ፈልግ

Cookie Policy
The portal Vatican News uses technical or similar cookies to make navigation easier and guarantee the use of the services. Furthermore, technical and analysis cookies from third parties may be used. If you want to know more click here. By closing this banner you consent to the use of cookies.
I AGREE
Messa di Requiem, per soli, coro e orchestra (conclusione)
መርዐ-ግብር በድምጽ የቀረበ ዘገባ
በአመጽ የተጎዱት የምዕራብ ሶርያ ነዋሪዎች በአመጽ የተጎዱት የምዕራብ ሶርያ ነዋሪዎች 

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዣክ ሙራድ፥ ሶርያ ለዓለም አቀፍ ሰላም ቁልፍ አገር መሆኗን ገለጹ

በሶርያ የሆምስ ካቶሊካዊ ሊቀ ጳጳስ ዣክ ሙራድ ሮምን በጎበኙበት ወቅት በሶርያ ባለውን ሁኔታ በማስመልከት ከቫቲካን መገናኛ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ሊቀ ጳጳሱ በአገሪቱ ምዕራባዊ የባህር ዳርቻ በአላውያን ማኅበረሰብ ላይ የተፈጸመውን እልቂትንም አስታውሰው ሶርያ ለዓለም አቀፍ ሰላም ቁልፍ አገር መሆኗንም አስረድተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የሶርያ የሽግግር መንግሥት ፕሬዚደንት አቶ አህመድ አል ሻራ መጋቢት 4/2017 ዓ. ም. የሕገ መንግሥታዊ ስምምነት መፈራረማቸው ሲታወስ በዚህም መሠረት የቀድሞው አገዛዝ እና ሕገ መንግሥት ተወግዶ አዲስ ምርጫ ከአራት እስከ አምስት ዓመታት ውስጥ እንዲካሄድ መወሰኑ ይታወሳል።

ይህም የሆነው በሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል በተለይ በአላዊ ጽንፈኛ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚደገፉ የሽግግር መንግሥት ሃይሎች ወደ 1,600 የሚጠጉ ሰዎችን በጨፈጨፉበት ወቅት እንደ ነበር ታውቋል።

በማዕከላዊ ሶርያ የሚገኙ የሆምስ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዣክ ሙራድ ሮምን በጎበኙበት ወቅት በሀገሪቱ የወደፊት ሁኔታ ላይ ያላቸውን ስጋት በተመለከተ ከቫቲካን መገናኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

ይህ ትክክለኛ የእስልምና እምነት ተግባር አይደለም

“ከተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ አንጻር የኃይል ድርጊቱ እና እልቂቱ አሁንም አላበቃም” ሲሉ ያስረዱት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሙራድ፥ “የዚህን መንግሥት ቅንነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባው በሚነገረው እና በተጨባጭ ሁኔታ መካከል ትልቅ ልዩነት መኖሩ ነው” ብለው፥ ስለዚህም መንግሥት ዜጎችን የሚያታልል ወይም አገሪቱን ማስተዳደር የማይችል” ሲሉ ኮንነውታል።

“በሀገሪቱ እየሆነ ያለው ነገር እንደ ሶርያ ባለ የእስልምና አክራሪነት ባልነበረበት ሀገር ውስጥ በእስልምና እምነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖን ያሳድራል” ያሉት ሊቀ ጳጳስ ሙራድ፥ “እነዚህ የጥቃት እና የእልቂቶች ድርጊቶች እስልምና አሉታዊ መልክ እንዲኖረው እንደሚያደርግ ተናግረው፥ እስልምና በመሠረቱ እንዲህ አይደለም ሲሉ አሳስበዋል።

ከሕዝቡ መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆነው የሱኒ ሙስሊም በመሆኑ በቁጥር ጥቂቶች በሆኑ ክርስቲያኖች እና በሙስሊሞች መካከል ግጭት እንደሌለ፥ ይልቁንም “በቅርብ ጊዜ ትውስታችን እና በታሪካችን ውስጥ በጣም አስቸጋሪ የሕመም ጊዜያት የነበሩ ቢሆንም በሁለቱ ቡድኖች መካከል የበለጠ ወንድማማችነት እና ሰላማዊ ግንኙነት እንዳለ ጠቁመዋል።

በሶርያ አዲስ ሕገ መንግሥት

የሽግግር መንግሥቱ በአዲሱ ሕገ መንግሥት አገሪቱን በእስልምና ሕግ ሥር እንድትተዳደር ማድረጉን ሊቀ ጳጳሱ እንደማይደግፉ ተናግረው፥ ችግሩ ሶርያ እስላማዊ አገር መሆን ወይም አለመሆን ሳይሆን ነገር ግን የእስልምና ሕግ የግለሰብን ነፃነት የማያከብር፣ በሰብዓዊ መብት እና በእስልምና ሕግ መካከል ብዙ ልዩነቶች አሉ” ሲሉ አስረድተዋል። “ሶርያ ውስጥ የተለያዩ ጎሳዎች በመኖራቸው እስልምና የሕግ ምንጭ ሊሆን አይችልም፤ የሽግግር መንግሥቱ እነዚህን ልዩነቶች ግምት ውስጥ አላስገባም” ሲሉ ተናግረዋል።

ስለዚህም ብዙ ሶርያውያን ከፍርሃት የተነሳ በመንግሥት ላይ እምነት እንደሌላቸው፣ ስደት የብዙ ሰዎች መነጋገሪያ ርዕሥ እንደሆነ እና በትውልድ ሀገራቸው እንግድነት ሊሰማቸው እንደማይገባ ሊቀ ጳጳስ ዣክ ሙራድ አሳስበዋል።

“አንድ መሠረታዊ ጉዳይ የሽግግር መንግሥቱ ሁሉንም የተለያዩ ቡድኖች በአዲሱ ሕገ መንግሥት ላይ አለማወያየቱ ነው” ያሉት ሊቀ ጳጳስ ዣክ ሙራድ፥ “በዚህም ከዲሞክራሲ እና ከነፃነት በጣም የራቅን ነን” ሲሉ አስምሮበታል።

እጅ ለእጅ ተያይዘው በጋራ መሥራት

በአሌፖ መላውን ክርስቲያን ሕዝብ የሚወክል የጋራ መግለጫ ለአዲሱ መንግሥት ማስገባታቸውን የገለጹት ሊቀ ጳጳስ ሙራድ፥ በክርስቲያኖች መካከል የተወሰነ ስምምነት ቢኖርም ነገር ግን ይህ ዓይነቱ ተነሳሽነት እና አንድነት በሁሉም ቦታ እና በማንኛውም ሁኔታ ሊተገበር የማይችል መሆኑን ጠቁመዋል።

ሊቀ ጳጳስ ሙራድ እንደ ሌላው የዓለም ቤተ ክርስቲያን የሲኖዶሳዊነትን መንገድ በመከተል ለክርስቲያኖች አንድ ጉባኤ ለማዘጋጀት መሞከራቸውን ተናግረው፥ ሆኖም በመካከላቸው በአንድ ድምፅ የመናገር እውነተኛ ፍላጎት ባለመኖሩ እስከ ዛሬ ድረስ ተግባራዊ አለመሆኑን ገልጸዋል።

ሶርያ ለዓለም ሰላም ቁልፍ ሀገር ናት

ሊቀ ጳጳስ ሙራድ፥ በሶርያ እየኖሩት ያለው ሕይወት ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኃላፊነት ጉድለት የተነሳ እንደሆነ አስረድተው፥ በቅድሚያ በሶርያ ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን የዓለም ሕዝብን ጠይቀው፥ “ሶርያ እስያን እና አውሮፓን የምታገናኝ ቁልፍ ሀገር ናት” ብለዋል።

ሊቀ ጳጳስ ሙራድ፥ በሶርያ ሰላምን ለማምጣት የመጀመሪያው እርምጃ ዓለም አቀፍ ማዕቀቦችን ማንሳት እንደሆነ ተናግረው፥ ለምን እንደተጫኑባቸው ማጣራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። በአሳድ ቤተሰብ ላይ እንደ መከላከያ ሆነው ቢቀመጡም ነገር ግን ከዚያ በኋላ ላይ ምንም ዓይነት አስፈላጊነት እንደሌላቸው፣ ማዕቀብን ማንሳት ማለት ሰዎች ወደ ቀድሞው ሕይወታቸው እንዲመለሱ መርዳት ማለት እንደሆነ፣ ሥራን እና ፕሮጀክቶችን እንደገና መጀመር ማለት እንደሆነ እና ሰዎች በጥረታቸው የመኖር ዕድልን እና ዋስትና እንዲኖራቸው የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል።

ማዕቀቡ ከተነሳላቸው በኋላ ሶርያውያን አራት ነገሮች እንደሚያስፈልጓቸው፥ እነርሱም፡- ምግብ፣ ሕክምና፣ ትምህርት እና የመኖሪያ ቤት ችግርን መፍታት እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው፥ “ይህንን ሁሉ ግምት ውስጥ በማስገባት፥ አሁን እንደሚታየው በግማሽ የተገነባች ሶርያ ሳትሆን በጥሩ ሁኔታ እንደገና የተገነባች እና የበለጸገች ሀገርን በመፍጠር ላይ ማተኮር እንደሚቻል በማስረዳት በሶርያ የሆምስ ካቶሊካዊ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዣክ ሙራድ ከቫቲካን መገናኛ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ደምድመዋል።

 

27 Mar 2025, 13:59
Prev
April 2025
SuMoTuWeThFrSa
  12345
6789101112
13141516171819
20212223242526
27282930   
Next
May 2025
SuMoTuWeThFrSa
    123
45678910
11121314151617
18192021222324
25262728293031