ፈልግ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርስቲን ጎበኙ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርስቲን ጎበኙ 

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርስቲን ጎበኙ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስትር ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አዲስ አበባ፥ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን እና በቅዱስ አኪውነስ ስም የተሰየመውን የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሆነውን ኢኩስታ (Ethiopian Catholic University St Thomas Aquiuness -ECUSTA) ዛሬ ሚያዝያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ከብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ፕረዚዳንት፣ ከብጹእ አቡነ ሉቃስ የእምድብር ሃገረ ስብከት ተተኪ ጳጳስ፣ ከክቡር አባ ዳንኤል ሃሶ በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት የትምህርት ክፍል ሃላፊ እና ከከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ጎብኝተዋል።

አዘጋጅ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ክቡር ሚንስትሩ ተቋሙን የጎበኙት የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ውስጥ የምታበረክተውን ከፍተኛ አስተዋጽዖ እና ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ለማበረታታት እና ከዚህም በተሻለ መልኩ እንድትሰራ በትግበራው ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሟትን ተግዳሮቶች መቅረፍ በሚቻልባቸው እና ከመንግስት ጋር በትምህርት ዘርፍ ላይ አብሮ ለመስራት የሚያስችሉ መንገዶች ላይ ተቀራርቦ ለመወያየት እንደሆነም ተገልጿል።

ብጹእ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ በመርሃ ግብሩ ላይ ለክቡር ሚኒስትሩ እና ለእንግዶቹ ባደርጉት ገለፃ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ ላይ ያበረከተችውን እና እያበረከተች ያለውን አበርክትሆ አጠር ያለ ንግግር ካደረጉ በኋላ፥ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ በርካታ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንዳያሰለጥን እንቅፋት ከሆኑት ችግሮች ውስጥ ወደ ተቋሙ የሚወስደውን የመንገድ ችግር በማንሳት መንግስት አስፈላጊውን ነገር ሁሉ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ ተቋሙ እየሰራቸው ያሉትን ሥራዎች ዞረው ከጎበኙ በኋላ ባደረጉት ንግግር መንግስት ተቋሙ ያሉባቸውን ችግሮች ለመቅረፍ የሚቻልባቸውን መንገዶች ለማመቻቸት ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሆነው ‘የቅዱስ ቶማስ አኪውነስ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ’ ኢኩስታ በአሁኑ ወቅት በሜዲስን፣ በሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኖሎጂ እና በሶሻል ዎርክ የትምህርት ዘርፎች 247 የሚሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያሰለጠነ የሚገኝ ሲሆን፥ ወደፊት ከመንግስት ጋር ተቀራርቦ በመስራት ከዚህ በተሻለ መልኩ የትምህርት ዘርፎችን በማስፋፋት በርካታ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የአጭር ጊዜ ዕቅዶችን ቀርጾ እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው እስከ ዛሬ ድረስ ለዘጠኝ ጊዜያት ያህል ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች አሰልጥኖ አስመርቋል።  

 

 

 

29 April 2024, 14:46