ፈልግ

ሲስተር ጆይሲ ጆይ ለተለያዩ ጎሳዎች ሰብአዊ መብትን አስመልክቶ ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮችን ሲተገብሩ ሲስተር ጆይሲ ጆይ ለተለያዩ ጎሳዎች ሰብአዊ መብትን አስመልክቶ ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮችን ሲተገብሩ  

የህግ ባለሙያ የሆኑት መነኩሴ በህንድ ሃገር በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ እየሰሩ መሆኑ ተገለጸ

የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ቀንን አስመልክቶ በወጣው መረጃ መሰረት በህንድ ሃገር ለሚገኙ የተለያዩ የጎሳ አባላት እና ለተገለሉ ወገኖች ጠበቃ በመሆን ህጋዊ ድጋፍ የሚሰጡት መነኩሴ እና የህግ ባለሙያ የሆኑት ሲስተር ጆይሲ በርካታ ሥራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

እ.አ.አ. ከ1948 ዓ.ም ጀምሮ ታኅሣሥ 10 በዓለም አቀፍ ደረጃ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀን ተብሎ በየዓመቱ ይከበራል።

ባለፈው ዓመት በተከበረው የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ቀን ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በመልአከ እግዚያብሄር ጸሎት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ሁሉም ሰው ‘በጥበብ እና በትዕግስት በሰላም አብሮ ለመኖር ያለመታከት ጠንክረው የሚሰሩትን ወንዶች እና ሴቶችን ተምሳሌትነት እንዲከተሉ’ በመጋበዝ፥ “ለሰብአዊ መብት መከበር ያለው ቁርጠኝነት መቼም ቢሆን አያልቅም!” ማለታቸው የሚታወስ ነው።

ሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር ወስነው ሥራ ከጀመሩ ገዳማዊያት መካከል ሲስተር ጆይሲ ጆይ አንዷ ሲሆኑ፥ ሲስተር ጆይሲ በሙያቸው የህግ ባለሙያ እንደሆኑ እና በህንድ ኬራላ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ዋይያናድ ወረዳ የተለያዩ ጎሳ ያላቸው የአከባቢው ህዝቦች ውስጥ የሚገኙ ሴቶች፣ ህጻናት እና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸው ገበሬዎችን ህይወት፣ ክብር፣ ነፃነት እና ሰብአዊ መብቶችን ለማስጠበቅ ቆርጠው እየሰሩ ይገኛሉ።

የህግ አገልግሎት
የሲስተር ጆይሲ የህግ ተሟጋችነት አገልግሎት የጀመረው የፓኒያ ጎሳ ማህበረሰብ አባል የሆነች ሴት ድንገተኛ ሞት ተከትሎ የተጠየቀ ካሳ ክፍያን በሚመለከት ፈታኝ ጉዳይ የጀመረ ሲሆን፥ ቤተሰቡ ሲስተሯ ባደረጉት ከፍተኛ የጥብቅና ጥረት ምክንያት አሸናፊ በመሆናቸው ከመንግስት ከፍተኛ ካሳ በማግኘት ጥረታቸው ተሳክቷል። ጉዳዩን በማስታወስ እንደተናገሩትም ይህ ስኬት የህግ ተሟጋችነት አንድን ሰው የመቀየር ኃይል ላይ ያላቸውን እምነት ያጠናከረ መሆኑን ለቫቲካን ዜና ተናግረዋል።

ሲስተር ጆይሲ በኬራላ ግዛት መንግስት የሴቶች እና ህፃናት መምሪያ የህግ አማካሪ አድርጎ ሲሾማቸው በፊት የነበራቸው ሚና የበለጠ እንደሰፋ በመግለጽ፥ ይህ ቦታ በቤት ውስጥ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመፍታት፣ ነፃ የህግ ውክልና እና ለተጎጂዎች የስነ-ልቦና ድጋፍ ለመስጠት እንዳስቻላችው ጠቁመዋል።

መነኩሴዋ በአምስት ፓንቻይቶች (አካባቢያዊ አስተዳደሮች) ላይ ስልጣን ስላላቸው በህግ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ ለመግባት የበለጠ ስልጣን እንዳገኙም ጭምር ገልጸዋል።

ቤተክርስቲያኗ ለሲኖዶሳዊነት ሥራ ባቀረበችው ጥሪ መሰረት ጥሪውን ተቀብለው በመሰጠት ከሚሰሩ በጎ ፈቃደኛ የምዕመን ቡድን ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ገልጸዋል።

በዚህም አንፃር በጋራ በመሆን ሁለቱንም ህጋዊ እና ስሜታዊ ተግዳሮቶችን በመፍታት በወረዳው ውስጥ የሚገኙ የተገለሉ ማህበረሰቦችን እያገለገሉ ይገኛሉ።

የጥብቅና ዓመት
ባለፈው ዓመት ሲስተር ጆይሲ 105 የሚሆኑ የቤት ውስጥ ጥቃት ጉዳዮችን፣ 30 የቤተሰብ ጉዳዮችን፣ 17 የመሬት ይዞታ ጉዳዮችን በተመለከተ፣ እንዲሁም በ117 የምክክር ክፍለ ጊዜዎች በንቃት እንደተሳተፉ ገልጸዋል።

የናዝሬት በጎ አድራጎት ገዳማዊያት አባል የሆኑት ሲስተር ጆይሲ ባላቸው ቁርጠኝነት እና እምነት፥ የበለጠ ፍትሃዊ የሆነ ማህበረሰብ ለመፍጠር በጥሪያቸው የሚኖሩ ግንባር ቀደ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሆነው ቆመዋል።
 

11 December 2024, 14:31