ፈልግ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት 

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “ማመን ማለት ታማኝ የሆነውን እግዚአብሔርን በታማኝነት ማመስገን ማለት ነው”

በሚያዝያ 07/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለአረጋውያን እና በተለይም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተጠቁትን እና በወረርሽኙ ምክንያት ተገልለው ለብቻቸውን ለሚኖሩ አረጋዊያን ጸሎት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደረጉት ስብከት ስለ እግዚአብሔር ታማኝነት እና ለእዚህ ታማኝነት እኛ የምንሰጠው ምላሽ ላይ ትኩረቱን ያደርገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ታማኝ ለሆነው እግዚአብሔር በታማኝነት ምስጋና ማቅረብ ይገባል ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ትኩረት ሰጥተው የጸለዩት ለአረጋውያን በተለይም ብቻቸውን ለሚኖሩ ወይም በአረጋውያን መጦሪያ ጣቢያ ውስጥ ለሚገኙ የእድሜ ባለጸጎች እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።  ብዙዎቹ ማንም ሰው በአጠገባቸው ስለሌለ ለብቻቸው መሞት እንደሚፈሩ ተናግሯል፡፡ ነገር ግን “እነሱ ማለትም አረጋዊያን ሥር መሰረቶቻችን እና ታሪኮቻችን” ናቸው ያሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ አስቸጋሪ በሆነ ወቅት ጌታ ለእነርሱ ቅርብ ይሆን ዘንድ መጸለይ ይኖርብናል ብለዋል።

ለአምላክ ታማኝነት የምንሰጠው ምላሽ

ቅድስት ማርያም መግደላዊት በቅዱስ ወንጌል እይታ “የታማኝነት ተምሳሌት” መሆኗን የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጹኋል።  ለአምላክ ያለን ታማኝነት “ለእግዚአብሔር ታማኝነት ምላሽ ከመስጠት ሌላ ትርጉም የለውም” ብለዋል ፡፡

እግዚአብሔር “ለቃሉ የታመነ… ለገባው ቃል ኪዳን የታመነ” ነው ፡፡ እሱ “ከህዝቡ ጋር የገባውን ቃል በመፈፀም ከህዝቡ ጋር ይሄዳል” ለገባው ቃል ታማኝ ነው በማለት የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እግዚአብሔር አዳኝ መሆኑን የሚገልጸው የሕይወት ተመክሮ የመነጨው እግዚአብሔር ለገባው ቃል ታማኝ በመሆኑ ላይ ነው ብለዋል።

የበለጠ አስደናቂ የሆነው ዳግም-መፍጠር

በእለቱ ከሐዋርያት ሥራ 3፡1-10 ላይ ተወስዶ በተነበበው የመጀመሪያው ምንባብ  ላይ ከተወለደ ጀምሮ ሽባ የነበረ አንድ ሰው በጴጥሮስ አማካይነት በኢየሱስ ስም መፈወሱን እንደ ሚገልጽ ያወሱት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህ “ነገሮችን መለወጥ የሚችል ፣ እንደገና የመፍጠር ችሎታ ያለው የእግዚአብሔር ታማኝነት ምሳሌ ነው… ይህ እርሱ ለእኛ ፍፁም ታማኝ መሆኑን የሚያሳይ ነው፣  እንደገና መፈጠር ከመፈጠር የበለጠ አስደናቂ መሆኑን ያሳየናል” ብለዋል።

እንደ አንድ ጥሩ እረኛ እግዚአብሔር የጠፋውን በግ ለመፈለግ በጭራሽ አይታክትም ያሉት ቅዱስነታቸው እሱ የሚያደርገውን ነገር የሚፈጽመው  “በፍቅር እና በታማኝነት” ነው በክፍያ ሳይሆን ከክፍያ ነጻ በሆነ መልኩ ነው ብለዋል። እግዚአብሔር ልጁ ወደ ቤቱ እስኪመለስ ድረስ ሳይታክት በደጅ ቆሞ ልጁን እንደ ሚጠባበቅ፣ ልጁን ባገኘ ጊዜ ድግስ እንደ ሚያዘጋጅ አንድ አባት ነው ያሉት ቅዱስነታቸው  “የእግዚአብሔር የታማኝነት ድግስ ፣ ነፃ የሆነ ግብዣ ፣ ለሁላችንም የተዘጋጀ ትልቅ በዓል ነው” ብለዋል።

የእግዚአብሔር ታማኝነት ከእኛ ታማኝነት ቀድሞ ይመጣል

በሕማማቱ ወቅት ኢየሱስን ለካደው ጴጥሮስ “ለጋስ የሆነው አምላካችን” ያሳየው መለኮታዊ ታማኝነት ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከትንሳኤ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጌታ ለጴጥሮስ ሲገለጽ የተናገረውን ነገር ባናውቅም “ጴጥሮስን ፈልጎ ያዳነው የእግዚአብሔር ታማኝነት መሆኑን ግን እናውቃለን” ብለዋል።

እንደ ጴጥሮስ የእግዚአብሔር ታማኝነት ሁል ጊዜም ከእኛ ታማኝነት በፊት ቀድሞ የሚገኝ ነው፣  “እናም ታማኝነታችን ሁል ጊዜ ታማኝ ሆኖ ለሚጠብቀን አምላክ የምንሰጠው ምላሽ ነው” ብለዋል።

“ለእኛ” አሉ  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን ከማጠቃለላቸው በፊት ለእኛ “ታማኝ መሆን ማለት እርሱን እግዚአብሔርን በታማኝነት ማመስገን ማለት ነው፣ ለአምላክ ታማኝ መሆን ማለት ነው፣ ለእዚህ ታማኝነት የምንሰጠው ምላሽ ነው ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

15 April 2020, 16:32
ሁሉንም ያንብቡ >