ፈልግ

Cookie Policy
The portal Vatican News uses technical or similar cookies to make navigation easier and guarantee the use of the services. Furthermore, technical and analysis cookies from third parties may be used. If you want to know more click here. By closing this banner you consent to the use of cookies.
I AGREE
የማታ ጸሎት በላቲን ቋንቋ
መርዐ-ግብር በድምጽ የቀረበ ዘገባ
የፊሊፒንስ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቡነ ፓብሎ ቨርጂሊዮ ዴቪድ የፊሊፒንስ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቡነ ፓብሎ ቨርጂሊዮ ዴቪድ  

የፊሊፒንስ ጳጳሳት ምእመናን በቤተክርስቲያን ተልእኮ ውስጥ የበለጠ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅረቡ!

የፊሊፒንስ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቡነ ፓብሎ ቨርጂሊዮ ዴቪድ በማኒላ እየተካሄደ ባለው “የሰበካ ካህናት ብሔራዊ ስብሰባ” ላይ ካህናት ከምእመናን ጋር የመጋቢነት ኃላፊነታቸውን እንዲጋሩ አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

እ.አ.አ ከሐምሌ 29 እስከ ነሀሴ 1/2024 ዓ.ም የሚቆየው ዝግጅቱ 250 ካህናትን ከተለያዩ የሀገሪቱ አህጉረ ስብከት በመሰብሰብ በሲኖዶሱ ርዕሰ ጉዳዮች እና ተግባራት ላይ ተወያይቷል።

አቡነ ዴቪድ ብዙ ጊዜ ካህናቱ የሚሸከሙትን ሸክሞች ለማቃለል ምእመናንን ማበረታታት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

“አገልጋዮች ሆነው የተሾሙ ካህናት፣ በሐዋርያዊ ተልእኮዎች ውስጥ የተለየ ሚና አላቸው። ነገር ግን የዚህ ተግባር ሸክም ይበልጥ ቀላል የሚሆነው ምእመናን በቤተክርስቲያኗ ሕይወት እና ተልእኮ ውስጥ ትርጉም ባለው መልኩ እና በብቃት እንዲሳተፉ ማበረታታት ሲቻል ነው ብለዋል።

በፊሊፒንስ አዲስ የወንጌል ስርጭት ኮሚሽን አዘጋጅነት በቫቲካን በሚገኘው የሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ ሲስተር ናታሊ ቤካርትን ጨምሮ ታዋቂ ሰዎች ንግግር እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል።

አቡነ ዴቪድ በባህላዊው የቄስ ማዕቀፍ ምክንያት በርካታ ቀሳውስት ብቻቸውን እንደ ሻማ የሚቀልጡበት ሁኔታን አጉልተው ገልጸው “በጣም አላስፈላጊ” በማለት ገልጸው እና የበለጠ የትብብር አቀራረብን በመደገፍ ላይ ናቸው ብለዋል።

የማኒላ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ጆሴ አድቪንኩላ በመክፈቻው ቅዳሴ ላይ ባደረጉት ስብከት፣ ካህናት “የቤተክርስቲያናችን ሲኖዶስ ምስክሮች” እንዲሆኑ እና በሰበካ ማህበረሰቦች ውስጥ እውነተኛ ሕብረት እንዲፈጥሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ኃጢአተኞችን፣ ድሆችን እና የተገለሉትን ጨምሮ ሁሉንም ያካተተ እንግዳ ተቀባይ ቤተክርስቲያን እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥው ተናግረዋል። ድሆችን ካልሰማን እግዚአብሔርን እንሰማለን ወይ? ሲሉ ካርዲናል አድቪንኩላ ጠይቀዋል።

የፊሊፒንስ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዘዳንት አቡነ ማይሎ ሁበርት ቬርጋራ፣ ካህናት ከምእመናን ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ደስታን እና ግልጽነትን እንዲቀበሉ፣ የምእመናንን ድፍረት እና አስተዋጽዖ የምታውቅ እና የምትደግፍ ቤተክርስቲያንን በማስተዋወቅ እንዲሰሩ አበረታተዋል።

በጣሊያን ሳክሮፋኖ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የምእመናን እና የካህናት ስብሰባ ላይ የተወያየውን ምክረ ሐሳብ ያስቀጠለው የሰበካ ካህናት ብሔራዊ ስብሰባ ሲሆን በሮም ሲኖዶስ በተደረገው የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ከሲኖዶሱ የተወሰዱ ትምህርቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ ነው።

በማኅበረሰባዊ መግባባት ላይ ያተኩራል፣ እናም በቀሳውስቱ መካከል ያለውን ተሳትፎ እና መግባባት ማሳደግ ይችላል ተብሎ የታቀደ ስብሰባ ነው።

የጳጳሳት ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ ብፁዕ ካርዲናል ማሪዮ ግሬች ከዚህ ቀደም በፊሊፒንስ ባደረጉት ጉብኝት፣ ሲኖዶሳዊነት የካህናት እና የኤጲስ ቆጶሳት ስጦታ እንደሆነ ገልጸው፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን ልዩ ልዩ ምሥክርነት የሚያከብር አገልግሎት ይደግፋሉ።

የትብብርን አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተዋል "የእርስ በርስ አገልጋዮች እና ቸርነትን መንፈስ ማክበር አለብን። እርስ በርሳችን መማማር እንችላለን ሲሉ የጳጳሳት ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ ብፁዕ ካርዲናል ማሪዮ ግሬች ተናግረዋል።

 

01 Aug 2024, 15:03
Prev
February 2025
SuMoTuWeThFrSa
      1
2345678
9101112131415
16171819202122
232425262728 
Next
March 2025
SuMoTuWeThFrSa
      1
2345678
9101112131415
16171819202122
23242526272829
3031