ፈልግ

ገዳማውያት በሰው ሰራሽ አስተውሎት አውደ ጥናት ላይ ገዳማውያት በሰው ሰራሽ አስተውሎት አውደ ጥናት ላይ  

የሕንድ ካቶሊክ ሚዲያ ዲጂታል አድማሱን ለማስፋት እንደሚፈልግ አስታወቀ

ዘንድሮ በሕንድ የተካሄደው ብሔራዊ የካቶሊክ ሚዲያ ጉባኤ በአገሪቱ የሚገኙ የካቶሊክ ሚዲያ ባለሞያዎችን በማስተባበር የኢየሱስ ክርስቶስን የምሥራች ለማወጅ እና የቤተ ክርስቲያኗን የዲጂታል ሚዲያ ለውጥን ለማገዝ መፈለጉ ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በሕንድ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከመላው ሕንድ የተወጣጡ የካቶሊክ መገናኛ ባለሞያዎችን በመሰብሰብ ታሪካዊ እርምጃ መውሰዷ ታውቋል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ በሁሉም የሕይወት መለኪያዎች ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ በመገንዘብ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያላትን አቅም በመጠቀም የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ይበልጥ በተገቢ መንገድ ለማወጅ መፈለጓ ታውቋል።

ብሐራዊ የካቶሊክ ሚዲያ ጉባኤ በሕንድ ባንጋሎር በሚገኘው የቅዱስ ጆን ሜዲካል ኮሌጅ ከኅዳር 14-15/2017 ዓ. ም. የተካሂደ ሲሆን፥ ጉባኤውን ካህናትን፣ ገዳማውያት እና ገዳማውያንን ጨምሮ 285 አባላት በንቃት መሳተፋቸው ታውቋል።

የጉባኤ መሪ ርዕሥም፥ “የዲጂታል ሚዲያ አገልግሎትን መንከባከብ” የሚል ሲሆን ዓላማውም ገዳማውያት እና ገዳማውያን ዲጂታል የመገናኛ መሣሪያዎችን በብቃት እንዲጠቀሙ፣ አገልግሎቶቻቸውን ለማሻሻል እና የቤተ ክርስቲያኗን ተልዕኮ ለማጠናከር እንደሆነ ታውቋል።

ዶ/ር ፓውሎ ሩፊኒ ከ 'SIGNIS' ፕሬዝዳንት አባ ቪክቶር ቪጃይ ሎቦ ጋር፣
ዶ/ር ፓውሎ ሩፊኒ ከ 'SIGNIS' ፕሬዝዳንት አባ ቪክቶር ቪጃይ ሎቦ ጋር፣

ጉባኤውን ያዘጋጁት በኅብረት የዶን ቦስኮ ማኅበራዊ መገናኛ፣ የደቡብ እስያ የሳሌዥያን ማኅበራዊ መገናኛ ተቋም (BOSCOM)፣ የቫቲካን የመገናኛ ጽሕፈት ቤት፣ በሕንድ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ የማኅበራዊ መገናኛ መምሪያ፣ የእስያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤዎች ፌዴሬሽን እና የሕንድ ካቶሊክ ገዳማት መሆናቸው ታውቋል።

በጉባኤው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከነበሩት መካከል የቫቲካን መገናኛዎች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ዶ/ር ፓውሎ ሩፊኒ እና በጽሕፈት ቤቱ የነገረ-መለኮት ሐዋርያዊ የመገናኛ አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ናታሻ ጎቬካር እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፥ የእነርሱ መገኘትም ቫቲካን ከሕንድ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጋር ያላትን የውይይት እና የትብብር ቁርጠኝነትን ለማጎልበት እንደምትፈልግ የሚገልጽ እንደሆነ ተነግሯል።

በጉባኤው የባንጋሎር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፒተር ማቻዶን፣ የማኅበራዊ መገናኛ አማካሪ አባ ጂልዳሲዮ ሳንቶስ እና በሕንድ የምዕራብ ባንጋሎር የፓርላማ አባል ሽሪ ዴሪክ ኦብሪየን መሳተፋቸው ታውቋል።

እያንዳንዳቸው በጉባኤው ወቅት በሰጡት አስተያየት እና የጋራ እይታ ዝግጅቱን ለማሳደግ የሚረዱ ልዩ ልዩ ገንቢ አመለካከቶችን አቅርበው፣ በሕንድ የምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተልዕኮዋን አጠናክራ እንድትቀጥል ለማድረግ ዶ/ር ፓውሎ ሩፊኒ እና ዶ/ር ጎቬካር ለሚያደርጉት ድጋፍ እና መመሪያ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የጉባኤው ተሳታፊዎች ዲጂታል የመገናኛ አገልግሎትን በምስጋና ተቀብለው የዲጂታል ዘመን ዕድሎች እና ፈተናዎች በእምነት፣ በፈጠራ እና በሃላፊነት እንዲዳስሷቸው በማሳሰብ ጉባኤው በይፋ የተጀመረ ሲሆን፥በትብብር እና ወደፊት የማለም አመራርን በፍጥነት በማሳደግ ላይ ላለው የዲጂታል ገጽታ አፅንዖት ሰጥቷል። 

ዶ/ር ጎቬከር በሕንድ የታሚል ቴሌቪዥ ጣቢያ ሃላፊ ከሆኑት ከአባ ዴቪድ አሮኪያም ጋር፣
ዶ/ር ጎቬከር በሕንድ የታሚል ቴሌቪዥ ጣቢያ ሃላፊ ከሆኑት ከአባ ዴቪድ አሮኪያም ጋር፣

እምነትን እና ቴክኖሎጂን ማገናኘት
ከተለያዩ የዲጂታል ሚዲያ መስኮች የተውጣጡ ባለሙያዎች በጉባኤው ላይ በቀረቡት የተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰቱ ሲሆን፥ ከእነዚህም መካከል የዲጂታል መልክዓ ምድርን መረዳት፣ ካኅናትን፣ ገዳማውያትን እና ገዳማውያንን የሚያጋጥሙ ዕድሎች እና ተግዳሮቶች፣ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አቀራረብ እና መመሪያዎች በዲጂታል አገልግሎታቸው፣ በዲጂታል ሚዲያ አገልግሎት ላይ ማሰላሰል እና የስነ-ምግባር ምርጫዎችን ማሳደግ፣ ማኅበራዊ ሚዲያ እና የምንኩስና ሕይወት ተልዕኮ፣ የዲጂታል ሚዲያ ደኅንነት እና የመቋቋም ችሎታ፣ የዲጂታል ሚዲያ አገልግሎት እና አገልግሎቱን ለሌሎች ማድረስ የሚሉት ይገኙበታል።

ዶ/ር ሩፊኒ እና ዶ/ር ጎቬካር ከባንጋሎር ሊቀ ጳጳስ ፒተር ማቻዶ እና ሌሎች እንግዶች ጋር
ዶ/ር ሩፊኒ እና ዶ/ር ጎቬካር ከባንጋሎር ሊቀ ጳጳስ ፒተር ማቻዶ እና ሌሎች እንግዶች ጋር

እነዚህ ውይይቶች ተሳታፊዎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂን እና ግብዓቶችን በመጠቀም እንዴት ውጤታማ በሆነ መንገድ ወንጌልን ለሌሎች መመስከር እንዲችሉ ጠቃሚ እውቀትን ከመስጠቱ በተጨማሪ የማኅበራዊ ሚዲያ ቻናሎችን በመጠቀም የእግዚአብሔርን ቃል ለማሰራጨት እና ሕይወት ለማሻሻል ብዙ ዕድሎችን የሰጠ እንደነበረም ተመልክቷል።

ዶ/ር ፓውሎ ሩፊኒ ለጉባኤው ንግግር ሲያደርጉ
ዶ/ር ፓውሎ ሩፊኒ ለጉባኤው ንግግር ሲያደርጉ

ጉባኤው ከዚህም በላይ ተሳታፊዎቹ እውነቱን በትክክለኛነት እንዲናገሩ እና ዲጂታል ማስተዋልን እንዲያሳድጉ በማሳሰብ ጥሩ ተናጋሪ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲመስሉ መጠራታቸውንም አሳስቧል።

 

27 November 2024, 16:37