ፈልግ

እ.አ.አ ሐምሌ 11/2021 ዓ.ም በሜዲትራንያን ባህር ለሞቱት ስደተኞች ጸሎት የሚደረግበት ቀን ነው! እ.አ.አ ሐምሌ 11/2021 ዓ.ም በሜዲትራንያን ባህር ለሞቱት ስደተኞች ጸሎት የሚደረግበት ቀን ነው! 

እ.አ.አ ሐምሌ 11/2021 ዓ.ም በሜዲትራንያን ባህር ለሞቱት ስደተኞች ጸሎት የሚደረግበት ቀን ነው!

በጣሊያን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባሄ  ከአመታት በፊት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በእየዓመቱ እ.አ.አ. በሐምሌ 11/2013 ዓ.ም እለተ ሰንበት ቀን የሜድትራኒያን ባሕር አቋርጠው ወደ አውሮፓ አህጉር ለመግባት በሚሞክሩበት ወቅት ላፓዱዛ በሚባል የጣሊያን የወደብ ከተማ አቅራቢያ የተሳፈሩበት ጀልባ በመስጠሙ የተነሳ ነብሳቸውን ላጡት በርካታ ስደተኞች የጸሎት ቀን ሆኖ እንዲዘከር ውሳኔ ማስተላለፋቸው ይታወሳል። በዚህ መሰረት ይህ የጸሎት ቀን እ.አ.አ በሐምሌ 11/2021 ዓ.ም በተከበረበት ወቅት የጣሊያን የካቶሊል ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባሄ ባስተላለፈው መልእክት ክርስቲያኖች የሰላም መልእክተኞች እና የሥልጣኔ አስተማሪዎች እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ 632 በላይ ወንዶች ፣ ሴቶችና ሕፃናት በአውሮፓ የተሻለ ኑሮ ለመፈለግ በማሰብ ማዕከላዊውን የሜዲትራንያን ባሕር በማቋረጥ ላይ በነበሩበት ወቅት ጀልባቸው ሰምጦ ለሕልፈት ተዳርገዋል።

በአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) መረጃ መሠረት ከተመዘገቡት 632 ሰዎች ሞት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ 200 % ጭማሪን ማሳየቱ ተገልጿል። እነዚህን የመሳሰሉ አደጋዎች የጣሊያን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባሄ እንዳመለከተው “ህሊናን የሚያናውጥ እና የስደተኞችን ሁኔታ በአትኩሮት እንድንመለከት የሚያደርገን መጥፎ አጋጣሚ ነው” ማለታቸው ተገልጿል።

የጸሎት ቀን

የጣሊያን የጳጳሳት ጉባሄ አክሎ እንደ ገለጸው በተጨማሪም በሜድትራንያን እና በምድር መስመሮች ከድህነት ፣ ከግጭት ፣ ከስደት እና ከአየር ንብረት ለውጥ በመሸሽ የሞቱትን ሁሉ ለማስታወስ እ.አ.አ በሐምሌ 11 የስደተኞ የጸሎት ቀን ላይ ሁሉም እንዲሳተፉ መልካም ፈቃድ ያላቸውን ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ጥሪ ያቀርባል።

በባህር ላይ የሚሞቱ ስደተኞችን የሚመዘግቡ አስገራሚ አኃዛዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ፣ በየቀኑ አራት ሰዎች በተስፋ ጉዞአቸው ላይ እንደሚሞቱ የጣሊያን ጳጳሳትም አዳዲስ ጉዳይ የስደት መንገዶች መኖራቸውን አጉልተዋል። እነሱም ባለፈው ዓመት ከሰሃራ በረሃ መንገድ ቁጥራቸው እጅግ እየጨመረ የመጣውን የካናሪ ደሴቶች ፣ በሊቢያ ለሚገኙ የስደተኞች ካምፖች ሁኔታ እና ቀደም ሲል ብዙዎች በአደጋ ላይ እና በአስጊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙባቸውን የባልካን መንገዶች ይገኙበታል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ

የጣሊያን ጳጳሳት ጉባሄ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በሰኔ 13/2021 ዓ.ም የመላከ እግዚአብሔር ጸሎት ከደገሙ በኋላ ቅዱስነታቸው በወቅቱ አስተላልፈውት የነበረውን ጥሪ በማስታወስ “የሜዲትራንያን ባህር የአውሮፓ ትልቁ የመቃብር ስፍራ ሆኗል” በማለት አፅንዖት በመስጠት ምእመናንን “ልባቸውን ለስደተኞች እንዲከፍቱ” እና “ቤተሰቦቻቸውን ያጡትን እንዳይረሱ” በማለት ጥሪ አቅርበዋል ወደ ጣሊያን እና አውሮፓ የባህር ዳርቻዎች ለመድረስ በመሞከር ላይ የሚገኙ በርካታ ስደተኞ ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደ ሚገባ መልእክት አስተላፈዋል።

እ.አ.አ በሐምሌ 11/2021 ዓ.ም የተዘከረው የጸሎት ቀን “እያንዳንዱ ክርስቲያን የአውሮፓን ደጋፊ የሆነ አርአያ በመከተል የሰላም መልእክተኛ እና የስልጣኔ መምህር ለመሆን የሚያስችለንን ምክረ ሐሳብ ለማቅረብ እንፈልጋለን” በማለት የጣሊያን ጳጳሳት ጉባሄ መልክቱን ይደመድማል።

እ.አ.አ በሰኔ 8/2013 ላፓዱዛ በመባል በሚታወቀው በአንድ የጣሊያን የወደብ ከተማ አቅራቢያ የዛሬ ስምንት  አመት ገደማ በተለየያዩ አስገዳጅ ምክንያቶች የተነሳ ቤት ንበረታቸውን ጥለው በመሰደድ በከፍተኛ ደረጅ አስከፊ የሆኑ መንገዶችን በማለፍ በሊቢያ በኩል ወደ ጣሊያን በጀልባ ለመግባት ሲሞክሩ በነበረበት ወቅት በጀልባው ላይ በደርሰው አደጋ ከ3000 ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ይህ አደጋ በዓለም ዙሪያ የመነጋገሪያ አርእስት ሆኖ ማለፉ ይታወሳል።

በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አደጋው በደርሰበት ላፓዱዛ በመባል በምትታወቀው የጣሊያን የወደብ ከተማ ተገኝተው በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች ጸሎት ማደርጋቸው እና እንዲሁም ከእዚህ አስከፊ አደጋ በተዐምር የተረፉ ስድተኞች በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ከእዚያን ጊዜ አንስቶ በእዚህ  አሰቃቂ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ስደትኞችን በማስታወስ በእየአመቱ መስዋተ ቅዳሴ እንደ ሚያሳርጉ ይታወቃል። በእዚህም መሰረት በሊቢያ በኩል አድርገው ወደ ጣሊያን መለሻገር በሚሞክሩበት ወቅት እ.አ.አ. ልክ የዛሬ ስምንት ዓመት ገደማ ላፓዱዛ በመባል በሚታወቀው የጣሊያን የወደብ ከተማ አከባቢ ሕይወታችውን ላጡ ስደተኞች በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት በነሐሴ 01/2011 ዓ.ም መስዋዕተ ቅዳሴ በተደርገበት ወቅት ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “የስደተኞች ጉዳይ ማኅበራዊ ሳይሆን ሰብዓዊ ነው” ማለታቸው ይታወሳል።

12 July 2021, 12:40