ፈልግ

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መወለድ የሚያሳይ የጥበብ ሥራ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መወለድ የሚያሳይ የጥበብ ሥራ 

የገና መልዕክት፡ 'በገና ወቅት ፊታችን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት የበራ ይሁን'

የመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ፍርሀት እና ጥርጣሬ በነገሰበት ጨለማው ዓለም ውስጥ ትልቅ የተስፋ ምልክት እና መልእክት ነው። ለዘንድሮ የገና በዓል የቫቲካን ሬዲዮ የሃይማኖት መሪዎች እና የክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅቶች ኃላፊዎች “የጌታ ልደት የሰላም ልደት ነው” በሚል መሪ ቃል አስተያየታቸውን እንዲሰጡ የጠየቀ ሲሆን፥ የዛሬው መልዕክት የተላለፈው ከኒውዚላንድ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት ከሆኑት የኦክላንድ ጳጳስ ስቲቭ ሎው ነው፥ እንደሚከተለው ይቀርባል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

                                        የጳጳስ ስቲቭ ሎው የገና መልዕክት
          የኦክላንድ ጳጳስ እና የኒውዚላንድ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት

‘ቴና ኩቱኡ፣ ካቶአ’ የገና ሰላምታ ኒው ዚላንድ ውስጥ ከምትገኘው ኦቴሮአ ከተማ ለእናንት ይሁን ፤ ለእኛ ኒውዚላንዳዊያን አሁን ጊዜው የበጋ ወቅት ነው፣ እናም ዛሬ በጥዋት፥ ገና ከመድረሱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ፥ ፀሀይ ስትወጣ በባህር ዳርቻው ላይ በእግር ለመጓዝ ሄድኩኝ። ፀሃይዋ በፀጥታ ከባህሩ ጀምበር ወጥታ ፊቴን በማለዳ ጨረሮች አበራች።

በተመሳሳይ መልኩ የሰላም አለቃ በሆነው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ፊታችንን እንድናበራ ተጋብዘናል። ወደ ቤተልሔም ጥልቅ ዋሻ ተጋብዘናል፣ ወደ እርሱ ፊት እንድንመለከት ተጋብዘናል፣ እርሱም ለሰው ሁሉ የተሰጠ የእግዚአብሔር ሰላም ነው። በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ ወደ ሰላም መሻቱ ምስጢር እንድንገባ ተጋብዘናል።

ሁላችንም እንድንመለከተው የተጋበዝንበት ፊት ይህ ነው። ፀሐይ መውጣቷ አዲስ ቀን እንደምትወልድ እና ፊታችንን እንደሚያበራልን። ብሩህ የሆነውን የህፃኑን ኢየሱስ ፊት አተኩረን ባየን ቁጥር በሰላሙ ይሙላን።

እኛ በተራው የምንፈነጥቀው ሰላም ለምናገኛቸው ሁሉ ይሁን፥ በተለይ ብስጭት ውስጥ ሰላምን የምናመጣ ይሁን፣ አለመቻቻል ውስጥ ሰላምን የምናመጣ ይሁን ፣ በንዴት ወይም በትዕግስት ማጣት ውስጥ ሰላምን የምናመጣ ይሁን።

የሰላሙን ልዑል ልደት ማክበር ብቻውን በቂ አይደለም፥ በፍጹም በቂ አይደለም፥ በሕይወታችን ውስጥ ያንኑ ሰላም መውለድ አለብን። የመዝሙሩ ቃላት እንደሚሉት፣ በምድራችን ላይ ሰላም ይሁን፣ እናም ሰላሙ በእኔ ይጀምር።

የህፃኑ ክርስቶስ ብሩህ ብርሃን ዛሬ በደስታ እና በሰላሙ ይሙላችሁ፥ ያንን ሰላም የተካፈላችሁ ሁኑ። የተባረከ እና በሰላም የተሞላ የገና በዓል ይሁንላችሁ።
 

29 December 2023, 14:08