የሰላሳ ዓመት የጋራ ኤኮኖሚ ጉዞ የሰላሳ ዓመት የጋራ ኤኮኖሚ ጉዞ 

የ30 ዓመት የጋራ ኤኮኖሚ ጉዞ ፣ የፍቅር ውጤት መሆኑ ተገለጸ

ሎፒያኖ በተባለ የጣሊያን ከተማ የተካሄደው የፎኮላሬ እንቅስቃሴ ዓለም አቀፍ ጉባኤ፣ እንቅስቃሴው የተመሰረተበትን ሰላሰኛ ዓመት ለማስታወስ የተካሄደ መሆኑ ታውቋል። እንቅስቃሴው የተጀመረውም ከወንጌል የሚገኝ ፍቅርን መሠረት ያደረገ መሆኑን የሲቪል ኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት መሪ እና መስራች ክቡር አቶ ሉጂያኖ ብሩኒ አስታውቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የፎኮላሬ እንቅስቃሴ መስራች የሆኑት ኪያራ ሉቢክ፣ በአንድ የንግድ ማኅበር ወስጥ የሚታየውን ትልቅ ችግር ለማስወገድ በማሰብ የጋራ ኢኮኖሚ መድረክ መጀመራቸው ይታወሳል። የጋራ ኤኮኖሚ ዘርፉ በብዙ ሺህ ዎች የሚቆጠሩ ድሆችን ለመርዳት እና ለርካታ ልጆች የትምህርት ዕድሎችን ማመቻቸቱ ታውቋል። ህይን ልምድ የሚያካፍል ስብሰባ በጣልያን ውስጥ ሎፒያኖ ከተማ ውስጥ የተካሄደ ሲሆን ዝግጅቱን በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ ሰዎች በማኅበራዊ መገናኛዎች በኩል በቀጥታ መከታተላቸው ታውቋል። በላቲን አሜሪካዊቷ አገር ብራዚል እ. አ. አ በ1991 ዓ. ም የተጀመረው የጋራ ኤኮኖሚ ፕሮጀክት ቀ-ትሎም እ. አ. አ በ2010 ዓ. ም በፖርቱጋል የተካሄደ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ የጋራ ኤኮኖሚው አድጎ ከመቀበል ይልቅ የመስጠት ፍላጎትን ማሳደጉ ታውቋል። ቀስ በቀስም ያጋራ ኤኮኖሚ ስሜት በትምህርት ቤቶች እና ማሰልጠኛዎች፣ በስብሰባዎች፣ በበዓላት በወጣቶች፣ በሠራተኞች እና በንግድ ተቋማት እና በልዩ ልዩ ዘርፎች ውስጥ በሚገኙ ዜጎች ልብ ውስጥ እንዲገባ አድርጓል።

ከተዘራ ዘር ፍሬ ይገኛል

ከልጅነት ዕድሜ ጀምሮ ለጋራ ኤኮኖሚ አስተሳሰብ እድገት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግጉ የቆዩት እና የጋራ ኤኮኖሚ ተቋም አስተባባሪ እና መስራች የሆኑት አቶ ሉዊጃኒ ብሩኒ፣ ለጋራ ኤኮኖሚ ሃሳብ ማደግ፣ የማኅበራዊ አስተሳሰቦች መስፋፋት ግንባር ቀደም ተዋናይ ሲሆኑ ከዚህም በተጨማሪ በሮም በሚገኝ ሉምሳ በተባለ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር፣ እንዲሁም በቅድስት መንበር የምዕመናን፣ የቤተሰብ እና የሕይወት መምሪያ ጳጳሳዊ ምክር ቤት አማካሪ፣ አቬኒር የተሰኘ የቤተክርስቲያን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ዋና አስተባባሪ እና የር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ የኤኮኖሚ አቅጣጫን በመከታተል ለውጤቱ ከፍተኛ ሚናን መጫወታቸው ይታወቃል።

አቶ ሉዊጃኒ ብሩኒ ስለ ጋራ ኤኮኖሚ ዕድገት ሲያስረዱ እንደተናገሩት ዕድገቱ ገና በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ልምዶች የሚወለዱት ከመንፈሳዊ ሕይወት እና ከቤተክርስቲያን የአገልግሎት ጥሪ የሚጀምር ስለሆነ የረጅም ጊዜ ሂደትን የሚጠይቅ መሆኑን አስረድተዋል። ኪያራ ሉቢክን በማስታወስ የተናገሩት ክቡር አቶ ሉዊጃኒ ብሩኒ እ. አ. አ በ1991 ዓ. ም የተጀመረው የጋራ ኤኮኖሚ ሃሳብ እንቅስቃሴው መሠረቱን ከወንጌል በሚገኝ ፍቅር ላይ ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል። ኪያራ ሉቢክ የስነ ምጣኔ አዋቂ ወይም ስለንግድ እንቅስቃሴ ምንም ዓይነት እውቀት የሌላት፣ ነገር ግን የፎኮላሬ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ መስራች አባል መሆኗን ክቡር አቶ ሉዊጃኒ ብሩኒ አስረድተው፣ በብራዚል ማኅበረሰብ ዘንድ የሚታየውን የድሕነት ኑሮን ከልብ በመገንዘብ ችግራቸው የሚወገድበትን መንገድ መፈለግ መጀመሯል አስረድተዋል። ዛሬ እንቅስቃሴ በዓለማችን ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ በማደግ በአፍሪካ፣ በእስያ፣ በደቡብ አሜሪካ እና በአውስትራሊያ የሚገኙ በርካታ ወጣቶችን ያገናኘ መሆኑን አስረድተዋል።

በመስፋፋት ላይ ያለ ፕሮጄክት

በጣሊያን ውስጥ የሚገኝ የሎፒያኖ ከተማ የማኅበራዊ ሕይወት አስተሳሰብ የተወለደው ከጋራ ኤኮኖሚ አስተሳሰብ አስቀድሞ የነበረ መሆኑን ክቡር አቶ ሉዊጃኒ ብሩኒ አስረድተው፣ መነሻ ሃሳቡን ያገኘው ከቅዱስ ወንጌል መሆኑን አስረድተዋል። የጋራ ኤኮኖሚ አስተሳሰብ የሚጀምረው ከሎፒያኖ ከተማ ሳይሆን መላው የንግድ ተቋማት በድህነት ሕይወት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በመርዳት የጋራ ሕይወት ልምድን ለማሳደግ በመፈለጋቸው ነው።

የጋራ ኤኮኖሚ ተጨማሪ አዲስ ልምዶችን ማፍለቁን የገለጹት አቶ ሉዊጃኒ ብሩኒ፣ ከልምዶቹ አንዱ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ከሁለት ዓመት በፊት ይፋ ያደረጉት የጋራ ኤኮኖሚ አስተሳሰብ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ የር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ የጋራ ኤኮኖሚ ሃሳብ በሌሎች የዓለም ክፍሎች፣ በደቡብ ኮርያ፣ በፊሊፒን እና በቤኒን በመድረስ ከጊዜ ወደ ጊዜ በማደግ ላይ የሚገኝ ፕሮጄክት መሆኑን አስረድተዋል።  

31 May 2021, 18:05