ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በገና በዓል ቡራኬ ወቅት ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም ያስተላለፉት መልእክት

በዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል በምናከብርበት በገና በዓል የወንድማማችነት መንፍስ ማጠናከር እንደ ሚገባን በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው “በሰማይ ለእግዚኣብሔር ምስጋና ይሁን” በማለት የምንዘምርበት ወቅት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት በተለይም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት የገና በዓል ቀን እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በተነሳበት የትንሳኤ ቀን ልማዳዊ በሆነ መልኩ አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በላቲን ቋንቋ “Urbi et Orb”i በአማሪኛው ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም የተሰኘ መልእክት በዓላቱን አስመልክተው እንደ ሚያስተላልፉ ይታወቃል። በእዚህም መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በታኅሳስ 16/2011 ዓ.ም ረፋዱ ላይ Urbi et Orbi በአምሪኛው ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም በተሰኘው እና የገናን በዓል አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት “ለእዚህ አዲስ ለተወለደው ሕጻን ተንበርክከን መስገድ ይኖርብናል” ማለታቸው ተገልጹዋል።
የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል በምናከብርበት በገና በዓል የወንድማማችነት መንፍስ ማጠናከር እንደ ሚገባን በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው “በሰማይ ለእግዚኣብሔር ምስጋና ይሁን” በማለት የምንዘምርበት ወቅት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
እግዚኣብሔር መልካም አባት ነው
እግዚኣብሔር መልካም የሆነ አባት እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን አባታችንን የሆነውን የእግዚኣብሔርን መልካም አብነት በመከተል እኛም ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን መልካም መሆን ይኖርብናል ያሉት ቅዱስነታቸው የወንድማማችነት መንፈስ ሰጪ የሆነው ኢየሱስ በውስጣችን እና በሕይወታችን ከሌለ ሕይወታችን ባዶ እና ከንቱ ይሆናል ብለዋል።
የወንድማማችነትን መንፈስ ማጥናከር ይገባል
የወንድማማችነትን መንፈስ ማጠናከር እንደ ሚገባ በመግለጽ መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሁላችንም፣ ዘርን፣ ሀገርን፣ ዜግነትን፣ ሐይማኖትን ማዕከል ባላደረገ መልኩ እርስ በእርሳችን በምንዋደድበት እና የወንድማማችነት መንፈስ በምናጠናክርበት ወቅት እራሱን በልጁ በእየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የገለጸውን እግዚኣብሔር አብነት በመከተል እኛም የእግዚኣብሔ ምንፈስ መገለጫ ልንሆን እንችላለን ብለዋል።
ለእስራኤል እና ለፍልስጤም ሰላም
ለእስራኤል እና ለፍልስጤም ሰላም መጸልይ እንደ ሚገባ በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ለባለፉት ሰባ አመታት ያህል ያለማቋረጥ እየተከሰተ የሚገኘው ግጭት በሰላማዊ መልኩ በውይይት ይፈታ ዘንድ ጥሪ አቅርበው እግዚኣብሔር በፍቅር የተሞላ ፊቱን ለመግለጸ የመረጠው ቦታ በመሆኑ አሁንም እግዚኣብሔር ለእዚያ አከባቢ ሰላሙን እንዲሰጥ መጸለያችንን ልንቀጥል የገባል ብለዋል።
ለሶርያ ሰላም
በሶርያ ለባለፉት ስድስት አመታት ያህል ሲካሄድ የቆየው የእርስ በእርስ ግጭት እና አስከፊ ጦርነት ያበቃ ዘንድ የሚመለከታቸው ባልደርሻ አካላት እና ዓለማቀፉ ማኅበርሰብ በትብብር ሊሰሩ እንደ ሚገባ ጥሪ ያደርጉት ቅዱስነታቸው በአሁኑ ወቅት በእነዚህ ግጭቶች እና ጦርነቶች ምክንያት ሀገራቸውን ጥለው የተሰደዱት በሚልዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ሀገራቸው በሰላም ይመለሱ ዘንድ በቅድሚያ በሶርያ ሰላምን ማረጋገጥ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው አሳስበዋል።
በተመስሳይ መልኩም በየመን፣ በአፍርካ፣ በኮርያ ልሳነ-ምድር፣ በቬንዙዌላ፣ በዩክሬን፣ በኒኳራጓ እና በተለያዩ ግጭቶች በሚስተዋሉባቸው ሀገራት ውስጥ ሰላም ይሰፍን ዘንድ የሚመለክታቸው አካላት ተግተው እንዲሰሩ እና የሕዝቦቻቸው ስቃይ ያበቃ ዘንድ ትኩረት በመስጠት የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበው፣ በገና በዓል ወቅት የተወልደው ሕጻኑ ኢየሱስ ሰላሙን ሁሉ ለሁሉም ይሰጥ ዘንድ ጸሎታቸው እንደ ሆነ ገልጸው፣ በእዚያ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተገኙትን ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የሀግር ጎብኝዎች ሰላምታን አቅርበው፣ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው እንደ ተለመደው “እባካችሁን ለእኔ መጸልይ እንዳትዘንጉ” ካሉ በኋላ መልካም የገና በዓል እንዲሆን ተመኝተው መሰናበታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

 

Photogallery

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ
25 December 2018, 18:11