በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት በሮም የምያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝ
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ከሐዋርያዊና ከባህላዊ እይታ አንጻር "የአጥቢያ" ቤተ ክርስትያን በእነዚህ ችግሮች ላይ እንዴት ጣልቃ እንደምትገባ፣ በጣም ችግር ያለባቸው ጉዳዮች ምን መሆናቸውን የምትለይበት እና የመፍትሄ ሐሳቦችን እና አቅጣጫዎችን የምታቀርብበትና ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የሚመካከሩበትን አጋጣሚ የሚፈጥር ሐዋርያዊ ጉብኝት እና መንፈሳዊ ንግደት ነው።
በላቲን ቋንቋ “ad limina apostolorum” (አድ ሊሚና አፖስቶሎረም) የሚለው አገላለጽ በቤተ ክርስቲያኗ ታሪክ የመጀመሪያዎቹ መቶ ዓመታት ውስጥ መታየት የጀመረ ክስተት ነው፥ እንዲያውም በቀኖናዊ ቋንቋ ‘ሊሚና አፖስቶሎረም’ የሐዋርያው ጴጥሮስና የጳውሎስን መካነ መቃብር ሥፍራ በመጎብኘት የሚገኘውን መንፈሳዊ በረከት አመላክቶ ያለፈ ክስተት ሲሆን ስለዚህም የእነዚህ መንፈሳዊ እና ሐዋርያዊ ጉብኝቶች ግባቸው ተመሳሳይ ጉዳዮችን የሚፈጽሙትን፣ የቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ ክቡር እና ቅዱስ የሆነ አጽማቸው ያረፈበትን የመካነ መቃብር ሥፍራ በመሄድ መንፈሳዊ ንግደት የሚያደርጉትን የምዕመናንንም ንግደት ስያማመላክት እንደ ነበረ ታሪክ ያወሳል፣ በጊዜው መዕመናን የሚያደርጉትን መንፈሳዊ ንግደት ስያመላክት ቆይቷል። እ.አ.አ በ745 ዓ.ም በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን 91ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዘካሪያስ በእርሳቸው ሥር በሮም ጉባኤ እንደተቋቋመው፣ ሁሉም ጳጳሳት ወደ ሮም የሚያደርጉትን ጉብኝት የሚያመለክት ነበር።
ባለፉት መቶ ዓመታት ዘመናት ውስጥ ይህ ልምምድ ቀስ በቀስ እየደበዘዘ መጥቶ የነበረ ሲሆን እ.አ.አ በ 1585 ዓ.ም እንደገና ተመልሶ ጥንካሬውን እያገኘ ማንሰራራት ጀምሮ ነበር፥ 227ኛው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሲክስተስ 5ኛ (1585-1590) በወቅቱ ባወጡት ሐዋርያዊ ሕገ ጋት የእንደዚህ ዓይነቶቹ ሐዋርያዊ ንግደቶች በየሦስት አመቱ እንዲደረግ የሚያስገደድ ሐዋርያዊ ግዴታ እንዲወጣ አድርገው ነበር፣ "ይህ መንፈሳዊ ንገደት" በኋላ ላይ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 14ኛ እ.አ.አ በህዳር 23 ቀን 1740 ዓ.ም በላቲን ቋንቋ ‘Quod sancta” (ያ ቅዱስ) በተሰኘው ድንጋጌ ማረጋገጫ ተሰጥቶታል። ይህ ሁሉ የተከሰተው በፀረ-ተሐድሶ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሐዋርያዊ ኃላፊነታቸውን እና ግዴታቸውን ለመወጣት እንዲሁም በመቆጣጠር ረገድ በጳጳሱ ሐዋርያው ሥልጣን ማጠናከሪያ አውድ ውስጥ የተፈጸመ ጉዳይ ነው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሲመረጡ ጉዳዮን በበላይነት የሚቆጣጠረው እና የምያስፈጸመው ማሕበር ይህ መንፈሳዊ ንግደት እና ሐዋርያዊ ጉብኝት በእየአምስት አመቱ እንዲካሄድ እ.ኤ.አ. በ 1909 ዓ.ም የደነገገ ሲሆን (10 አመት ከአውሮፓ አህጉር ውጪ ላሉ አገሮች) ይህ ንግደት እና ሐዋርያዊ ጉብኝት በጳጳሳት ቢቻ የሚከናወን ሳይሆን የየአገሮቹ አበሜኒቶች፣ የአገረ ስብከት አስተዳዳሪዎች ጭምር እንዲሳተፉ ድንግጎ ነበር። እ.ኤ.አ. በ 1975 ዓ.ም የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጉባኤ በወጣው አዋጅ “አድ ሮማናም ኤክሌዚያም “ሐዋርያዊ ጉብኝቱ” እንደገና በማደራጀት በእየአምስት አመቱ እንዲከናወን ወስኖ ነበር።
እ.ኤ.አ. በ 1983 ዓ.ም ይፋ የሆነው ሕገ ቀኖና ይህን ሐዋርያዊ ጉብኝት በተመለከተ ሁለት ቀኖናዎች ድንግጓል (399 እና 400)።
“የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ በሐዋርያዊ መንበረ ጵጵስና በተቋቋመው ቅጽና ጊዜ መሠረት በአደራ የተሰጣቸውን የሀገረ ስብከቱን ሁኔታ የሚመለከት ሪፖርት በየአምስት ዓመቱ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል (...) የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሪፖርቱን ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲያቀርቡ በተፈለገበት ዓመት፣ በሐዋርያዊ መንበር ካልተቋቋመ በስተቀር፣ ወደ ሮም እና ቫቲካን በመሄድ የብፁዕን ሐዋርያት ጴጥሮስና የጳውሎስን መካነ መቃብርለመሳለም እና እራሳቸውን ለሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ማቅረብ ይኖርባቸዋል” ሲል ደንግጓል።