ፈልግ

የሐዋሳ አገረ ስብከት ዕጩ ጳጳስ ክቡር አባ ጎበዛየው ጌታቸው ይልማ የሐዋሳ አገረ ስብከት ዕጩ ጳጳስ ክቡር አባ ጎበዛየው ጌታቸው ይልማ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ክቡር አባ ጎበዛየሁ ጌታቸውን የአዋሳ አገረስብከት ጳጳስ አድርገው ሾሙ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ክቡር አባ ጎበዛየው ጌታቸው ይልማን የሐዋሳ አገረ ስብከት ጳጳስ አድርገው በህዳር 6/2017 ዓ.ም መሾማቸው ተገልጿል። የሐዋሳ አገረ ስብከት ላለፉት 4 አመታት ያህል ያለ ጳጳስ በኢትዮጲያ የኮንቦኒ ማሕበር አባላት ካህናት ድጋፍ ሲተዳደር የነበረ አገረ ስብከት እንደሆነም ይታወቃል።

ግለ ታሪክ

ዕጩ ጳጳስ ክቡር አባ ጎበዛየው ጌታቸው ይልማ በኦሮሚያ ክልል ዶዶላ (ባሌ ዞን) በተባለ ቦታ እ.አ.አ በታኅሣሥ 4 ቀን 1978 ዓ.ም ተወለዱ። በጅማ የግብርና ዩኒቨርሲቲ የግብርና ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ሲሆን በመቀጠልም በአዲስ አበባ በሚገኘው ካፑቺን ፍራንችስካዊያን ኢንስቲትዩት የፍልስፍና እና ነገረ-መለኮት ትምህርት ተምረው አጠናቀዋል። ከሮማ ጳጳሳዊ ኡርባኒያና ዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና ዲፕሎማ እና በነገረ መለኮት የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል።

ዕጩ ጳጳስ ክቡር አባ ጎበዛየው ጌታቸው እ.አ.አ በጥር 16 ቀን 2005 ዓ.ም ማዕረገ ክህነት ተቀብለዋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኃላፊነት ቦታዎች በመያዝ ተጨማሪ ሐዋርያዊ እና ማሕበራዊ ተግባራትን አከናውነዋል። የመቂ ቫካሪየት ጸኃፊ እና የወጣቶች አስተባባሪ (እ.አ.አ 2004-2005)፣ ምክትል ዋና ጸሐፊ፣ ከዚያም የመቂ የካቶሊክ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ (እ.አ.አ 2006-2009)፥ በዲብሊን በሚገኘው የኪሜጅ ልማት ጥናት ማዕከል በልማት ጥናት የማስተሬት ድግሪ እና ከሜይኖዝ ቅዱስ ፓትሪክ ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ በሥነ መለኮት የዶክትሬት ዲግሪ (በካቶሊክ ማህበራዊ አስተምህሮ፥ እ.አ.አ 2009-2015)። ከፍተኛ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው እ.አ.አ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የመቂ አገረ ስብከት ጳጳስ ጸኃፊ እና በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚተዳደረው ካሪታስ (የመቂ ካቶሊካዊ ጽሕፈት ቤት) ሥራ አስኪያጅ ሆነው አገልግለዋል።

15 November 2024, 14:03