የአየርላንድ ጳጳሳት በቤተሰብ ላይ የሚደረጉት የሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች ያሳስበናል አሉ
አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
መጪው አርብ፣ የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. አየርላንድ የሃገሪቷ ህገ መንግስት ስለ ቤተሰብ እና ለቤተሰብ ስለሚሰጠው እንክብካቤ የሚገልጸው አንቀጽ ላይ ያሉትን የቃላት አጠቃቀሞችን ለመቀየር በህዝበ ውሳኔ ድምጽ ለመስጠት ተዘጋጅታለች።
የአንቀጽ 41 ማሻሻያዎች
የአየርላንድ ዜጎች በሃገሪቷ ህገመንግስት አንቀጽ 41.1.1 ላይ ቤተሰብን ሲገልጽ “በጋብቻ ላይ የተመሰረተ” በሚለው ላይ “ሌሎች ዘላቂ ግንኙነቶች” የሚለውን አረፍተ ነገር ለማካተት በሚያስችል ማሻሻያ ላይ ህዝበ ውሳኔ እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል።ይህም በአሁኑ ጊዜ ሴት በቤት ውስጥ ሕይወቷ ለጋራ ጥቅም በማይውል መልኩ ለመንግሥት ድጋፍ የምትሰጥ በመሆኑ፥ በዚህም ምክንያት መንግሥት እናቶች በኢኮኖሚያዊ ፍላጎት ምክንያት የቤት ውስጥ ተግባራቸውን ትተው ተቀጥረው ለመሥራት የማይገደዱ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት የሚል ነው።
የቀረበው ማሻሻያ “በቤት ውስጥ ያሉ ሴቶች” የሚለውን አንቀፅ ይሰርዝ እና “በመካከላቸው ባለው ትስስር ምክንያት የቤተሰብ አባላት እርስ በርስ እንክብካቤ የሚሰጣጡ መሆን አለበት” የሚል አዲስ ዓረፍተ ነገር ያስገባል።
የአየርላንድ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ የካቲት 17 ባወጣው መግለጫ፥ “በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ያሉትን የእናትነት መብትን የሚጠቅሱትን ነገሮች በሙሉ የመሰረዝ” ውጤት እንደሚኖራቸው በመግለጽ በታቀዱት ለውጦች ላይ ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል።
ልዩ የሆነ የጋብቻ ባህሪ
በቤተሰብ ላይ የተደረገውን የመጀመሪያ ማሻሻያ በተመለከተ ጳጳሳቱ አዲስ የገባው ዓረፍተ ነገር “በጋብቻና በቤተሰብ መካከል ያለውን ግንኙነት በማህበረሰቡ እና በመንግስት ፊት ያለውን ልዩ ጠቀሜታ የሚቀንስ እና ወጣቶች ለጋብቻ ያላቸው አመለካከት እንዲዳከም” እንደሚያደርግ ጳጳሳቱ ተናግረዋል።
“‘ጋብቻ’ ህዝባዊ እና ህጋዊ ቁርጠኝነትን የሚጨምር ቢሆንም፣ ‘ዘላቂ ግንኙነት’ የሚለው ቃል በህጋዊ እርግጠኝነት የተሸፈነ እና ለሰፊ የህግ ትርጓሜ ክፍት ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
“የጋብቻ ቁርጠኝነት ለቤተሰብ እና ለህብረተሰቡ መረጋጋትን በማምጣት ልዩ በሆነ መንገድ ለጋራ ጥቅም አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት እናምናለን፥ በዚህም ምክንያት በአሁኑ ጊዜ በአየርላንድ ህገ-መንግስት የተረጋገጠ የመንግስት ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል” ብለዋል።
አንቀጽ 41.2ን በመሰረዝ አዲስ የሆነውን አንቀጽ 42 Bን የሚያስገባው የቤተሰብ እንክብካቤ ማሻሻያ አስመልክቶ መግለጫው “የአየርላንድ ሕገ መንግሥት ቀድሞውኑ በተለይ የቤተሰብን እና የቤት ውስጥ ፍላጎቶችን ለመንከባከብ ለሚፈልጉ እናቶች ምርጫ እውቅና ሰጥቶ እንደሚያመቻች” አመላክተዋል።
የአየርላንድ ሕገ መንግሥት ሴቶችን ከሥራ አይከለክልም
ጳጳሳቱ ‘ቤት’ የሚለው ቃል ከአንቀጹ መወገድን በተመለከተ ተመሳሳይ ስጋቶች እንዳላቸው ይገልጻሉ። ይሄንንም ሲያብራሩ “በወቅቱ ባለው ማህበረሰብ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ በሴቶች እና በወንዶች መካከል በቤት ውስጥ እንክብካቤን ጨምሮ በሁሉም የቤት ውስጥ ሕይወት በሴቶች እና በወንዶች መካከል ተቀባይነት ያለው የጋራ ኃላፊነት አለ” ካሉ በኋላ፥ “አሁን ያለውን የሴቶች ሚና እና የመኖሪያ አከባቢ እውቅና ከማስወገድ ይልቅ” ምንም ጠቀሜታ ዬለውም በማለት ጠቁመዋል።
በማከልም በመግለጫው እንዳብራሩት “መንግስት ለሴቶች እና ለወንዶች የሚሰጠውን እንክብካቤ መቀጠሉ ተመራጭ እና ከዘመናዊ ማህበራዊ እሴቶች ጋር የሚስማማ ይሆናል” ብለዋል።
"በቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጭ የሚደረግ እንክብካቤ የርህራሄ መሰረት ነው" በማለት ጳጳሳቱ በአጽንዖት የገለጹ ሲሆን ፥ “አሁንም ለቤተሰብ ተንከባካቢዎች በቂ የገንዘብ ክፍያ አቅርቦት እንደሚኖር ምንም ፍንጭ የለም” ብለዋል።
በህገ መንግስቱ ውስጥ የእናቶች ሚና ተከብሮ መቀጠል አለበት
እንደ አየርላንድ ጳጳሳት ገለጻ፥ የቀረበው ማሻሻያ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ያሉትን የእናትነት ማጣቀሻዎች በሙሉ በማጥፋት እና በቤት ውስጥ ያሉ እናቶች በአየርላንድ ያደረጉትን እና የሚያደርጉትን ልዩ እና የማይቆጠር ህብረተሰባዊ አስተዋፅዖን ሳይገነዘቡ የሚቀሩበት ውጤት ይኖረዋል በማለት ይገልጻሉ።
"አሁን ሊተገበሩ የታቀዱት ሕገ መንግሥታዊ ቃላቶች በምንም መልኩ ሴቶችን በማህበራዊ እና ህዝባዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ከመሥራት ወይም ተገቢውን ቦታ እንዲይዙ አያደርግም፥ ሆኖም ግን ማሻሻያው በቤተሰብ ውስጥ በተፈጥሮ የሚነሱ ተጨማሪ እና ልዩ ባህሪያትን ያከብራል” ሲሉ ገልጸዋል።
የአየርላንድ ጳጳሳት ሲያጠቃልሉ “የእናቶች ሚና በሕገ መንግስታችን ውስጥ እንደተከበረ መቀጠል አለበት” ሲሉ በድጋሚ ገልጸዋል።