ፈልግ

2023.08.08 Incontro vocazionale del Cammino neocatecumenale dopo Gmg di Lisbona 07-08-2023

ክርስቶስ ሕያው ነው! ተስፋችን ነው

የእግዚአብሔር ቃል ስለ ወጣቶች ምን ይላል?

አዘውትረው ስለ ወጣቶች እና እግዚአብሔርም እንዴት ቀርቦአቸው እንዳነጋገራቸው ስለሚናገሩ" እስቲ ወደ ተቀደሱ የእግዚአብሔር ቃላት እንመልከት”በብሉይ ኪዳን ወጣቱ ሕዝብ ብዙም ትኩረት በማያገኝበት በዚያን ዘመን" አንዳንድ የንባብ ክፍሎች እግዚአብሔር እንዴት በልዩ ሁኔታ ይመለከታቸው እንደነበር ያሳያሉ”ለምሳሌ ያህል" ዮሴፍ" ለቤተሰቡ የመጨረሻ ልጅ (ዘፍ. 37: 2 -3) የነበረ ቢሆንም እግዚአብሔር ግን በሕልም እጅግ ታላቅ የሆኑ ጉዳዮችን ያሳየው ነበር; ወደ ሃያ ዓመት እድሜ ላይ በደረሰ ግዜም ዋና ዋና በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከታላላቅ ወንድሞቹ መላቅ ጀመረ”(ዘፍ 37- 47)።

በጌድዮን" በማር የተለወሰ ሬት የማይቀርብበት ነባራዊ ሁኔታ" በወጣቶች ዘንድ ያለውን ግልጽነት እንመለከታለን”እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደሆነ ሲነገረው" እንዲህ ሲል ነበር የመለሰው" “ጌታ ሆይ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ሁሉ እንዴት ሊደርስብን ቻለ?”(መሳ 6:13) ይህ ጥያቄ ግን እግዚአብሔርን አላስከፋውም" እንዲያውም ትዕዛዘዙን እንዲቀጥል ነው ያደረገው" “ሂድ" ባለህ ኃይል እስራኤላውያንን ከምድማውያን እጅ ነጻ እንድታወጣ” (መሳ 6:14) ሳሙኤል ገና ወጣት ልጅ ነበር" ዳሩ ግን ጌታ ተናገረው”ለዐዋቂ ምክር ምስጋና ይግባውና" ለእግዚአብሔር ጥሪ ለመስማት ልቡን ከፈተ" “ባሪያህ ይሰማልና ተናገር አለ$”(1 ሳሙ 9-10 )”በውጤቱም" ወሳኝ በሆኑ ጊዜያት ሁሉ በአገሩ ታሪክ ውስጥ ጣልቃ የሚገባ ታላቅ ነቢይ ለመሆን በቃ”ንጉሥ ሳኦልም ተልእኮውን ሲቀበል ወጣት ልጅ ነበር (1 ሳሙ 9:2)።

ንጉሥ ዳዊት የተመረጠው ገና በለጋነት እድሜው ነበር”ነቢዩ ሳሙኤል ወደፊት እስራኤልን የሚያወጣና የሚያስገባ ንጉሥ እየፈለገ ባለበት" አንድ ሰው ትልልቆቹንና ልምድ ያለቸውን ልጆቹን በእጩነት አቀረበ”ዳሩ ግን ነቢዩ የተመረጡት እነርሱ ሳይሆኑ በእረኝነት ስራ ላይ የተሰማራው ትንሹ ዳዊት እንደሆነ ተናገረ (1 ሳሙ 16: 6 - 13) ምክንያቱም “ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” (1 ሳሙኤል 16፡7) በሌሎች ላይ ከሚያሳድረው ግምት እና ከአካላዊ ጥንካሬ ይበልጥ የወጣት ክብር ያለው በልቡ ውስጥ ነው”።

ሰሎሞን በአባቱ እግር በተተካ ግዜ" ግራ በመጋቱ ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረ" “እኔ ግን ገና ትንሽ ልጅ ስለ ሆንሁ መውጫና መግቢያዬን አላውቅም ” ( 1ኛ ነገ 3: 7) ሆኖም ደግሞ የወጣትነት ድፍረቱ ከእግዚአብሔር ጥበብና ማስተዋልን እንዲጠይቅና ራሱንም ለተልእኮው እንዲሰጥ አደረገው”ነቢዩ ኤርምያስም ተመሳሳይ ሁኔታ ገጥሞታል የተጠራው ምንም እንኳን ወጣት ልጅ ቢሆንም ሕዝቡን ግን ማስነሣት ነበረበት”በፍርሃትም ውስጥ ሆኖ እንዲህ አለ" “እኔም ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እንዴት እንደምናገር አላውቅም ገና ሕጻን ልጅ ነኝና አልሁ” (ኤር 1:6) እግዚአብሔር ግን እንደዚያ እንዳይል ተናገረው (ኤር 1:7)እንዲህም አከለበት" “እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራቸው” (ኤር 1:8) ነቢዩ ኤርምያስ ለተልዕኮው የነበረው ታማኝነት" የወጣትነት ድፍረት ከእግዚአብሔር ኃይል ጋር ሲጣመር ምን እንደሚሆን የሚያሳይ ነው”።

የውጭ አገር ሰው የነበረው የአዛዡ ንዕማን አገልጋይ የነበረችው አይሁዳዊ ልጃገረድ" በእምነቷ" ከነበረበት የጤና ችግር እንዲፈወስ ረድታዋለች”(2 ነገሥ 5: 2-6) ሌላዋ ደግሞ" አማቷን ነገር በከፋ ሰዐት ባለመተዋ" ወጣቷ ሩት የልግሥና ተምሳሌት ነበረች”(ሩት 1: 1-18) በሕይወት ወደ ፊት ለመቀጠልም ድፍረትን አሳይታለች”(ሩት 4:1-17)።

ምንጭ፡ ክርስቶስ ሕያው ነው በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለወጣቶች እና ለጠቅላላው የእግዚአብሔር ሕዝብ ከጻፉት ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ምክር ከአንቀጽ 5-11 ላይ የተወሰደ።

20 December 2024, 14:54