ፈልግ

የሰኔ 14/2012 ዓ.ም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም ሰንበት የእግዚአብሔር ቃል አስተንትኖ የሰኔ 14/2012 ዓ.ም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም ሰንበት የእግዚአብሔር ቃል አስተንትኖ 

የሰኔ 14/2012 ዓ.ም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም ሰንበት የእግዚአብሔር ቃል አስተንትኖ

እግዚአብሔር ሕይወታችንን ይቀይርልን ዘንድ እንፍቀድለት

የእለቱ ምንባባት

1.      ዘዳግም 8፡2-3. 4-6

2.    መዝሙር 147

3.    1ቆሮንጦስ 10፡16-17

4.    ዮሐንስ 6፡51-58

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እርስ በርሳችሁ አታጒረምርሙ፤ የላከኝ አብ ካልሳበው በቀር ማንም ወደ እኔ መምጣት አይችልም፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። በነቢያትም፣ ‘ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ’ ተብሎ ተጽፎአል፤ አብን የሚሰማና ከእርሱም የሚማር ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል። ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሆነው በቀር አብን ያየ ማንም የለም፤ አብን ያየው እርሱ ብቻ ነው። እውነት እላችኋለሁ፤ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው። የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ። አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ፤ ይሁን እንጂ ሞቱ። ነገር ግን ሰው እንዳይሞት ይበላው ዘንድ ከሰማይ የሚወርድ እንጀራ ይህ ነው። ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ማንም ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ ይህም እንጀራ፣ ለዓለም ሕይወት እንዲሆን የምሰጠው ሥጋዬ ነው።”

አይሁድም፣ “እንበላ ዘንድ ይህ ሰው ሥጋውን እንዴት ሊሰጠን ይችላል?” እያሉ እርስ በርሳቸው አጥብቀው ይከራከሩ ጀመር።

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ የሰውን ልጅ ሥጋውን ካልበላችሁና ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ፣ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፤ ሥጋዬ እውነተኛ ምግብ፣ ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና፤ ሥጋዬን የሚበላ፣ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ። ሕያው አብ እንደ ላከኝ፣ እኔም ከእርሱ የተነሣ በሕይወት እንደምኖር፣ የሚበላኝም እንዲሁ ከእኔ የተነሣ በሕይወት ይኖራል። ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ መና በሉ፤ ሞቱም፤ ይህን እንጀራ የሚበላ ግን ለዘላለም ይኖራል።” 

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

ዛሬ የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም የሚታሰብበት ዓመታዊ በዓል ይከበራል። በዛሬው ዕለት ስርዓተ አምልኮ ላይ የተነበበው ሁለተኛው ንባብ  ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ የቅዱስ ቁርባን ሥነ-ስርዓት አከባበርን ይገልጻል (1 ቆሮ 10፡16-17)።  የሚባርከው የበረከት ጽዋ እና የሚቈርሰው እንጀራ የሚያስከትሉትን ሁለት ውጤቶችን አጉልቶ ያሳያል እነዚህም ምስጢራዊ ተጽዕኖ እና ሕብረት በመፍጠር ላይ ያላቸውን  ተጽዕኖ ናቸው።

በመጀመሪያ  ሐዋርያው ​​“ የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቈርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? (1ቆሮ 10፡16) በማለት ይናገራል። እነዚህ ቃላት ምስጢራዊነትን ይገልጻሉ ወይም ቅዱስ ቁርባን የሚያደርገውን መንፈሳዊ ተፅእኖን ይናገራሉ፤ እርሱ በእንጀራው እና በውይን ጠጅ አማካይነት ሁሉንም ለማዳን ራሱን ከሚያቀርበው ከክርስቶስ ጋር ካለው አንድነት ጋር ይዛመዳል። ኢየሱስ ምግባችን ለመሆን፣  እንደገና እኛን ለመጠገን እና እያንዳንዳችን ለአፍታ ያህል ከቆምንበት ወይም ከእያንዳንዱ ውድቀት በኋላ እንደገና የሚወጣውን የማደስ ኃይልን በውስጣችን ለማምጣት ኢየሱስ ቅዱስ ቁርባን ውስጥ ይገኛል። ነገር ግን ይህ የእኛን ማረጋገጫ ፣ እራሳችንን ለመለወጥ ፈቃደኛ መሆናችንን ማለትም አስተሳሰባችን እና ድርጊታችን ይጠይቃል። ያለበለዚያ የምንሳተፍበት የቅዱስ ቁርባን ሥነ-ስርዓት ወደ ባዶ እና መደበኛ የአምልኮ ሥርዓቶች ይቀነሳል። እናም ብዙ ጊዜ ​​አንድ ሰው መስዋዕተ ቅዳሴን የሚከታተለው እንዲህ  ማድረግ ስለሚኖርብኝ ነው ብሎ በማሰብ ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም አንድ ማህበራዊ ክስተት ነው ብሎ ስለሚያምን ፣ አክብሮት ያለው ግን ማህበራዊ ክስተ ነው ብሎ ስለሚገምት። ነገር ግን ምስጢሩ ሌላ ነገር ነው ፡፡ በእዚያ የሚገኘው ኢየሱስ ራሱ ነው፣ እኛ የምንመገበው እርሱን ነው።

ሁለተኛው ውጤት አንድነት መፍጠር ነው፣ እናም ይህ  በቅዱስ ጳውሎስ በእነዚህ ቃላት ተገልጿል “እንጀራው አንድ እንደሆነ፣ እኛም ብዙዎች ሆነን ሳለ አንድ አካል ነን፤ ሁላችን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና” (1ቆሮ 10፡17)። አንዱ እንጀራ እንደ ተቆረሰ እና እንደ ተከፋፈለ በተመሳሳይ መንገድ አንድ አካል ለመሆን እስከ ቅዱስ ቁርባን ተሳትፎ ድረስ የሚያደርስ የጋራ አንድነትን ይፈጥራል። እኛ የክርስቶስ ሥጋና ደም ተመግበን የምንኖር ማህበረሰብ ነን። ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ማድረግ ውጤታማ የአንድነት ፣ የመተባበር ፣ የመጋራት ምልክት ነው። አንድ ሰው  የወንድማማችነት መንፈስ ይሰፍን ዘንድ የራሱን አስተዋጾ ካላደርገ በስተቀር በቅዱስ ቁርባን ውስጥ መሳተፍ አይችልም - ይህም ቅን መሆን ማለት ነው። ነገር ግን የእኛ ሰብዓዊ ጥንካሬ ብቻ ለዚህ በቂ እንዳልሆነ ጌታ በሚገባ ያውቃል ፡፡ በተቃራኒው ፣ እሱ ሁልጊዜ በደቀ መዛሙርቱ መካከል የፉክክር ፣ የቅናት ፣ የጭፍን ጥላቻ ፣ የመከፋፈል ፈተና እንደሚኖር ያውቃል። እኛ እነዚህን ሁሉ እናውቃለን ፡፡ በዚህም ምክንያት ከእርሱ ጋር አንድ ሆነን ከቆየን ሁልጊዜ የዘለአለማዊ ፍቅርን ስጦታ እንቀበል ዘንድ እንዲሁ እርሱ እውነተኛ ፣ ተጨባጭ እና ዘለአለማዊነቱን በሚገልጸው ቅዱስ ቁርባን ተወውልን።  “በፍቅሬ ኑሩ” (ዮሐ 15 9) በማለት ኢየሱስ ተናግሯል።  እናም ለቅዱስ ቁርባን ምስጋና መስጠት ይቻላል። በወዳጅነት እና በፍቅር መንፈስ መኖር ያስፈልጋል።

ይህ ቅዱስ ቁርባን የሚሰጠን ሁለት ፍሬ: መጀመሪያ ከክርስቶስ ጋር አንድነት እንድንፈጥር ያደርገናል፣ ሁለተኛ  እርሱን ከሚመገቡ ሰዎች ጋር የሚደረግ ኅብረት ለክርስቲያን ማኅበረሰብ ምንጭ ይሆናል እንዲሁም ቀጣይነቱን ያድሳል። ቅዱስ ቁርባንን የምትፈጽመው ቤተክርስቲያን ናት ፣ ነገር ግን ቅዱስ ቁርባን ቤተክርስቲያንን መሥራቷል፣ ተልዕኳዋን ከማከናወኗ በፊትም እንኳን የተልእኳዋ ዋነኛው መሰረት ነው።  የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ይህ ነው: - ኢየሱስን ለመቀበል ከውስጣችን መለወጥ እና ኢየሱስን ለመቀበል ከእርሱ ጋር ሕብረት እንድንፈጥር ያደርገናል፣ እንድንከፋፈል ሳይሆን አንድ እንድንሆን ያደረጋናል።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የኢየሱስን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደሙ የሆነውን ምስጢረ ቅዱስ ቁርባን በመተው የሰጠን ታላቅ ስጦታ ሁል ጊዜም በምስጋና እና በአክብሮት እንድንቀበል በአማላጅነቷ ትርዳን።

ምንጭ የቫቲካን ሬዲዮ የአማርኛው አገልግሎት

አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

20 June 2020, 15:02