉ በፊት ከአብ ጋር በጸሎት ይነጋገር ነበር፣ ብዙን ጊዜ ብቻውን ወደ ሚሆንበት ስፍራ በመሄድ በእዚያ ብቻውን ጸሎት ያደርግ ነበር፣ ለምሳሌ “ኢየሱስ ስምዖን ስምዖን ሆይ! እነሆ ገበሬ ስንዴውን ከገለባ አበጥሮ እንደ ሚለይ እንዲሁም ሰይጣን እናንተን ሊያበጥራችሁ ወይም ሊፈትናችሁ ተመኘ። ነገር ግን የአንተ እምነት እንዳይጠፋ እኔ እጸልያለሁ፣ አንተም ተጸጽተህ ወደ እኔ በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና” (ሉቃስ 22፡31-32) በማለት ለስምዖን የምልጃ ጸሎት አድርጎ እንደ ነበረም ይታወሳል።

ሌላው ቀርቶ የመሲሑ ሞት እንኳ ሳይቀር በፀሎት መንፈስ ውስጥ ሆኖ የተካሄደ ነው፣ ስለዚህም ነው እነዚያ የመከራ ጊዜያት በሙሉ በሚያስደንቅ መልኩ በከፍተኛ የመረጋጋት መንፈስ የተከናወኑትና ከፍተኛ የሆነ የመረጋጋት ምልክቶች የታዩትም በዚሁ ምክንያት ነው፣ ለምሳሌም በወቅቱ ስያለቅሱ የነበሩትን ሴቶች ኢየሱስ አጽናንቱዋቸዋል፣ ለአሳዳጆቹ ጸልዩዋል፣ ከኢየሱስ ጋር ተሰቅለው ከነበሩት ከክፉ አድራጊዎች መካከል አንዱን ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” በማለት ይቅርታ ያደርገለት እና ኢየሱስ  በታላቅ ድምፅ ጮኾ፣ አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ” (ሉቃስ 23፡46) ካለ በኋላ የሞተበትን እነዚህን አጋጣሚዎች በዋቢነት መጥቀስ ይቻላል። የኢየሱስ ጸሎት በጣም ከባድ የነበረውን አስቸጋሪ የነበሩ ሁኔታዎችን፣ የክህደት እና የበቀል ፍላጎቶችን በከፍተኛ ሁኔታ በማቃለል የሰውን ልጅ በጣም ክፉ ከሆነው ከጠላቱ ሞት ጋር ስያስታርቅ እናያለን።

አሁንም ቢሆን የእርሱ በደቀ-መዛሙርት ከነበሩት ውስጥ አንዱ “ጌታ ሆይ መጸለይ አስተምረን” (ሉቃስ 11፡1) ብሎ የጠየቀው ጥያቄ የሚገኘው በዚሁ በሉቃስ ወንጌል ውስጥ ነው።

ከዚህ ጥያቄ አንፃር በመነሳት ነው እንግዲህ ኢየሱስ እጅግ በጣም ሰፋ ያለ ማብራሪያ በማቅረብ የእርሱ ለሆኑት ደቀ-መዛሙርት ምን ዓይነት ቃላቶችን እና ምን ዓይነት ስሜቶችን ተጠቅመው ወደ እግዚአብሔርን መጸለይ እንደሚገባቸው ያብራራላቸው በዚሁ ምክንያት ነው።

የዚህ ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል ለአብ ትክክለኛ የሆነ ጸሎት ስለማድረግ ያመለክታል፣ ይህም  በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰውን እና እኛ በስርዓተ አምልኮ ወቅት ከምንጠቀመው ጸሎት ይልቅ በሉቃስ ወንጌል ውስጥ ሰፋ ያለ ቅርጽ ይሰጠዋል። አንድ ክርስቲያን "አባት" የሚለውን መጠሪያ በመጠቀም ወደ እግዚአብሔር ጸሎቱን ያቀርባል። በሉቃስ ወንጌል ውስጥ “የእኛ” የሚለው ቃል “በሰማይ የምትኖር” በሚለው ገላጭ ቃል ሲተካ እናያለን። ከዚህም ባሻገር የአጠቃላይ የጸሎቱ መዋቅር ተመሳሳይ ቢሆንም ጥያቄዎቹ ግን ከሰባት ወደ አምስት ይቀንሳሉ።

ነገር ግን በዚህ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ባስተማረው ፀሎት ውስጥ የሚገኙትን አንዳንድ ትዕዛዞች ውስጥ የሚገኙትን የጸሎቱ አንኳር የሆኑ ሐሳቦችን አንድ ጊዜ ቆም ብለን መመልከት ጠቃሚ ነው። እነዚህም ትዕዛዛት ጸሎቱን የሚጸልየው አማኝ የሆነ ሰው ሊኖረው ስለሚገባ ባህሪ ይገልጻሉ። አንድ መልካም ያልሆነ ሰው ምሳሌን በመጠቀም ወዳጁ በእኩለ ሌሊት ወደ እርሱ ዘንድ ሄዶ “አንድ ወዳጄ ከመንገድ ወደ እኔ መጥቶ የማቀርብለት እንጀራ የለኝም እና አውሰኝ” ብሎ በሚጥይቀበት ወቅት “ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም ይላልን?  ወዳጁ ስለ ሆነ ተነሥቶ ባይሰጠው እንኳ፥ ስለ ነዘነዘው ተነስቶ የሚፈልገውን ሁሉ ይሰጠዋል” (ሉቃስ 11፡9) በማለት ኢየሱስ የተናገረውን ንግግር ማስታወስ ግድ ይላል። ከእዚያም በመቀጠል ወዲያውኑ አንድ አባት የተራበ ልጁን እንዴት እንደ ሚያስተናግድ በመግለጽ “ ከእናንስ አባት ሆኖ ልጁ ዓሣ ቢለምነው በዓሣ ፋንታ እባብ የሚሰጠው ማነው? “ (ሉቃስ 11፡11) በማለት አክሎ ይናገራል።

እነዚህ ምሳሌዎች በመጠቀም ኢየሱስ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ የሚመልስ አምላክ መሆኑን እንድንገነዘብ ያደርገናል፣ ማነኛውም ዓይነት ጸሎታችን ሳይሰማ እንዲሁ በከንቱ አይቀርም፣ እርሱ አባት በመሆኑ የተነሳ በመከራ ውስጥ ሆነው እርሱን የሚለምኑትን ልጆቹን በፍጹም አይረሳም።

እርግጥ ነው እነዚህ ከላይ የተገለጹት ማረጋገጫዎች እኛን ሁላችንን ልያደናግሩን ይችሉ ይሆናል፣ ምክንያቱም ብዙዎቹ ያቀረብናቸው ጸሎቶቻችን ምንም ዓይነት ውጤት ያለስገኙልን መስሎን ሊታየን ይችላል። ምን ያህል ጊዜ ጠይቀን አተናል? ምን ያህል ጊዜ ደጋግመን አንኳኩተን በሩ ተዘግቶብናል? የዚህ ዓይነት ሁኔታዎች በሚገጥሙን ወቅት ኢየሱስ እንደ ሚመክረን ጸሎታችንን ተግተን መቀጠል ይገባናል እንጂ ተስፋ ቆርጠን ማቆም የለብንም። ጸሎት ዘወትር እውነታውን ያመጣል፣ በአቅራቢያችን የሚገኙ ነገሮች ባይለወጡም እንኳን እኛ ልንለወጥ እንችላለን።

እግዚአብሔር መልስ እንደሚሰጥ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። ብቸኛውና እርግጠኛ ለመሆን የሚያስቸግረን ነገር ቢኖር የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ፣ ነገር ግን እርሱ አንድ ቀን መልስ እንደ ሚሰጠን ግን ጥርጥር የለንም። ምናልባት ዕድሜ ልካችንን ለምነን ይሆናል፣ እርሱ ግን አንድ ቀን መልስ ይሰጣል። እርሱ ዓሣ ለሚተይቀው ልጁ እባብ እንደ ሚሰጠው አባት ዓይነት እንዳልሆነ ቃል ገብቶልናል። ሁላችንም በልባችን ውስጥ እንዲከሰት የምንፈልገው የደስታ ምኞት አንድ ቀን እንደ ሚፈጸም ግን ምንም ጥርጥር የለውም። ይህንን በተመለከተ ኢየሱስ እንዲህ ይላል “እግዚኣብሔር ታዲያ ቀን እና ሌሊት እየጮኹ ለሚለምኑት ሕዝቦቹ አይፈርድላቸውምን?” (ሉቃስ 18፡7) በማለት ይናገራል። በዚያን ጊዜ እንዴት ያለ የክብር ቀን እና ትንሣኤ ይሆናል! የብቸኝነት እና ተስፋ የመቁረጥ ስሜቶቻችን ላይ ድል እስክንጎናጸፍ ድረስ መጸለይ ይኖርብናል። በመንገድ ላይ እንዳለ እንቅስቃሴ ዓይነት ነው፣ በእያንዳንዱ መንገድ መጨረሻ ላይ ሁሉንም ለመቀበል እጆቹን ዘርግቶ የሚጠብቀን አንድ አባት እንዳለ ማመን ያስፈልጋል።

ምንጭ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር 1/2011 ዓ.ም በሚለው ጸሎት ዙርያ በቫቲካን ካደረጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የተወሰደ።

የቫቲካን ዜና

14 May 2020, 13:39