ፈልግ

የኬንያ ፖሌቲካዊ ተቃውሞ የምያሳይ ምስል የኬንያ ፖሌቲካዊ ተቃውሞ የምያሳይ ምስል   (AFP or licensors)

የኬንያ ጳጳሳት፡ የሀገራችን ወጣቶች መታመን ይገባቸዋል ማለታቸው ተገልጿል።

በቅርቡ በኬንያ ወጣቶች የተደረጉ የፖለቲካ ሰልፎችን ተከትሎ የሀገሪቱ ጳጳሳት ወጣቶች የህዝቡ አመኔታ ይገባቸዋል ሲሉ መናገራቸው የተገለጸ ሲሆን ሁሉም ሰው አብያተ ክርስቲያናትን እንደ ቅዱሳን ቦታዎች አድርጎ እንዲጠብቅ ጠይቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የኬንያ ካቶሊካዊ ጳጳሳት ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነውን የሀገሪቱን ህዝብ የሚሸፍነው ወጣቱ ትውልድ በመጨረሻ የኬንያን የወደፊት እድል እንደሚገነባ እና እምነት ሊጣልበት እንደሚገባ አስታውሰዋል።

የቫቲካን የፊደስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ጳጳሳቱ ይህንን አስተያየታቸውን የሰጡት ባለፉት ሳምንታት ወጣቶች ወደ ጎዳና በመውጣት የታክስ ጭማሪን ከመቃወም ባለፈ የፖለቲካ ሰልፎችን ካደረጉ በኋላ ነው።

የናይሮቢ ሊቀ ጳጳስ፡ 'በጋራ ጥቅም ላይ በአንድነት እንቆማለን’

ኬንያውያን እ.ኤ.አ. ሐምሌ 7 ቀን 1990 ዓ.ም ነፃ ምርጫን ለመጠየቅ ያደረጉትን ብሄራዊ ተቃውሞ በሚያስታውሱበት በሀገሪቱ ልዩ ቀን በሆነው በሳባ ሳባ ቀን በቅድስት ቤተሰብ ባሲሊካ ለወጣቶች ባስተላለፉት መልእክት የናይሮቢ ሊቀ ጳጳስ ፊሊፕ አርኖልድ አንዮሎ እንደ ገለጹት ከሆነ ወጣቶች ሁሉንም የጎሳ እና የፓርቲ ክፍፍል በማሸነፋቸው አወድሰዋል።

“ትግላቸው በአንድ የጋራ ጥቅም፣ በጋራ ሰብአዊነት እና በኬንያ ዜጎች የጋራ ማንነታችን አንድ መሆናችንን ያስታውሰናል” ብሏል።

“ኬንያን ከጎሳ ቁርኝታችን እና ከግል አጀንዳችን የበለጠ አስፈላጊ ነገር አድርገን መቁጠራችን ብቻ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው” ሲሉ አክለውም የገለጹ ሲሆን “ከራስ ወዳድነት ነፃ እንድንሆን፣ ሌሎችን እንደ ራሳችን እንድናስብ ይጠይቃሉ፣ ከብዙዎች የሚለዩን ድንበሮች እና ማዕረጎች አልፈን እንድንሄድ ይጠይቁናል" ብለዋል።

የንጎንግ ጳጳስ፡ ትክክለኛ ጥያቄዎችን ያነሳሉ።

ከ2 ሚሊዮን ነዋሪዎች መካከል ወደ 250,000 የሚጠጉ የተጠመቁ ሰዎች ያሏት የንጎንግ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ጆን ኦባላ ኦዋ ለፊደስ እንደተናገሩት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሕዝባዊ ተቃውሞ ከተጀመረ አምስተኛ ሣምንት ላይ መሆናቸውን ገልጸው ነገር ግን “ለጊዜው ነገሮች ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው የሚመለሱ ይመስላል” ሲሉ አክለው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

"በእነሱ ሀሳብ የሚያምኑ እና ትክክለኛ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ወጣቶች ናቸው" ብሏል ጳጳሱ። "የህብረተሰባችንን እውነተኛ ችግሮች፣ አስፈላጊ የሆኑ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ፣ ታክስ፣ ሙስና፣ ከፍተኛ የስራ አጥነት መጠን ከፍተኛ ብቃት ባላቸው ወጣቶች እና ምንም እንኳን ለዓመታት በትምህርት ገበታ ቢቆዩም በእውቀት ላይ ያተኮሩ ናቸው፣ ነገር ግን ወጣቱ የመኖሪያ ቤት የለውም፣ በአብዛኛው ሥራ አጥ ነው ብለዋል።

ፍትሐዊ ፍላጎታቸውን ለማሳካት፣ “ብዙዎቹ በሕይወታቸው ከፍተኛ ዋጋ ከፍለዋል ወይም ተጎድተዋል” በማለት ጳጳሱ የተናገሩ ሲሆን  አሁንም እ.አ.አ በነሐሴ 8 ታላቅ ሰልፍ ይጠበቃል ሲሉ አክለው ተናግረዋል።

"የባለብዙ ዘርፍ ውይይት" ያስፈልጋል

የቤተክርስቲያን ተቀዳሚ የአመራር አባላት ለወጣቶቹ አጋርነታቸውን አሳይተዋል፤ ይህ ቃል በብዙዎች ዘንድ ቁርጠኝነት የላቀ የፍትህና የማህበራዊ ሰላም ዘር ነው።

አቡነ ኦባላ ኦዋዋ “ኬንያን የተሻለች አገር ለማድረግ የሚፈልግ ታላቅ ​​የአንድነት ስሜት አለ፣ ስለዚህም የድጋፍ መግለጫዎችን እና ቃል ኪዳኖችን የገቡ ሲሆን "ለእኛ በጣም ውድ የሆነውን ጽንሰ-ሐሳብ ደግመን እንገልጻለን" ሲሉ አጽንዖት ሰጥቷል እሱም "የባለብዙ ዘርፍ ውይይት አስፈላጊ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

አብያተ ክርስቲያናት ሁል ጊዜ የተቀደሱ ቦታዎች ሆነው መቆየት አለባቸው

"በአንድ ቅሬታ በሚኖርበት ቤተሰብ ውስጥ እንደሚደረገው ሁሉ የተሻለው መፍትሄ መነጋገርና መደማመጥ ነው" ብሏል። "ከወጣቶቹ ጋር በጣም ተቀራርበናል እናም በእነሱ እና በፖለቲካ መሪዎች መካከል የውይይት ሂደት ጀምረናል" ሲሉ ተናግረዋል።

ከሰሃራ በስተደቡብ ባሉ የአፍሪካ ማህበረሰቦች ውስጥ አብዛኞቹ ወጣቶች ሲሆኑ ከጠቅላላው ህዝብ ወደ 80 በመቶ የሚጠጉ ናቸው።

"ለወጣቶቹ ቤተክርስቲያናችን ክፍት መሆኗን አሳይተናል፣ ችግራቸውን እንዲነግሩን እንጋብዛቸዋለን" በማለት ፖለቲከኞች እንዳይጋበዙ እና አብያተ ክርስቲያናት የተቀደሱ ሥፍራዎች ሆነው እንዲቀጥሉ እና መሳሪያ የማይጠቅሙ ቦታዎች እንዲኖሩ መጠየቃቸውን አረጋግጠዋል።

ጳጳሱ "በአንድ ነገር እርግጠኞች ነን፣ እነዚህ ወጣቶች የፈፀሙት ነገር ብዙ መዘዝ እንደሚያስከትል እና እውነተኛ ለውጦችን እንደሚያመጣ" ተናግረዋል።

01 August 2024, 15:06