ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ለእምድብር አገረ ስብከት ተተኪ ጳጳስ መሾማቸው ተገለጸ!
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለእምድብር አገረ ስብከት ተተኪ ጳጳስ አድርገው ክቡር አባ ተሾመ ፍቅሬ ወልደትንሳኤን በታኅሳስ 6/2016 ዓ.ም መሾማቸውን ቫቲካን ያስታወቀች ሲሆን ክቡር አባ ተሾመ ፍቅሬ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጲያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሆነው በማገልገል ላይ እንደሚገኙም ይታወቃል።
የግለ ታሪክ
ክቡር አባ ተሾመ ፍቅሬ ወልደተንሳኤ እ.አ.አ በሰኔ 6/1972 ዓ.ም በቀድሞ የአዲስ አበባ አገረ ስብከት በናደነ ቅዱስ ማርቆስ ቁምስና ተወልደው ያደጉ ሲሆን እ.አ.አ በ1992 ዓ.ም ወደ ዘረዐ ክህነት ትምህርት ቤት ገብተው በአዲስ አበባ በሚገኘው የቅዱስ ፍራንችስኮስ የፍልስፍና እና ሥነ መለኮት ተቋም የፍልስፍና እና የነገረ መለኮት ጥናት አድርገው አጠናቀዋል።
እ.ኤ.አ. በጥር 11/1998 ዓ.ም የእምድበር አገረ ስብከት ካህን ሆነው የተሾሙ ሲሆን በሮም ትምህርታቸውን አጠናቀው በምስራቃዊ ቀኖና ህግ የዶክትሬት ዲግሪ አግኝተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በግዕዝ ቋንቋ የተካኑ ናቸው። የአጣጥ ቁምስና ቆመስ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ከ10 ዓመታት በላይ የእምድብር የካቶሊክ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ ሆነው አገልግለዋል። እ.አ.አ በ 2017 ዓ.ም የኢትዮጲያ ካቶሊክ ጽሕፈት ቤት የሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ጸኃፊ ሆነው ተሹመው ያገለገሉ ሲሆን እ.ኤ.አ. ከ2019 ጀምሮ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ ሆነው እያገለጉሉ ይገኛሉ።
16 December 2023, 14:53