ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በካናዳ ሐዋርያዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በካናዳ ሐዋርያዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት   (Vatican Media)

የካናዳ ቤተ ክርስቲያን ከአገሬው ተወላጆች ጋር ያደረገችውን እርቅ ሕያው ለማድረግ እንደምትፈልግ ገለጸች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2022 ዓ. ም. ወደ ካናዳ ያደረጉትን “የንስሐ ንግደት” ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት የካናዳ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት አቡነ ዊልያም ማክግራታን፥ በካናዳ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እየተወሰደ ያለው ተጨባጭ ተግባር እውነትን እና ከአገሬው ተወላጆች ጋር የተደረገውን ዕርቅን ሕያው ለማድረግ የሚረዳ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ወደ ካናዳ ያደረጉት የንስሐ ጉዞ የአገሪቱ ብጹ ዓን ጳጳሳት ተስፋ ያደረጉት የመጀመሪያ ደረጃ እና ከአገሬው ተወላጆች ጋር ዕርቅን ለማድረግ ባደረጉት ጉዞ ትርጉም ያለው እርምጃ እንደ ነበር የወቅቱ የካናዳ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚደንት እና የካልጋሪ ጳጳስ አቡነ ዊልያም ማክግራታን ተናግረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን ወደ ካናዳ የደረጉትን ሐአዋርያዊ ጉብኝት ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያን አስመልክተው ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት አቡነ ማክግራታን፥ ባለፉት ሁለት ዓመታት በካናዳ ቤተ ክርስቲያን ያከናወኗቸውን ተጨባጭ ውጥኖች፣ ለሕክምና እና ለዕርቅ ፕሮጀክቶች የተሰበሰበ 30 ሚሊዮን ዶላርን ጨምሮ የቤተ ክርስቲያኒቱን መዛግብት ግልፅ እንዲሆኑ በማመቻቸት እና ቀጣይ የውይይት እና የማዳመጥ ጥረቶች መደረጋቸውን አስረድተዋል።

የመጀመሪያ ደረጃ ጥረቶች
ብጹዓን ጳጳሳቱ ፅንሰ-ሃሳብ በታሪካዊ እና ትምህርታዊ ዕይታን በመመርመር ላይ ያተኮሩትን "የግኝት ትምህርት" እየተባለ የሚጠራውን ጥልቅ ግንዛቤ ለማስተዋወቅ ያለመ ውይይቶች ላይ ያተኮረ ከመሆኑ በተጨማሪ በቫቲካን ቤተ መዘክሮች የተያዙ ቅርሶችን በተመለከተ ከካናዳ መንግሥት ጋር በመተባበር አንዳንድ ይዞታዎችን መመለስ የሚቻልበትን ሁኔታ መመርመርን በማስመልከት በቅርቡ ውይይት ጀምረዋል።


አቡነ ማክግራታን እንዳብራሩት፥ እነዚህ የመጀመሪያ ደረጃ ጥረቶች እንደሆኑ እና ከእነርሱም መካከል አንዳንዶቹ ይበልጥ ቀዳሚ በሆነ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቢሆንም ወደፊት የተወሰነ ፍሬ እንደሚያፈሩ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ወቅታዊ ፈተናዎች
አቡነ ማክግራታንም እንዲሁም፣ በአገር በቀል እርቅ ፈንድ በኩል አገር በቀል ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ የተደረገው ጥረት ያለፈውን ብቻ ሳይሆን የካናዳ ተወላጅ ማኅበረሰቦችን የጤና አጠባበቅ እና የማኅበራዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ጨምሮ ወቅታዊ ጉዳዮችን ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንደረዳቸው አስረድተዋል።

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በካናዳ ሐዋርያዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት
ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በካናዳ ሐዋርያዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት

“የአዳሪ ትምህርት ቤቶች ውርስ እና አንዳንድ የመንግሥት ፖሊሲዎች አብዛኛዎቹ ካናዳውያን እና ካቶሊክ ምዕመናን የማያውቁትን የማግለል ሥ ር ዓት እንደነበር ማየት ጀምረናል” ሲሉ አቡነ ማክግራታን ተናግረው፥ ይህም የበለጠ ንቁ ለመሆን እና የበለጠ ለመገንዘብ እንዲሁም እራሳችንን ለማስተማር የመጀመሪያው እርምጃ ይመስለኛል” ብለዋል።

ተጨባጭ እውነታ
የካናዳ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት አቡነ ማክግራታንም እንዳሉት፥ “በፈንዱ የሚደገፉ ፕሮጀክቶችን የሚለይ የአገሬው ተወላጆች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አንዳንድ ፍሬዎችን ማየቱ፥ ካቶሊክ ምዕመናን የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሌሎች ተወላጆች ሥራን እንዴት እንደሚደግፍ የበለጠ ለመገንዘብ ይረዳቸዋል” ብለዋል። “እርቅን እና እውነትን የመፈለግ ተጨባጭ እርምጃ መኖሩን እና ትርጉም ባለው መንገድ እየተሳተፉ መሆኑን ለማወቅ የሚረዳቸው ይመስለኛል” በማለት አክለዋል።

የካናዳ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት በመጨረሻም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሰዎችን እና ባሕልን በመቅረጽ አስፈላጊነት ላይ አጽንዖት መስጠታቸውን በማስታወስ የአዳሪ ትምህርት ቤት ሥርዓት አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው አምነው፥ “አሁን የምንወስዳቸው እርምጃዎችም እውነትን እና እርቅን ካናዳ ውስጥ በአገሬው ተወላጅ ማኅበረሰቦች መካከል ተጨባጭ ለማድረግ እንደሚረዳ ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ካናዳ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት አቡነ ዊልያም ማክግራታን ጋር ሲገናኙ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ካናዳ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት አቡነ ዊልያም ማክግራታን ጋር ሲገናኙ

 

01 August 2024, 22:28