ፈልግ

Cookie Policy
The portal Vatican News uses technical or similar cookies to make navigation easier and guarantee the use of the services. Furthermore, technical and analysis cookies from third parties may be used. If you want to know more click here. By closing this banner you consent to the use of cookies.
I AGREE
Requiem in Re minore, per coro maschile e orchestra
መርዐ-ግብር በድምጽ የቀረበ ዘገባ
የጋዛ ግጭት ያስከተለው ውድመት የጋዛ ግጭት ያስከተለው ውድመት   (AFP or licensors)

አባ ፋልታስ፡- በጋዛ የሚገኙ ሕጻናት ‘የተከበረ የሰላም ስጦታ’ ይገባቸዋል ማለታቸው ተገለጸ!

የጋዛ ጦርነት እንደገና ሲቀጥል የቅድስት ሀገር ተንከባካቢ ቄሰ ገበዝ የሆኑት አባ ኢብራሂም ፋልታስ በቅድስት ሀገር ህጻናት ላይ የደረሰውን የስቃይ ጦርነት ሲገልጹ የዜጎችን በተለይም የህጻናትን መብት ለማስጠበቅ አዲስ ጥረት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በጋዛ እንደገና የጀመረው ጦርነት በአሳዛኝ ሁኔታ የሚገደሉት ሕፃናት ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። የቅድስት ሀገር ተንከባካቢ ቄሰ ገበዝ የሆኑት አባ ኢብራሂም ፋልታስ ኦዞርቫቶሬ ሮማኖ ከተሰኘው ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በጋዛ ቤተሰቦች ላይ ያለውን ጠባሳ እና ቤተክርስቲያን በተቻለ መጠን የጋዛን ልጆች ለመደገፍ እና ለማስጠለል የምታደርገውን ጥረት አብራርተዋል።

ጥያቄ፡- አባ ኢብራሂም ይህን ያህል ከፍተኛ መጠን ያለው የህጻናት ጉዳት የደረሰበት ሌላ ጦርነት የለም። ለምን እንደሆነ እንድንረዳ ሊረዱን ይችላሉ?

እኔ አምናለሁ በአብዛኛው በጋዛ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች በተለምዶ ብዙ ልጆች ያላቸው እና ህዝቡ በጣም ወጣት ስለሆነ ነው። ምንም እንኳን ትክክለኛዎቹን ምክንያቶች በትክክል መለየት አስቸጋሪ ቢሆንም፣ በጋዛ የሚኖሩ ልጆችን በሞት ያጡ ወላጆችን እና ብዙውን ጊዜ ከአንድ በላይ የሆኑ ወላጆችን ሥቃይ ጠንቅቄ አውቃለሁ። ንፁሀን ህጻናትን እና ነቀፋ የሌላቸው ሕጻናት ላይ ጉዳት ማድረስ የሰው ልጅ ከታሪኩ ሊጠፋው የማይችል እድፍ ነው።

በጋዛ የተገደሉት ሕፃናት ቁጥር በጣም አስፈሪ ነው፣ እናም ብዙዎቹ በሕይወት የተረፉ ሰዎች - በአካላቸው፣ በልባቸው እና በአእምሮአቸው - በቀሪው ሕይወታቸው የሚሸከሙትን ጠባሳ ማሰብ በጣም አሳዛኝ ነው። መገናኛ ብዙሃን በሰሜን ጋዛ ሰርጥ እያሻቀበ ስላለው ሁከት እና ሞት፣ የአካል ጉዳት እና እስራት እነዚህ ጉዳዮች እየጨመሩ ባሉበት ሁኔታ ላይ ያነሰ ዘገባ ይዘግባሉ። እዚያም ብዙ ተጎጂዎች ህጻናት ናቸው።

ጥያቄ፡- የፍልስጤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አኃዝ በጣም አስገራሚ ነው፡ ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ 15,613 ሕጻናት ተገድለዋል፣ 33,900 ቆስለዋል ይላል። ከሟቾቹ መካከል 876 አዲስ የተወለዱ እና 4,110 ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህጻናት ይገኙበታል። ወላጅ አልባ በሆኑ ልጆች ቁጥር ላይ ምንም መረጃ የለም። በእዚህ ላይ ምንም አይነት መረጃ አሎት? ስንት ልጆች ወላጆቻቸውን አጥተዋል ተብሎ ይታመናል? ማን ነው የሚንከባከባቸው?

በግምት ወደ 20,000 የሚጠጉ ህጻናት ወላጅ አልባ ሆነዋል። በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ ቁጥር ሊያድግ ይችላል። ምክንያቱም ምን ያህል አስከሬኖች በፍርስራሹ ውስጥ ተቀብረው እንዳሉ ስለማናውቅ ነው። በብዙ አጋጣሚዎች ትልልቅ ልጆች የአዋቂን ኃላፊነት በመያዝ ታናናሽ ወንድሞቻቸውን እና እህቶቻቸውን እየተንከባከቡ እንደሆነ ተነግሮኛል።

የዚህ ጦርነት አንዱ ታላቅ አሳዛኝ ነገር እኛ መርዳት አለመቻላችን ነው፡ የሰብአዊ እርዳታ ሊያልፍ አይችልም፣ እና ጥቂት በጎ ፈቃደኞች ብቻ ወደ ጋዛ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው - ይህም የሆነው በቅርቡ ብቻ። በጣም ቅርብ ጊዜ፣ ግን አቅም የለሽ መሆን በጣም ከባድ ነገር ነው።

ጥያቄ፡- ባለፈው የፀደይ ወቅት ከ200 በላይ የቆሰሉ ወይም የታመሙ የጋዛ ህጻናት በጣሊያን ሆስፒታሎች እንዲታከሙ ለማድረግ ከጣሊያን መንግስት ጋር እርሶ ተባብረው ሰርተዋል። በግብፅ በኩል ሕጻናቱን ለማውጣት ተችሏል። ተመሳሳይ ጥረቶች እንደገና ሊከሰቱ ይችላሉ ብለው ያስባሉ?

እ.አ.አ ከጥር 2024 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ፣ ከ200 በላይ ህጻናት በጣሊያን ሆስፒታሎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ እንኳን ለጊዜያዊ የተኩስ አቁም ምስጋና ይግባውና ከጋዛ ብዙ ህጻናት በግብፅ በኩል ወጥተው ጣሊያን እንዲገቡ ተደርጓል።

እ.አ.አ. በሕዳር 2023 ዓ.ም ከቅዱስ አባታችን ጋር ከተገናኘን በኋላ፣ ጓደኞቻችንን በባምቢኖ ጄዙ ሆስፒታል ጎበኘሁ። የእነሱ ልግስና - በመጀመሪያ እንደ ወላጅ ከዚያም እንደ ዶክተሮች እና አስተዳዳሪዎች - እነዚህን ትናንሽ ልጆች ለመርዳት በር ከፍቷል። የጣልያን መንግስት ይህን ለማድረግ የሚቻለውን ሁሉ ዲፕሎማሲያዊ ጥርት እንዲሰራ አድርጓል። የጣልያን ህዝብ ላሳዩት ልግስና ማመስገን መቼም አላቆምም።

ሌሎች የአውሮፓ አገሮችም የታመሙ ሕፃናትን ከጋዛ እንደወሰዱ አውቃለሁ፣ እናም ብዙ እንደሚከተል ተስፋ አደርጋለሁ። ህክምና የሚያስፈልጋቸው ህጻናት ዝርዝር በጣም ረጅም ነው፣ ነገር ግን እነሱን ማውጣት ቀላል አይደለም። እርቅ - ወይም የተሻለ ፣ ጦርነቱ ማቆም - ቀድሞውኑ በጣም የተጎዱትን ሕፃናትን ሕይወት ሊያድን ይችላል።

ጥያቄ፡ ከእነዚህ አብዛኞቹን ልጆች በግል ረድተዋል። ከእርስዎ ጋር የቆዩ ልዩ ታሪኮች አሎት ወይ? ማጋራት የሚፈልጉት በተለይ አነቃቂ ጉዳዮች አሉ?

ከጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ ጋር በመሆን አብዛኞቹን ልጆች ጣሊያን ሲደርሱ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን ነበረ። በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ እየጠበቅናቸው ሳለ ስለልጆቹ ተነጋግረን ነበር፣ ነገር ግን አንድ ጊዜ ታሪካቸውን ከወላጆች እና አሳዳጊዎች ስንሰማ፣ ዝም ብለን ቀረን።

በኋላ፣ በሆስፒታሎች ውስጥ ጎበኘኋቸው እና ማገገማቸውን ተከታትያለሁ። አንድ ልጅ አገኘሁ፣ በከባድ እግሩ ላይ ቆስሏል - ውስብስብ ቀዶ ጥገና ከተደረገለት በኋላ እንደገና ሲራመድ አየሁት። በካንሰር በሽታ ተጠቅታ የምትሰቃይ አንዲት ወጣት አሁን በጣም በተሻለ ሁኔታ ላይ ትገኛለች፤ ምንም እንኳን እዚያ ስትደርስ ዶክተሮች በአስጊ ሁኔታ ላይ እንዳለች አስጠንቅቀውኝ የነበረ ቢሆንም።

በጣሊያን እነዚህ ልጆች ሁለቱንም ማለትም የሕክምና እንክብካቤ እና ፍቅር አግኝተዋል። አንዳንዶች ጣልያንኛ ቋንቋ እየተናገሩ ነው። ሲጠሩኝ በመጨረሻ በድምፃቸው ሰላም ይሰማኛል - እግዚአብሔር ይመስገን።

ጥያቄ፡- ባለፉት አመታት በጣሊያን በተለይም በሳን ማሪኖ እና ኡምብሪያ አካባቢ ወላጆቻቸውን ያጡ ወይም የተጣሉ የፍልስጤም ልጆችን ለመውሰድ የተደረገውን ትልቅ ተነሳሽነት መርተዋል። ከእነዚህ ልጆች መካከል አንዳንዶቹ አሁን ያደጉ ወንዶችና ሴቶች ናቸው። የምያስታውሷቸው ልጆች አሉ ወይ? ለጋዛ ልጆች ተመሳሳይ ተነሳሽነት ሊጀመር ይችላል? በጣሊያን ውስጥ ምንም አይነት ውይይት ጀምረዋል?

በቅርብ ጊዜ በሳን ማሪኖ ውስጥ የ "ፈገግታ ፕሮጀክት" ተነሳሽነት የተጀመረበትን 25 ኛ አመት አከበርን። በወቅቱ የኢየሩሳሌም ሐዋርያዊ ልዑክ በነበሩት ሊቀ ጳጳስ ፒዬትሮ ሳምቢ በጥብቅ የሚፈለጉት ፕሮጀክት ነበር፤ ይህን በማስታሻ ደብተሬ የምይዝ ጉዳይ ነው።

እ.ኤ.አ. በ2000ዎቹ መጀመሪያ ላይ በቅድስት ሀገር ከባድ ግጭት ለዓመታት ተከስቶ ነበር ፣ እና አብረን እውነተኛ የአብሮነት ድልድይ መገንባት ቻልን-ከቤተልሔም ብዙ ልጆች በሳን ማሪኖ ውስጥ በጉዲፈቻ ተወሰዱ። በአመታት ውስጥ ብዙ ጊዜ አግኝቻቸው ነበር-ደስተኞች እና በጣም የተወደዱ ናቸው።

ዓለም አቀፍ ጉዲፈቻ በጣሊያንም በጣም አስቸጋሪ ሆኗል። ነገር ግን ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችን በፍቅር ቤተሰቦች ውስጥ የማኖር አስፈላጊነት - የወደፊት ጊዜያቸውን ሊሰጡ የሚችሉ ቤተሰቦች - ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ነው። ወላጅ የሌላቸው ልጆችን ለመቀበል ዝግጁ ከሆኑ ሰዎች ጋር ለማገናኘት እና ቆንጆ ቤተሰቦችን ለመመስረት ብችል እመኛለሁ ፣ ሁል ጊዜም በሕግ እና ከልጆች ጥበቃ ጋር ሙሉ በሙሉ በተያያዘ መልኩ። እስካሁን ድረስ ይህ ሊሆን አልቻለም። እኛ ግን ተስፋ እናደርጋለን እንጸልያለን።

ጥያቄ፡- ስለ ልጆች ለመነጋገር ብዙ ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር ተገናኝተው ነበር። በጉዳዩ ላይ ምን ነገሮዎት?

ቅዱስ አባታችንን ለመጨረሻ ጊዜ ያገኘኋቸው እ.አ.አ የካቲት 3 ቀን በጂሚሊ ሆስፒታል ከመተኛታቸው አስር ቀናት ቀደም ብሎ ነበር። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “እንውደዳቸው እና እንጠብቃቸው” በሚል መሪ ቃል ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ መሪዎችን እና ተቋማትን በመሰብሰብ በልጆች ላይ የመሪዎች ስብሰባ ጠርተው ነበር። ከጉባዔው በኋላም ከጦርነት ቀጠና ወደ ጣሊያን ከመጡ ሕፃናት ጋር በግል ተገናኙ።

የጋዛ ልጆች በደግ አይኖች የሚመለከቷቸውን አፍቃሪ አያት እንዳገኙ ነገሩኝ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩባቸው አሥራ ሁለት ዓመታት፣ ከእርሳቸው ጋር ለመነጋገር ብዙ እድሎችን አግኝቻለሁ፣ እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነዚያ ጊዜያት በጣም ተደጋጋሚ ሆነዋል። ሁል ጊዜ ስለ ቅድስት ሀገር ሁኔታ - ሰዎች እንዴት እንደሚኖሩ፣ በተለይም ልጆቹን ይጠይቃሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለመጪው ትውልድ በጥልቅ ያስባሉ። ህጻናትን የመንከባከብ እና የመጠበቅ ራዕዩ በሚሰራው ነገር ሁሉ ይመጣል፡ እርሳቸው አባት ናቸው-ንቁ፣ ፍትሃዊ እና አዛኝ ናቸው። በተለይ በትምህርታቸው እና ሰላምን በማስፈን ረገድ ለህፃናት በምሰራው ስራ ሁሌም ያበረታታኝ ነበር።

ጥያቄ፡- ጦርነቱ ካገረሸበት ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ የተገደሉት ህጻናት ቁጥር ጨምሯል -በመጀመሪያው ምሽት ብቻ 130 ህጻናት። ከጋዛ ምን ዜና እየተቀበሉ ነው?

በሚያሳዝን ሁኔታ ቁጥሩ ቀድሞውኑ ጨምሯል እና ብጥብጡ ካልቆመ እየጨመረ ይሄዳል። ከጋዛ የማገኘው ዜና በጣም አሳሳቢ ነው። ጦርነቱ እንደገና መቀስቀሱ ​​ድንገተኛ እና በጣም ኃይለኛ ነበር።

ይህ በቅድስት ሀገር ውስጥ የተቀደሰ ጊዜ ነው፡ ለሙስሊሞች ረመዳን እና ለክርስቲያኖች ጾም ነው። እነዚህ ጊዜያት ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ አንዳቸው የሌላውን ሥርዓት፣ ሥርዓተ አምልኮ እና ወጎች የሚያከብሩበት ጊዜ ነው።

በተለይ በዚህ ሰሞን ይህን ያህል ሞትና ውድመት መስማት በጣም ያሳዝናል። የንጹሃን ሰዎች ሞት ሁል ጊዜ በጣም ያማል።

ጥያቄ፡- እዚህ አውሮፓ ውስጥ እነዚህ ልጆች እየደረሰባቸው ላለው ችግር ጥልቅ ርህራሄ አለ። እርስዎ እና ሌሎች በፍልስጤም ውስጥ እየሰሩት ያለውን ጠቃሚ ስራ ለመደገፍ ምን እናድርግ?

በአለም ዙሪያ ሰዎች ለልጆች ርህራሄ እና ሐዘኔታ ይሰማቸዋል። መብቶቻቸውን፣ የወደፊት እጣ ፈንታቸውን፣ አስፈላጊ ፍላጎቶቻቸውን የመጠበቅ ሃላፊነት ይገነዘባሉ። በጣም የሚያስደነግጠው ግን ይህ ስሜት ለእነዚህ ልጆች ብዙ ስቃይ እና ሞት በሚያስከትሉ ሰዎች ላይ ሙሉ በሙሉ የማይታይ መስሎ ይታያል።

ከ800 ለሚበልጡ ዓመታት ቅዱሳን ቦታዎችን እና የሚኖሩባቸውን ሕያዋን ድንጋዮች ሲጠብቅ የቆየው የቅድስት ሀገር የጥበቃ ቄሰ ጎበዝ እንደመሆናችን መጠን ሥራ፣ ትምህርት፣ መኖሪያ ቤት እና ድጋፍ በተለያዩ መንገዶች እንሰጣለን ማለት እችላለሁ። በቅርብ ዓመታት፣ በጦርነት፣ በመካሄድ ላይ ባሉ ውጥረቶች እና በወረርሽኙ የተነሳ የበለጠ ተግዳሮቶች አጋጥመውናል። ጥረታችን የሚቆየው በመንፈሳዊ ጸጋ እና በጎ አድራጊዎች ልግስና ነው፣ ልጆቹን እና ቅድስት ሀገርን ለማገልገል የሚረዱንን ሁሉ ማለቴ ነው።

የዘንድሮው የስቅለተ አርብ ምጽዋዕት ስብስብ ለቅድስት ሀገር ካለፉት ጊዜያት የበለጠ ለጋስ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ከሁሉም በላይ፣ በሁሉም ሰዎች ጸሎት ላይ እንመካለን—ይህም ውድ የሆነው የሰላም ስጦታ በቅርቡ በሁሉም ቦታ ልጆች እንዲደርስ ያደርጋል። የቤተልሔም ቅዱስ ልጅ ይጠብቃቸው፣ ያበርታቸው፣ ፈገግታቸውንም ይጠብቅላቸው።

 

27 Mar 2025, 15:12
Prev
April 2025
SuMoTuWeThFrSa
  12345
6789101112
13141516171819
20212223242526
27282930   
Next
May 2025
SuMoTuWeThFrSa
    123
45678910
11121314151617
18192021222324
25262728293031