ፈልግ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ወላጆችን ማክበር እንደሚገባ ኣሳሰቡ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዛሬው ዕለት ማለትም ረቡዕ መስከረም 9 ቀን 2011 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ላይ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን፣ ነጋዲያንና ሀገር ጎብኝዎች በተሰበሰቡበት፣ የተለመደውን ሳምንታዊ የጠቅላላ ትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸውን ማቅረባቸው ተመልክቷል። ቅዱስ አባታችን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከተለያዩ ቦታዎች ለተሰበሰቡ ምዕመናንና ሕዝበ እግዚኣብሔር ሁሉ ኣባታዊ ሰላምታቸውን ካቀረቡ በኋላ ከአሥርቱ ትዕዛዛት መካከል ኣባትና እናት ማክበር እንደሚገባ የሚናገረውን ትዕዛዝ መሠረት በማድረግ ወደ ጠቅላላ ስብከታቸው ገብተዋል። ቅዱስነታቸው ዛሬ ያደረጉትን አስተምህሮ ሙሉ ይዘት ትርጉም እንደሚከተለው ቀርቧል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን

“ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ እንደምን ኣረፈዳችሁ!

የእግዚኣብሔርን ዐሥርቱን ትዕዛዛት ለመመልከት በምናደርገው ጉዞ በዛሬው ዕለት ኣራተኛ ትዕዛዝ ወደ ሆነው ኣባትህና እናትህን ኣክብር ወደሚለው ደርሰናል። ይህ ትዕዛዝ ለወላጆችም ቢሆን ትክክለኛና ማድረግ ስለሚገባቸው ነገር ይናገራል። ይህን በሚገባ ማድረግ በሚገባ መጠበቅ የሚገባውን ቦታና ክብር በተገቢ መልኩ መስጠት ያስፈልጋል።

ለመሆኑ ይህ ይምናወራለት ክብር ምን ዓይነት ክብር ነው? የዕብራይስጡ ትርጉም ለኣንድ ነገር የሚሰጥ ወይም ለኣንድ ትልቅ ሰው የሚሰጥ ክብር ወይም ትልቅ ዋጋ ያለውን ነገር የሚያመለክትና ኣንድ ወጥነት ያለውን እውነታ የሚያንፀባርቅ ነው። ስለዚህ በኣጭሩ ለኣንድ ነገር ወይም ለኣንድ ሰው ተገቢውን ክብር መስጠት ማለት የዛን ነገር ወይም የዛን ሰው ዋጋውን ማወቅና ለዛ ነገር ወይም ሰው ተገቢውን ቦታ መስጠት ማለት ነው። ይህ የምንሰጠው ክብር ወይም ዋጋ እንደው ለታይታ ከዉጭ ብቻ ያለ ነገር ሳይሆን በእውነታ ላይ የተመሠረተ ነገር ነው።

እግዚአብሔርን በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ማክበር ማለት ከእውነታው ጋር ያለውን ተምኔታዊ ሓቅ ወይም እውነታ ዋጋ መሥጠት ማለት ነው። ይህ በተጨማሪ በአምልኮ ሥርዓቶች ውስጥም ተገልጿል። ነገር ግን ከሁሉም በላይ ለእግዚአብሔር አንድ ትክክለኛ ስፍራን በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ ማቅረብ ማለት ነው። አባት እና እናት ማክበር አስፈላጊነታቸውን በተግባራዊ እሴቶች አማካኝነት እውቅና መስጠት ፍቅር እና እንክብካቤን ማሳየት ማለት ነው። ነገር ግን ይህ ኣባትና እናት ማክበር በዚህ ብቻ የሚተረጎም ሳይሆን ሓሳቡ እጅግ ሰፊና ጥልቅ ነው።

አራተኛው ትዕዛዝ የእራሱ የሆነ ባህሪ የራሱ የሆነ ውጤትም ያለው ትዕዛዝ ነው። በኦሪት ዘዳግም (ዘዳ 5 ፡16) አባትህ እና እናትህ አክብር አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ደስተኛ ትሆን ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ አክብር ይላል። ወላጆችን ማክበር ረጅምና አስደሳች ሕይወት ያስገኛል። ይህ "ደስታ" የሚለው ቃል በዐሥርቱ ትዕዛዛት ውስጥ ከወላጆች ጋር የተገናኘ ነው።

ይህ ብዙ ሺህ-አመት ያስቆጠረ ጥበብ ሰብአዊ ጥናቶች የተረዱትና ስለ እርሱም መግለፅ የጀመሩት ከአንድ ምዕተ-አመት በታች ነው። ስለሆነም በሕፃንነታችን በአእምሮኣችን የሚታተመው ነገር ሁሉ በወደፊት ሕይወታችን ላይ ትልቅ ተፅእኖ ያሳድራል እንደ ኣንድ ምልክትም ሆኖ ኣብሮን ይኖራል። አንድ ሰው ያደገው ጤናማና ሚዛናዊ ኣስተሳሰብ ባለው አካባቢ ወይም ማኅበረሰብ ወይም ቤተሰብ ውስጥ ከሆነ ይህንን እውነታ በቀላሉ ለመረዳት ይችላል።

ኣንድ ሰው ከኣስቸጋሪና የሰብኣዊ መብቶች ከሚጣሱበት ሚዛናዊ ኣስተሳሰብና ፍትሕ ከጎደሉበት ቦታ የሚመጣ ከሆነ ደግሞ ኣመለካከቱ ያደገበት ሁኔታና በዉስጡ ያስቀመጠው ልምድ ኣብዛኛውን ጊዜ የተዛባ ይሆናል። የሕፃንነት ጊዜኣችን ልክ ቀለሙ እንደማይጠፋ ወይም ሊሰረዝ እንደማይችል ቀለም ነው ይህም ነገር

ኣብዛኛውን ጊዜ በራሳችን ሕልውና ውስጥ በተለያዩ ሁኔታዎች ኣማካኝነት ይንፀባረቃል በዚህም ምክንያት ኣንዳንዶች በልጅነታቸው ያጋጠማቸውን ኣሉታዊ ሁኔታዎች ለመደበቅ ሲጥሩ ይስተዋላሉ።

ይህ አራተኛው ትዕዛዝ ኣሁንም የጠለቀ ትርጉም ኣለው። ስለወላጆች መልካም ፈቃድ አይናገርም አባቶች እና እናቶች ፍጹም እንዲሆኑም አይጠይቅም። ነገር ግን ከወላጆች ወደ ልጆች የሚተላለፈው ወይም ከወላጆች ወደ ልጆች ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውና ልጆች ከወላጆቻቸው ስለሚወርሱት ነጻና ኣስገራሚ ነገር ይናገራል። ምንም እንኳን ሁሉም ወላጆች መልካም ባይሆኑና ሁሉም ልጆች የሚያድጉበት መንፈስ በሁሉም መልኩ የሚፈለገውን ያሕል የተመቻቸና ብሩህ ባይሆንም ቅሉ ሁሉም ልጆች በወደፊት ሕይወታቸው ደስተኞች መሆን ይችላሉ ምክንያቱም ወደ ኣንድ ደስተኛና ሙሉ ሕይወት መድረስ የሚቻለው እኛን ወደ እዚህ ምድር ባመጡንና ባሳደጉን በወላጆቻችን የኑሮ ሁኔታና መንፈስ ነው።

ይህ ቃል ምንኛ ወጣቶችን በተለይም ደግሞ በልጅነት ጊዜኣቸው የተለያዩ ኣስቸጋሪና ያልተመቻቹ ሁኔታዎችን ያሳለፉ ኃላ ግን በብዙ ጥረት ራሳቸውን በመልካም ያነጹትን ወጣቶች ሊያስተምርና ሊያንጽ እንደሚችል ልብ እንበል። ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ይድረሰዉና ብዙ ቅዱሳኖችና እጅግ በጣም ብዙ ክርስቲያኖች በልጅነታቸው ብዙ ሥቃይና መከራ ቢያሳልፉም በስተመጨረሻ ከራሳቸው ሕይወት ጋር ሙሉ በሙሉ በመታረቃቸው ደስ የሚልና እንደ ብርሃን የሚያበራ ሕይወት ኖረው ኣሳልፈዋል እየኖሩም ናቸው።

እስቲ ቅዱስ ካሚሎ ዲ ሌሊስን እናስብ ምንም ካልተመቻቸ የልጅነት ኣስተዳደግ ወጥቶ የትልቅ ፍቅርና ኣገልግሎት ሕይወት ባለቤት ሆኟል ቅድስት ጅሴፒና ባኪታ በአንድ ከባድ የባርነት ሁኔታ ውስጥ ኣልፋለች ብጹእ ካርሎ ኞኪ ወላጆቻቸው በሞቱባቸው ሕፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ኣልፏል እንዲሁም ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ 2ኛ ገና በጨቅላ እድሜያቸው እናታቸውን በሞት በማጣታቸው በከፋ የልጅነት እድገት ውስጥ ኣልፈዋል።

ሰው ከየትኛዉም ይሕይወት ታሪክ ቢነሳ ከዚህኛው ከአራተኛው የእግዚኣብሔር ትዕዛዝ ወደ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የሚመራዉን ትዕዛዝ ያገኛል። በጌታችን እየሱስ ክርስቶስም ኣማካኝነት ወደ እውነተኛ ኣባቱ ወደ እግዚኣብሔር ይጠጋል። የሕይወታችንም እንቆቅሎሾች ሁሉ እግዚኣብሔር ልክ እንድ ራሱ ልጆች ኣድርጎ ባዘጋጀልን ሕይወት ውስጥ ስንገባና ስንቀበለው በዛን ጊዜ ይገለፅልናል። በሕይወታችን የምንፈጽማቸው እንቅስቃሴዎች በሙሉ ከእግዚኣብሔር የተቀበልናቸው ተልዕኮዎች ናቸው።

በፊት ያሳለፍናቸው ከባድ ሥቃዮች የሕይወት እንቆቅልሾች የፈጠሩብንን ጥያቄዎች ሁሉ በእግዚኣብሔር ጸጋ ስንረዳቸው ለኣዲስ ሕይወት ትልቅ ስንቅና ብርታት ይሆኑናል። እግዚኣብሔር በጸጋው በእኔ ሕይወት ውስጥ ገብቶ ብዙ ነግሮችን ይቀይራል ብዙ ነገሮችን ያስተካክላል።

በዚህ ሁኔታ ሁሉም ነገር ተገላቢጦሽ ይሆናል። ሁሉም ነገር ትልቅ ዋጋ ያለዉና ገንቢ ሊሆን ይችላል። እንግዲህ በዚህ መልኩ በትልቅ የልጅነት መንፈስ በተዘጋጀና ርኅራሄ በሞላው ልብ ወላጆቻችንን ማክበር

እንጀምር። ይህ ኣስገራሚ ሕይወት በሥጦታ የተበረከተልን እንጂ ባላያችን ላይ የተጫነ ጫና ኣይደለም። በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በኣዲስ መንፈስ መወለድ በነፃ የምንቀበለው ሥጦታና በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ኣማካኝነት በጥምቀታችን የምናገኘው ወይም የምንቀበለው ትልቅ ሓብት ነው። ቅዱስ ሓዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው መልዕክት ኣባታችን ኣንድ ነው እሱም በሰማይ ያለው ነው ይለናል”።

19 September 2018, 17:59