ኒቆዲሞስ ከኢየሱስ ጋር በመገናኘቱ ተስፋውን መልሶ አገኘ
ሀ/ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው ማለት ምድራዊ ጊዜያዊ ሰው ነው። ሥጋዊ ሰው በሥጋ መንገድ ይሄዳል፣ ሥጋዊ ነገር ያስባል፣ ይፈልጋልም ስለ ሥጋው ይኖራል፣ ይሠራልም “ሥጋቸውን የሚያገለግሉ ዓለማዊ ናቸው" (ሮሜ 8፣5) ይለናል ቅዱስ ጳውሎስ። ሥጋዊ ሰው የዓለም ልጅ በመሆኑ የዓለምን መንፈስ ይከተላል፤ የእግዚአብሔር ፍርሃትና የነፍሱ ደኀንነት ሐሳብ የለውም፣ የመንፈስ ነገር አይባውም፣ ይህ ለእርሱ ሞኝነት ነው" ይላል (1ኛ ቆሮ. 2፣14)።
ለ/ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው፥ ሰማያዊና ዘለዓለማዊ መልአክ የእግዚብሔር ልጅ ነው፣ ይህ ሰው በእግዚአብሔር መንፈስ ስለሚመራ ሰማያዊ ነገርን ይመኛል። አእምሮው ልቡ ፍላጐቱ ወደ አምላክ ያዘነብላል። ከመንፈስ የተወለደ ሰው ስለ አምላክ ክብርና ደኀንነት ባለው ኃይል ሁሉ ይታገላል፣ ከሁሉ አስቀድሞ የሚገደው የእግዚአብሔርና የነፍሱ ነው እንጂ የዓለምን ነገር አይደለም። የእግዚአብሔርን መንፈስ የለበሰ የዓለም መንፈስ ይጠላል፣ ከእርሱ ይሸሻል፣ ከኃጢአት ይርቃል። ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ በመሆኑ የብርሃን የጽድቅ ልጅ ነው፣ የሥጋ ልጆችና የመንፈስ ልጆች አይስማሙም ሐሳባቸው የተለያየ ነው። “ሥጋ የኃጢአትን ሕግ ያገለግላል፣ ተቃራኒ መንፈስ ደግሞ ይፈልጋል። መንፈስ ደግሞ ተቃራኒ የሥጋ አንጻር ይፈልጋል፣ እርስ በርሳቸው ይዋጋሉ" (ገላ. 5፣17) ይላል ቅዱስ ጳውሎስ የሥጋ መንገድ የጥፋት መንገድ ነው፣ የመንፈስ መንገድ ግን የጽድቅ መንገድ ነው፡፡
የኢየሱስ ተከታዮች መሆንን አንተው የመንፈስ ልጆች እንሁን፣ የሥጋ ግብርን ፍላጐትን እንተው፣ ሥጋችንን እናሸንፍ፣ ዓለምን ደግሞ እንናቅ፣ እንመንን በመንፈስ እንደገና እንድንወለድ በክርስቶስ መንፈስ መኖር ያስፈልገናል። ያደረግነውን ብናደርግ፣ ብንከተል ድርጊታችንን እንመስላለን፣ የእርሱ ተከታዮች እንሆናለን።