ፈልግ

በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የብዙሃን መገናኛ ባለሞያዎች ኅብረት “SIGNIS” ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ፒተር በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የብዙሃን መገናኛ ባለሞያዎች ኅብረት “SIGNIS” ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ፒተር  

የሰው ሠራሽ አስተውሎት ባደገበት ዓለም ሲኖዶሳዊነት እና ጋዜጠኝነት መፍትሄ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገለጸ

በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የብዙሃን መገናኛ ባለሞያዎች ኅብረት “SIGNIS” ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ፒተር በፊሊፒንስ በተካሄደው የመገናኛ ብዙሃን መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። ዋና ጸሐፊው ለጉባኤው ተካፋዮች ባሰሙት ንግግር የሰው ሰራሽ አስተውሎት ትክክለኛውን የሰው ልጅ ግንኙነቶችን እንዴት አድርጎ ሊያበረታታ እንደሚችል መገምገም አስፈላጊ መሆኑን አጉልተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በፊሊፒንስ ሊፓ ከሐምሌ 29-ነሐሴ 2/2016 ዓ. ም. ድረስ የተካሄደው ብሔራዊ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ መገናኛ ጉባኤ፥ የማኅበራዊ መገናኛ ባለሙያዎችን፣ የሚዲያ ባለሙያዎችን እና የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን በማሰባሰብ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ላይ ተወያይቷል።

የኅብረቱ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ፒተር በመክፈቻ ንግግራቸው፥ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በማኅበራዊ መገናኛ ተልዕኮዎች ውስጥ ትክክለኛ የሰው ልጅ ግንኙነቶችን እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል መገምገም አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል።

ዶ/ር ፒተር “በአገልግሎታችን መካከል ሰው ሰራሽ አስተውሎትን መቼ እና እንዴት መጠቀም እንደሚገባ ለመወሰን ራሳችንን መጠየቅ አለብን ብለው፥ ይህም ከማኅበራዊ ሚዲያ ተከታዮቻችን እና ከቁምስናዎቻችን የበለጠ ይቀርበናል ወይ?” ሲሉ ወሳኝ ጥያቄ አቅርበዋል።

ስው ሰራሽ አስተውሎት ለተልዕኮዎች እና ሂደቶች ፈጣን እና ቀልጣፋ ቢሆንም እኛ ከምንጽፋቸው ሰዎች ጋር እና ከምንጽፋቸው ርዕሦች ጋር ለሲኖዶሳዊ ጉዞዎች ወሳኝ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።

“በብዙ አጋጣሚዎች በእውነት ማዳመጥ ሂደቱ ብቻ ሳይሆን መፍትሄውም ጭምር ነው” በማለት ከእርሳቸው ቀደም ብለው የተናገሩትን የቫቲካን መገናኛዎች ባልደረባ የእህት ኒና ክራፒክ ንግግር ጠቅሰዋል።

በኅብረት መጓዝ እና በእውነት መደማመጥ የዋና ጸሐፊው የዶ/ር ፒተር የሲኖዶሳዊነት ዋና መልዕክት ፅንሰ-ሃሳቦች ናቸው። የማኅበራዊ መገናኛ ባለሙያዎች ሰው ሰራሽ አስተውሎት “AI” ርቀትን ከመፍጠር ይልቅ ማኅበራዊነትን እና አብሮነትን ማጎልበቱን እንዲያረጋግጡ አሳስበዋል።

ዶ/ር ፒተር ከችግሮች ጎን ለጎን የመፍትሄ ሃሳቦችን በማቅረብ ላይ የሚያተኩረውን የጋዜጠኝነት የመፍትሄ ሃሳቦችን ደግፈው፥ ሰው ሰራሽ አስተውሎት መረጃን በመተንተን እና አዝማሚያዎችን በመለየት ሊረዳ እንደሚችል ቢታመንም ነገር ግን የማኅበራዊ ግንኙነቶች ዓላማን ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የብዙሃን መገናኛ ባለሞያዎች ኅብረት ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ፒተር
በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የብዙሃን መገናኛ ባለሞያዎች ኅብረት ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ፒተር

የማኅበራዊ መገናኛ ባለሙያዎች የተልዕኮአቸው ስኬት የሆነውን የመጨረሻ ታሪክ ከመናገር ባለፈ በጉዞአቸው ያጋጠሙትን ፈተናዎች እና ውድቀቶች በእኩልነት እንዲገልጹ አሳስበዋል።

ይህም የተልዕኮው አካል ያልሆኑ እና ምናልባትም የካቶሊክ እምነት ተከታይ ያልሆኑት፥ ቤተ ክርስቲያን በኅብረተሰቡ የተገለሉትን ለመደገፍ እያደረገች ያለውን ጥረት ሙሉ በሙሉ ለማድነቅ እንደሚያስችላቸው ጠቁመዋል።

በጉባኤው መካከል የተካሄዱ አውደ ጥናቶች እና የፓናል ውይይቶች የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያዎችን በማኅበራዊ መገናኛዎች በመዳሰስ፥ የኢንደስትሪው መሪዎች ሰው ሰራሽ አስተውሎት ልዩ ልዩ ታሪኮችን በመንገር እና የተመልካቾችን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለውን አቅም በመጥቀስ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማጋራት በሥነ ምግባር አጠቃቀም አስፈላጊነት ላይ መግባባትን ፈጥረዋል።

“በትክክለኛ ተጽእኖ ፈጣሪ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካይነት ቤተ ክርስቲያንን ብቁ ማድረግ” የሚለው የጉባኤው መሪ ሃሳብ፥ ሰው ሰራሽ አስተውሎት በማኅበራዊ ግንኙነት ውስጥ ያለውን የመለወጥ አቅም አጉልቶ አሳይቷል።

የጉባኤው የመክፈቻ መስዋዕተ ቅዳሴ
የጉባኤው የመክፈቻ መስዋዕተ ቅዳሴ

 

10 August 2024, 16:10