ፈልግ

የሕንድ የኢየሱሳዊያን ማሕበራ አባላት በቅርቡ በሞት ለተለዩ የማሕበራቸው አባ ካህን ሽኝት አደረጉ። የሕንድ የኢየሱሳዊያን ማሕበራ አባላት በቅርቡ በሞት ለተለዩ የማሕበራቸው አባ ካህን ሽኝት አደረጉ። 

የሕንድ የኢየሱሳዊያን ማሕበራ አባላት በቅርቡ በሞት ለተለዩ የማሕበራቸው አባ ካህን ሽኝት አደረጉ።

በእስር ላይ የነበሩ የኢየሱሳዊያን ማሕበር ካህን አባ ስታን በእስር ላይ በነበሩበት ወቅት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የተገለጸ ሲሆን የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ማክሰኞ ሰኔ 29/2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በሙምባይ መፈጸሙ ተገልጿል። በቅርቡ በእስር ላይ በነበሩበት ወቅት በሆስፒታል ውስጥ ያረፉት የ 84 ዓመቱ የኢየሱሳዊያን ማሕበር ካህን በሕዝባቸው ዘንድ እጅግ በጣም የሚወደዱ እና የሚከበሩ ካህን እንደ ነበሩ ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የቀብር ስነ ስረዓታቸው የኮቭድ -19 ፕሮቶኮሎችን ከግምት ባስገባ መልኩ 20 ሰዎች ብቻ በተገኙበት ባንድራ በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ የተከናወነ ሲሆን ስነ ስረዓቱም በቀጥታ ስርጭት መተላለፉ ተገልጿል፣ በውጭ አገራት የሚገኙ ሰዎችን ጨምሮ በመላው አገሪቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የቀጥታ ስርጭቱን መከታተላቸው ተገልጿል።

አባ እስታን በምስራቅ ህንድ ጃሃርሃንድ ግዛት ውስጥ የሚገኙ ተወላጅ እና የተገለሉ ሰዎችን ጉዳይ ሲደግፍ የቆዩ ሲሆን እነዚህን የተገለሉ ሰዎችን በመርዳታቸው የተነሳ ለእስር ተዳርገው ነበር፣ ባለፈው ሰኞ ሰኔ 28/2013 ዓ.ም ሙምባይ ቅድስት ፋሚሊ ሆስፒታል ውስጥ የሕክምና አገልግሎት ሲያገኙ ከቆዩ በኋላ ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፣ በእስር ቤት በነበሩበት ወቅት በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ተይዘው የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።

በፓርኪንሰን በሽታ እና የመስማት ችግር በእስር ላይ በነበሩበት ወቅት በእነዚህ በሽታዎች ቀድም ሲል ተጠቅተው የነበሩ ሲሆን የ 84 ዓመቱ ካህን በጥቅምት 01/2013 ዓ.ም ከጃሃርካን ዋና ከተማ ራንቺ ከተማ ወጣ ብሎ ከሚገኘው የኢየሱሳዊያን ማሕበር ሥር ከሚተዳደረው ማሕበራዊ እርዳታ መስጫ ተቋም ማዕከል ባጊቻ በመባል ከሚታወቀው ከማኦይስት ታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው ተጠርጥረው መታሰራቸው ይታወሳል። በጥር 14/2013 ዓ.ም በማሃራሽትራ ግዛት በቢሚ ኮሬጋን መንደር ከተፈጠረው ሁከት በስተጀርባ ነበሩ ተብለው በአወዛጋቢው የሽብርተኝነት ሕገ ተጠርጥረው ሽብርተኝነትን እና አመፅን ለመዋጋት ኃላፊነት የተሰጠው በብሔራዊ የምርመራ ኤጀንሲ አማካይነት ለእስር መዳረጋቸው ይታወሳል። በማግስቱ ታሎጃ ማዕከላዊ እስር ቤት እንዲገቡ ተደርገው ነበር።

አባ አስታን “በሕይወቴ ጊዜያት በሙሉ ያልሄድኩበት ቦታ ነው” በማለት የተከሰሱባቸውን ክሶች በሙሉ ክደው የነበረ ሲሆን በእስር ላይ በነበሩበት ወቅት ሕይወታቸው ያለፈ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የሕንድ የእድሜ ባለጸጋ እስረኛ ለመሆን የበቁ ሲሆን የዋስትና መብት ተከልክለው ነበር።

የድሆችን ጩኸት መስማት

የአባ እስታን የቀብር ስነ ስረዓት በተከናወነበት ወቅት አባ አሩን ባደረጉት ንግግር አባ እስታን የክርስቶስን ምስል መላበሳቸውን የገለጹ ሲሆን አባ እስታን “መጽሐፍ ቅዱስ ‘በእግዚአብሔር የሚመኩ’ ብሎ የሚጠራቸውን  የድሆችን ፣ የተጨቆኑ ፣ የተገለሉ ሰዎችን ጩኸት አዳምጠዋል፣ ዋጋውን ለመክፈል ባለው ኃይል መሰቀል ነበረባቸው” በማለት መናገራቸው ተገልጿል።

በእለቱ በስርዐተ ቀብሩ ስነ ስረዓት ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል ከዮሐንስ ወንጌል የተወሰደ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ኢየሱስ ከተገረፈ በኋላ ጲላጦስ እንዲሰቀል አሳልፎ የሰጠበትን ሁኔታ የሚገልጽ የቅዱስ ወንጌል ክፍል ነበር። የአባ እስታን ተግባር እና ሥራ በከንቱ የሚቀር አይደለም ፣ ምክንያቱም “የፍቅር ኃይል ዛሬ በዓለማችን ውስጥ መስራቱን ይቀጥላል” ዓለም ለአብ የተሻለ ቦታ እንድትሆን አባ እስታን የበኩላቸውን ጥረት ማደረጋቸውም ተገልጿል።

የፍትህና የእርቅ ተልእኮ

በመልእክታቸው አባ ጄሪ ኩቲንሃ እንዳሉት አባ እስታን በመልካም እረኛ ጎዳና ተጓዙ፣ ከድሆች ጋር በመሆን የሕይወትን ሙላት ፣ በክብር እና ፍትህ ለመስጠት ይሞክሩ እንደ ነበረ መናገራቸው የተገለጸ ሲሆን ነገር ግን የ 84 ዓመቱ የኢየሱሳዊ ማሕበር አባል ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ የድሆችን እና ድምፃቸው የማይሰማ ሰዎች ድምፅ እንዲሰማ የበኩላቸውን አስተዋጾ ማድረጋቸው ተገልጿል።

አባ እስታን ለ 64 ዓመታት ያህል የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል የነበሩ ሲሆን ለ51 ዓመታት ያህል በክህነት ሕይወት አሳልፈዋል። መሬት አልባ አርሶ አደሮችን ፣ የጉልበት ሠራተኞችን እና የአገሬው ተወላጅ ነዋሪዎችን የመሬት መብቶች ለማስከበር የሚደረገውን ንቅናቄ ለማስከበር በማለም የተጀመረው በኃይል የተደገፈ የታጣቂዎች ቡድን  ይደግፋሉ በሚል ተጠርጥረው መታሰራቸው ተገልጿል። በተቃራኒው ግን አባ እስታን ጉልበታቸውን ሳይቆጥቡ በመስጠት ዕረፍት ሳይሹ ደከመኝ ሰለቸኝ ብለው ወሮታ ሳይፈልጉ የጉልበት ሥራን ጨምሮ በመሥራት ሕይወታቸውን የኖሩ የሎዮላው የቅዱስ ኢግናቲየስ ልጅ ነበሩ።

07 July 2021, 15:47