ር.ሊ.ጳ. ፍራንችስኮስ የቨሮኒካ ኣንቴል ለብጽእና መብቃትን በማሰብ እግዚኣብሔርን እናመስገን አሉ።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን
ዛሬ ማለትም ዕለተ ረቡዕ መስከረም 9 ቀን 2010 ዓ.ም. እ.ኢ.አ. ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ላይ እንደተለመደው ስብከታቸውን ኣሰምተዋል። በዛሬው ዕለት በጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ በተለይም ከዐሥርቱ ትዕዛዛት በአራተኛው የእግዚኣብሔር ትዕዛዝ ላይ ኣስተምህሮ ኣድርገዋል። እኛም የእሳቸውን ንግግርና ኣስተምህሮ ተርጉመን ለኣድማጮቻችን እንደሚከተለው ኣቅርበነዋል።
በስብከታቸው መጨረሻም በዚሁ ሳምንት እ. አ. አ. በመስከረም 22 ቀን 2018 በሮማኒያ ኔምት ተብሎ በሚጠራበት ቦታ 3ኛ የፍራንቺስካውያን ማኅበር ኣባል የሆነችው ምዕመን ቨሮኒካ ኣንታል በ1958 እ.አ.አ. በእምነት ጥላቻ ሰበብ ሕይወቷን ለእምነቷ ስትል በመስጠቷ የእርሷ ብጽእና እንደሚታወጅ ተናግረው ሁላችንም ይህች ጠንካራ ሴት በትልቅ ድፍረትና ወኔ ስለ እግዚኣብሔርና ስለ ውንድሞቿ ፍቅር ላበረከተችው ትጋድሎ እግዚኣብሔርን እናመሰግናለን ብለዋል።
በመቀጠልም የከበረ ሰላምታቸውን ለጣሊያንኛ ቋንቋ ተናጋሪ ነጋዲያን የቅዱስ ልበ እየሱስና ማርያም ወንድሞች የቅዱስ ቁርባን ስግደት ማኅበር እህቶች የፍራንቺስካን የቅዱስ ልበ እየሱስና ማርያም እህቶች ማኅበር የቀርሚሊዎስ የተልዕኮ ማኅበር ኣባላት በሮም ማርያም የቤተክርስቲያን እናት ዓለም አቀፍ ጳጳሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች እና የቀርሜሌዎስ ዓለም ኣቀፍ ስብሰባ ተሳታፊዎች እንዲሁም በሞንሲኞር ፍራንቲዜክ ራቤክ የስሎቫኪያ ብሔራዊ የጦር ሃይሎች ቡድን ከተለያዩ ቦታዎች የመጡትን የቁምስና ኣባላት
በተለይም ከቱሪና ከሳን ጆቫኒ ሮቶንዶ የመጡትን የእመቤታችን የቤተሰብ ሓዋርያዊ ቡድንን በሊቀ ጳጳስ ኤሪዎ ካስቴሉቺ የተመራዉን የካስትል ማሬ ስታቢያ ማየት የተሳናቸው ማኅበር ኣባላት በቦታው ለተሰበሰቡ ወጣቶችና አዋቂዎች እንዲሁም ሕፃናት ለታማሚዎችና ለኣዲስ ተጋቢዎች ሁሉ በሁሉ ቦታና በምንም ሁኔታ ውስጥ ወደ ክርስቶስ በመጠጋትና በእርሱ በመመራት ተስፋን ሰንቀው እንዲጓዙ ምክራቸዉን በመለገስ። ዘወትር በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ብቻ በሚገለፀው በእግዚኣብሄር ላይ እምነታቸዉን እንዲጥሉ ባማሳሰብ አጠቃላይ ጉባዔውን ዘግተዋል።