የወጣቶች ስደት እና በስደት ላይ የሚያጋጥማቸው ተግዳሮቶች
ክፍል ሁለት
የወጣቶችን ስደት በተመለከተ ባቀረብነው የመጀመርያ ክፍል ዝግጅት ላይ የወጣት ዜጎቻችን ስደት መነሻና የሚያስከትለው መዘዝ እንደ መነሻ አድርገን በጥቂቱ ለማየት ሞክረናል። በዚህ ዝግጅት ደግሞ የሚንመለከተው ከላይ በአርስቱ እንዳመለከትነው የወጣቶች ስደት ተግዳሮቶች ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ አተገባበር አጠቃላይ ሁኔታ ጋር በተያያዘ መልኩ በሰው ልጆች የደህንነት ታሪክ ውስጥ የተካተተ እና የወጣቶችን ስደት በተመለከተ ምን ማደረግ እንደ ሚገባ የሚገልጹ በርካታ አስተምህሮዎች ይገኛሉ።
የሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ማብቂያ ላይ ይፋ ከሆኑ ሰነዶች መካከል አንዱ የሆነው እና ቤተክርስቲያን በአሁኑ ዘመናዊ ዓለም ውስጥ ማደረግ ስለሚገባት ሐዋርያዊ ተግባር በተመለከተ የሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ይፋ ካደረጋቸው ሰነዶች መካከል አንዱ የሆነው እና ሐዋርያዊ ተግባራትን የሚመለከተው በላቲን ቋንቋ “GAUDIUM ET SPES” በአማርኛው “ደስታ እና ተስፋ” በሚል አርዕስት የቀረበው ሰነድ እንደ ሚያስረዳው “በዚህ ዘመን ያሉ ወንዶች ደስታ እና ተስፋዎች ፣ ሀዘንና ጭንቀቶች ፣ በተለይም ድሆች ወይም በማንኛውም መንገድ የተጠቁ ፣ እነዚህ የክርስቶስ ተከታዮች ሀዘንና ጭንቀት ፣ የክርስቶስ ተከታዮች ሀዘንና ጭንቀት ናቸው” (GAUDIUM ET SPES PROMULGATED BY PASTORAL CONSTITUTION ON THE CHURCH IN THE MODERN WORLD HIS HOLINESS, POPE PAUL VI ON DECEMBER 7, 196፣ ቁ 1) በማለት በሁለተኛው የቫቲካን ጉባዔ ማብቂያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት ጳውሎስ ስድስተኛ ኢኮኖሚ እና ኢ-ፍትሃዊነት በተመለከተ አጽኖት ሰጥተው መናገራቸው ይታወሳል።
እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ሀገራችን ውስጥ የሚደረግ ስደቶች ታሪካዊ ከሆኑ መንስኤዎች ጋር ተያይዞ የሚመጡ ውስብስብ ክስተቶች እንደ ሆኑ ይታወቃል። እነዚህ መሠረታዊ ምክንያቶች ድህነት፣ ድርቅ፣ የፖለቲካ አለመግባባት፣ እንድሁም ተፈጥሯዊ ክስተቶች ናቸው ፡፡ ድህነትን ከመጠ በላይ የሆነ ተጽኖ በማስከተሉ የተነሳ ለኢትዮጲያዊያን ስደት አንቀሳቃሽ ሞተር ሆኖ የሚገኝ እንደ ሆነ በግልጽ የሚታይ ጉድይ ነው። የምግብ ዋስትና ፣ የመሠረተ ልማት አውታር እና የስራ ዕድሎች ካልተፈጠሩ በስተቀር ሕገወጥ ስደትን ለመግታት እጅግ በጣም አዳጋች ይሆናል። ብዙ ወጣቶች ሥራ አጥነት ፣ መድልዎ ፣ ብዝበዛ ፣ ማህበራዊ መገለል እና የማኅበራዊ ዋስትና ማጣታቸው ያስጨንቃቸዋል። ሕገወጥ ስደት ለማንም ቢሆን የሚመከር ጉዳይ ባይሆንም በተለይ ደግሞ ለሴት እህቶቻችን አስቸጋሪ እና ልጥቃት የሚዳርጋቸው ክስተት ሊሆን ስለሚችል ለዚ ፆታ ተኮር ጥቃት ተጋላጭ ያደርጋቸዋል። ሕገወጥ የወጣቶች ስደት በማደግ ላይ ላሉ እንደ ኢትዮጲያ ላሉ አገራት እጅግ በጣም አስቸጋሪ ተግዳሮት። በተለይም ለወጣቶች ሕግወጥ ስደት ዋነኛው ሚክንያቶች ከሚባሉት መካከል የከተሞች መስፋፋት፣ ከፍተኛ የሆነ ያልተመጣጠነ የሕዝብ ብዛት፣ ድርቅ እና የተለያዩ ተፈጥሮአዊ አደጋዎች በሚያስከትሏቸው አደጋዎች እና ጫናዎች የተነሳ ሰዎች ለስደት ይዳረጋሉ። በነዚህ ምክንያቶች የተነሳ ከገጠራማ አካባቢዎች ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መምጣቱ በከቶች ላይ ከፍተኛ ጫና የፈጠረ ሲሆን በተመሳሳይ እልኩም በከተሞች ውስጥ የሥራ እጥረት እንዲፈጠር እይዳረገ ይገኛል። በዚህም የተነሳ በአከባቢ እና በአገሪቷ ላይ ጫና በመፍጠር ላይ ይገኛል።
አዘጋጅ እና አቅራቢ ክቡር አባ ኤርሚያስ ኩታፎ
ማሕበረ ልዑካን ላዛሪስት