ፈልግ

2021.11.26 Il Presepe nell'arte - libro di Rosa Giorigi 2021.11.26 Il Presepe nell'arte - libro di Rosa Giorigi 

የዶምኒካኑ ብጹእ ካርዲናል ቲሞቲ ራድክሊፍ ‘ጠላቶቻችንን እንደ ወንድም እና እህት እንመልከት’ አሉ

በፍርሃት እና በጥርጣሬ ጥላ በጨለመው ዓለም ውስጥ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ በጣም ትልቅ የተስፋ ምልክት እና መልዕክት ነው የተባለ ሲሆን፥ ለዘንድሮው የብርሃነ ልደቱ በዓል እና ‘የተስፋ ነጋዲያን’ በሚል ርዕስ ለሚከበረው የኢዮቤልዩ ዓመት ማስጀመሪያ ላይ የቫቲካን ረዲዮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪዎች “በጦርነት በተመሰቃቀለው ዓለም ውስጥ ያለው የክርስቶስ ሰላም” በሚል መሪ ቃል አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ደረጃ መልዕክታቸውን የላኩት የዶሚኒካኑ ብጹእ ካርዲናል ቲሞቲ ራድክሊፍ ሲሆኑ፥ ብፁዕነታቸው ብርሃነ ልደቱን አስመልክተው በላኩት መልዕክት፥ 'እኔ ከተወለድኩበት የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ወቅት ወዲህ ዓለማችን ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ በዓመፅ እየተናጠች ነው' ብለዋል።

ይህ ቁጣ አብዛኛውን ጊዜ የሚነሳው በብሔሮች መካከል ከሚነሳ ግጭት ሲሆን ነገር ግን አንዳንዴ በማህበረሰቦች መካከል በሚነሳ አለመግባባቶችም ሊከሰት ይችላል።

ማህበራዊ ሚዲያው ቁጣን ይበልጥ ያነሳሳል። ይህ ቁጣ ደግሞ አንባቢዎችን ይስባል፥ ብዙ ገንዘብም ያስገኛል። ቤተ ክርስቲያኑ እንኳን ሳይቀር በአመጽ ክስ ተሞልታለች።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደገው በዓመፅ በተበታተነች አገር ነው። በልጅነቱ የ2000 የአይሁድ አማጽያን በወራሪ ሮማውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተሰቅለው ሲገደሉ አይቶ ነበር፥ ነገር ግን እሱ የቀኝ ጉንጫችንን ሲመቱን የግራውን በድጋሚ እንድንሰጥ ያስተማረን ግፍ የሌለበት ሰው ነበር።

ከእሱ መማር የምንችለው እንዴት ነው?

ዓመፅ ከፍርሃት ይመነጫል፣ ይሄ ደግሞ ሌላውን ሰው ልክ እንደ እኛ የመውደድ እና የመጎዳት ችሎታ እንዳለው እንደ አንድ ደካማ የሰው ልጅ እንዳናይ ያደርጋል።

እኛ ግን መፍራት የለብንም፥ ምክንያቱም በትንሳኤው ቀን ፍቅር ድል አድርጓል፣ ጥላቻም ተሸንፏል። ቁጣን በቁጣ ምላሽ ከሚሰጡ ሰዎች ባርነት ነፃ እንውጣ። የአመፃ ድርጊት በተቀደሰው አርብ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደቆመ ሁሉ፣ በእኔ ዘንድም ዬለም ለማለት ነፃነቱ ይኑረን።

እንደገና ለመጀመር የክርስቲያን ነፃነታችንን መጠየቅ አለብን። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የታመሙትን፣ የሴተኛ አዳሪዎችን፣ የጠላቶቹን እና የሮማውያን ወራሪዎችን ስውር ክብርና መልካምነት አይቷል።

"እንደ ጠላት የምናስባቸውን ለማየት ዓይኖቻችንን እንክፈት፥ እንዲህ ካደረግን በእግዚአብሔር መልክና አምሳል የተሠሩ ወንድሞችና እህቶችን እናያለን” በማለት ብጹዕ ካርዲናል ቲሞቲ ራድክሊፍ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
 

24 December 2024, 13:06