ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ምድራችንን በርኅራኄ እንከባከባት ማለታቸው ተገለጸ

“ዛሬ የሰው ልጅን እየተፈታተኑ የሚገኙ ሁኔታዎች በጣም ውስብስብ ናቸው፣ እነዚህን ውስብስብ የሆኑ የሰው ልጆችን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሐስብ አንድነት፣ ወደ አንድነት የምያመራ ጥምረት፣ ተግባብቶ መሥራትን በማጠናከር የጥላቻ እና የራስ ወዳድነት መንፈስን ማስወገድ ያስፈልጋል”

በአሁኑ ወቅት በእስፔን ዋና ከተማ በማድሪድ የማድሪድ ፖሊቴክኒክ ተቋም ያዘጋጀው እና “ውሃ፣ ግብርና እና የምግብ አቅርቦት” በሚል መሪ ቃል አንድ ሲምፖዚየም በመካሄድ ላይ የግኛል። ለዚህ ዓለማቀፍ ሲምፖዚየም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የጹሑፍ መልእክት መላካቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው በጠረጴዛ ዙሪያ ተሰብስበን መወያየታችን ማመንጨት የሚገባው ሐሳብ ብክነትን እና ምኞትን ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የምድራችንን ችግሮች ለመፍታት በወንድማማችነት መንፈስ ተገናኝተን የምንወያይበት ሥፋራ ሊሆን እንደ ሚገባ” ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብታቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመልእክታቸው “ዛሬ የሰው ልጅን እየተፈታተኑ የሚገኙ ሁኔታዎች በጣም ውስብስብ ናቸው፣ እነዚህን ውስብስብ የሆኑ የሰው ልጆችን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሐስብ አንድነት፣ ወደ አንድነት የምያመራ ጥምረት፣ ተግባብቶ መሥራትን በማጠናከር የጥላቻ እና የራስ ወዳድነት መንፈስን ማስወገድ ያስፈልጋል” በማለት የዚህ በእስፔን ዋና ከተማ በማድሪድ እየተካሄደ ባለው ሲምፖዚዬም አዘጋጅ ተቋማት ለሆኑ ሙሁራን፣ የሲቪክ ማኅበርሰቡ እና ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች እንዲሁም የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የሆነው በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል FAO ባስተላለፉት መልእክት ቅዱስነታቸው  አጽኖት ሰጥተው ገልጸዋል።

በጥንቃቄ  በሚሰሩ ስሌቶች መዘፈቅ የለብንም

ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን በመቀጠል ውሃን፣ ግብርናን እና የምግብ አቅርቦትን አስመልክቶ በመካሄድ ላይ ባለው ሲምፖዚየም በመርዕ ሐሳብ ደረጃ በቀረቡት ጭብጦች እና መጽሐፍ ቅዱሳዊው ጥበብን በሚገልጹ "በዝናብ፣ በመከር እና በምግብ" መካከል ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት እንዳለ በመልእክታቸው የጠቆሙት ቅዱስነታቸው ምድራችን የምትሰጠንን በርከቶች ተቀብለን ማመስገን የጋባናል እንጂ ምድራችንን ማወደም እና መበዝበዝ ግን ተገቢ አይደለም ብለዋል። በዚህ የተነሳ በጥንቃቄ  በሚደረጉ ስሌቶች ውስጥ ተዘፍቀን መኖር እንደ ማይገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው በችግር ውስጥ የሚገኙ ማኅበርሰቦችን መሰረታዊ የሆኑ ፍላጎቶቻቸው ይሟሉ ዘንድ በመደገፍ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

በጥቂት ሰዎች ፍላጎቶች ውስጥ ብቻ ገብተን መዘፈቅ የለብንም

በዚህ በእስፔን ዋና ከተማ በማድሪድ በመካሄድ ላይ ባለው እና “ውሃ፣ ግብርና እና የምግብ አቅርቦት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ሲምፖዚዬም ላይ የወደፊቷን ምድራችንን አሁን እንገንባ በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲምፖዚዬ እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን "ይህ ሲምፖዚዬም አዎንታዊ የሆነ ገጽታ ያለው እና ትክክለኛ የለጋሽነት መንፈስ እና ትብብር" ተጨባጭ እና ታማኝ የሆነ ትብብር መፍጠር መሰረታዊ የሆኑ ነግሮች መሆናቸውን የገለጸ ሲሆን እነዚህም በማኅበርሰቡ ላይ ባተኮረ መልኩ ሰብአዊ መብትና መሠረታዊ የሰው ልጆች መብቶች ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ የሚረዱ ቁልፍ የሆኑ ሐሳቦች በመሆናቸው የተነሳ ማኅበርሰቡ እንዲበለጽግ የምያስችሉ መሰረታዊ ሐሳቦች እንዲከበሩ መሥራት እንደ ሚገብ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል። በተመሳስይ መልኩም ይህ ሐሳብ የወደፊቱ ትውልድ "አስፈላጊ እና ሙሉ የሆነ ኑሮ ለመኖር የምያስችላቸውን አስፈላጊ የሆኑ ሀብቶች" እንዲኖራቸው መንገድ የሚከፍት እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በመሬት ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ሳናደርስ መሬት ማልማት ያስፈልጋል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልእክታቸውን በቀጠሉበት ወቅት ባቀረቡት ጥሪ እንደ ገለጹት መልካም የሚባሉ ውሳኔዎችን ለማድረግ እና "ፍትሃዊ እና ሁሉን አቀፍ የሆነ ማኅበርሰብ ላይ መሰረቱን ያደርገ፣ ምንም እንኳን ምድር ለእያንዳንዱ ሰው በብዛትና በጥራት መኖር የምያስችላቸው የጠፈጥሮ ሐብት ያላት ቢሆንም ነገር ግን በሰው ልጅ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ እያሳደረ የሚገኘውን የረሃብ መቅሰፍቶችን እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል በሚገባ የሚያውቅ፣ መድራችንን ከጥፋት መታደግ የሚችል፣ የምድራችንን ውበት ጠብቆ ማቆየት እና የተለያዩ የምድራችንን የስነ-ምህዳር ክፍሎች መጠበቅ የሚያስችል፣  በምድራችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ሳያስከትሉ እርሻዎችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማልማት የሚያስችል ሁኔታዎችን እና ውሳኔዎችን ማስተላለፍ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

የክፋት እና የሰቆቃ መጥፎነት

“በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች እንደ ምናየው ሳይሆን ነገር ግን ምድራችንን በርኅራኄ መንፈስ ተሞልተን ማልማት ያስፈልጋል” በማለት በእስፔን ዋና ከታማ በማድሪድ በማካሄድ ላይ ባለው “ውሃ፣ ግብርና እና የምግብ አቅርቦት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ሲምፖዚዬም ባስተላለፉት መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በሁኑ ወቅት በዓለማችን በሚገኙ በርካታ ሥፍራዎች የሚገኙት የውሃ አካላት መበከላቸውን፣ በየሥፍራው ከልክ በላይ በሆነ መልኩ የተከመሩ አደገኛ የሆኑ ቆሻሻዎች መከማቸታቸውን፣ አስከፊ በሆነ መልኩ በመደረግ ላይ ያለውን የደን ጭፍጨፋ፣ ከባቢያዊ አየር በከፍተኛ ሁኔታ መበከሉን እና ወደ አሲድነት መቀየሩን” ምድራችን በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንደ ምትገኝ የሚያሳይ ክስተት በመሆን የተነሳ አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ እንደ ምያስፈልግ ገልጸው በማነኛውም ሁኔታ ምድራችንን በርኅራኄ ማልማት ያስፈልጋል፣ አለበለዚያ ግን እነዚህ ነገሮች ሁሉ ተዳምረው ከፍተኛ ሰቆቃ በምድራችን ላይ እንደ ምያስከትል ጨምረው ገለጸዋል።

የምግብን ተገብ የሆነ ክብር ማወቅ

በምንም ዓይነት መልኩ ምግብን ያለአግባብ ማባከን ተገቢ ያልሆነ መሰረታዊ ሐሳብ መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን ችግር ለመቀረፍ ይችላ ዘንድ “ሕጻናትን፣ ልጆችን እና ወጣቶችን እንዲያው ለይስሙላ ለመመገብ ብቻ አስበን መመገብ ብቻ ሳይሆን የሚጠበቅበን ነገር ግን ጤናማ ምግብ እንዲመገቡ ማስተማር አሰፋልጊ ነው” ብለዋል። በተገቢው ሁኔታ መመገብ - የምግብ ክብር በሚገባ እንድናውቅ በማድረግ እንዲያው ዝም ብሎ ምግብን ያለማቋረጥ መብላት እና ማጋበስ ሳይሆን የመመገብያ ሥፍራዎች የመገናኛ እና ወንድማማችነትን የመፍጠሪያ ሥፍራዎች እንዲሆኑ በማድረግ የምግብን ብክነት መቀነስ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ምድራችን የጋራ መኖሪያችን ናት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ውሃ፣ ግብርና እና የምግብ አቅርቦት” በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ ባለው ሲምፖዚዬም ላይ ባስተላለፉት መልእክት ማጠቃለያ ላይ ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት "የሰው ልጆች የሆንን ሁላችን የምንኖርበትን የጋራ መኖሪያችንን በሚገባ መንከባከብ እንደ ሚገባ” ገልጸው ሁለችንም በጋራ ያለንን በመቋደስ በሰላም የምንኖርበት ሥፋር ሊሆን እንደ ሚገባ ገልጸው ምድራችንን ከማንኛውም ጥፋት መታደግ የሁላችንም ኃላፊነ መሆኑንን ቅዱስነታቸው ከገለጹ በኃላ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

14 December 2018, 15:30