አቡነ አልቤርቶ ቬራ ፥ በሞዛምቢክ ምርጫ ዜጎች ሊረኩበት እንደሚገባ አሳሰቡ
በሞዛምቢክ ፕሬዝደንታዊ እና የህግ አውጭዎች የምርጫ ዘመቻዎች በከፍተና ደርጃ እየተካሄዱ ባሉበት በዚህ ወቅት የናካላ ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ አልቤርቶ ቬራ የአገሪቱ ፖለቲከኞች እና የምርጫ ቦርድ አካላት መጪው ምርጫ ሁሉን ያካተተ መሆኑን እንዲያረጋግጡ ጠይቀው፥ የሞዛምቢክ ምርጫ ዜጎች የሚረኩበት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
ብጹዕ አቡነ አልቤርቶ ቬራ ይህን የተናገሩት በቅርቡ በሀገረ ስብከታቸው ውስጥ ወደ አፍሪቃ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ መቅደስ በተደረገ መንፈሳዊ ንግደት ማጠቃለያ ላይ በሰጡት አስተያየታቸው ነው።
አቡነ አልቤርቶ ቬራ በመስከረም 29/2017 ዓ. ም. የሚጠናቀቀው የምርጫ ቅስቀሳ እና ሂደት በአገሪቱ ውስጥ የበዓል እና የደስታ ጊዜ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረው፥ ማንኛውም ሞዛምቢካዊ የአገሪቱ የሰላም አራማጅ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
ሞዛምቢካውያን ፕሬዚደንት ፊሊፔ ኒዩሲን ለሚተካው የምርጫ ውድድር ሲዘግጁ በውድድሩ የተስፋ ቃል ፉክክር ተባብሶ አንዳንዴም በጋሉ ቃላት ሊያልቅ እንደሚችል ተነግሯል።
በምርጫ ውድድሩ አቶ ዳንኤል ቻፖ ከገዢው ፍሬሊሞ ፓርቲ እጩ ሆነው ሲወዳደሩ ተቀናቃኛቸው አቶ ኦሱፎ ሞማዴ ደግሞ የዋናው ተቃዋሚ ሬናሞ ፓርቲ እጩ ሆነው እንደሚወዳደሩ ታውቋል።
ሉቴሮ ሲማንጎ የሞዛምቢክ ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴን ወክለው የሚወዳደሩ ሲሆን ቬንቺዮ ሞንድላን በግል የቀረቡ ፕሬዚዳንታዊ እጩ እንደሆኑ ተነግሯል።
16 September 2024, 17:25