ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ሕይወታችንን ሌሎችን ለማገልገል ካልተጠቀምንበት ምንም ፋይዳ የለውም” አሉ!

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በመጋቢት 27/2012 ዓ.ም ጌታችን ኢየሱስ በታላቅ ክብር ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት፣ ሕዝቡም በታላቅ ደስታ “በጌታ ስም ሚመጣው ንጉሥ የተባረከ ነው፣ በሰማይ ሰላም፣ በአርያምም ክብር ይሁን!” በማለት የኢየሩሳሌም ሕቦች ለኢየሱስ ታላቅ አቀባበል ያደረጉበት እለት የሚከበርበት የሆሣዕና በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሮ አልፏል። የእዚህ የ2012 ዓ.ም የሆሳዕና በዓል አከባበር የተከናወነው እንደ ተለመደው እና ከእዚህ ቀደም እንደ ሚደርገው በርክታ ምዕመናን በተገኙበት ሁኔታ እንዳልነበረ የተገለጸ ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት በአሁኑ ወቅት በተለይም በጣሊያን እና ብሎም በመላው ዓለም በስፊው በመስፋፋት ላይ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ምዕመኑ በእየቤቱ ሆኖ በተለቪዢን እና በተለያዩ የማሕበራዊ መገናኛ አውታሮች በያሉበት ስፍራ ሆነው እንዲከታተሉ ተገደዋል። ይህ በዓል ከእዚህ በላይ የጠቀስነውን ወቅታዊ የሆነ ሁኔታ ከግምት ባስገባ መልኩ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ጥቂት ምዕመን በተገኙበት ሁኔታ መከበሩ የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት መሰረቱን ያደርገው በማቴዎስ ወንጌል 27 ላይ በተጠቀሰው ኢየሱስ መከራውን ሊቀበል ወደ ኢየስሩሳሌም በታላቅ ክብር መግባቱን እና በእዚያም የደርሰበትን ክህደት እና ከፍተኛ የሆነ መከራ፣ ስቃይ እና ሞት በሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ የተገለጽ ሲሆን ቅዱስነታቸው በስበካታቸው “ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔርን የምናገለግለው እኛ እንደ ሆንን አድርገን እናስባለን፣ ነገር ግን እንዲህ አይደለም እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና፣እኛን ለማገልገል በነፃነት የመረጠው እሱ ነው፣ “ሕይወታችንን ሌሎችን ለማገልገል ካልተጠቀምንበት ምንም ፋይዳ የለውም” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ማለትም በመጋቢት 27/2012 ዓ.ም የሆሳዕና በዓል በተከበረበት ወቅት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ያደረጉትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

ኢየሱስ “ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ” (ፊሊጲሲዮስ 2፡7)። በእነዚህ ቅዱሳን በሆኑት ቀናት ውስጥ ይህ የቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ቃል እንዲመራን በመፍቀድ፣ ይህ የእግዚአብሔር ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አንድ አገልጋይ አድርጎ ያቀረበበትን ሁኔታ በመመልከት በሚቀጥልው የጸሎተ ሐሙስ ማታ ደግሞ ይህንን የአገልጋይነቱን መንፈስ የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠብ ማረጋገጫ ይሰጠዋል፣ በመጪ ስቅለተ አርብ ቀን ደግሞ እርሱ መከራ ይቀበላል፣ መከራውን አሸናፊ ሆኖ የወጣ አገልጋይ ሆኖ የቀረበ ሲሆን (ት. ኢሳያስ 52:13) ነገም ስለ እርሱ ኢሳያስ የተነበየውን “እነሆ ደግፌ የያዝኩት ባሪያዬ” (ኢሳ 42 1) በማለት የተናገረውን ትንቢት እንሰማለን። እግዚአብሔር እኛን በማገልገል አድኖናል። ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔርን የምናገለግለው እኛ እንደ ሆንን አድርገን እናስባለን።  እንዲህ አይደለም! እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና፣ እኛን ለማገልገል በነፃነት የመረጠው እሱ ነው። እሱን በምላሹ መውደድ እና አለመውደድ ከባድ ነው። እናም ራሳችንን እግዚአብሔር እንዲያገለግለን ካልፈቀድንለት በስተቀር እርሱን ማገልገል የበለጠ ከባድ ነው።

ነገር ግን ጌታ እንዴት ነው የሚያገለግለን? ነፍሱን ለእኛ በመስጠት። እኛ በእርሱ የተወደድን ነን ፤ እኛ በጣም ውድ ዋጋ ያለን ነን። ቅድስት አንጄላ ዘፎሊኖ በአንድ ወቅት “ለእናንተ ያለኝ ፍቅር ቀልድ አይደለም” በማለት ኢየሱስ  የተናገረውን ቃል ሰምታ ነበር። ለእኛ ያለው ፍቅር እራሱን እንዲሠዋ እና ኃጢያታችንን ወስዶ እንዲሸከም አደረገው። ይህ ያስደንቀናል-እግዚአብሔር በኃጢአታችን ምክንያት የተቃጣብንን ቅጣት ሁሉ የራሱ በማድረግ አድኖናል። ይህንንም ያደርገው ያለምንም ማጉረምረም ነገር ግን በትህትና ፣ በትዕግሥት እና እንደ አገልጋይ በመታዘዝ እንዲሁም በንጹህ ፍቅር ብቻ ነበር። አብም ኢየሱስን በአገልግሎቱ ደግፎታል። ዲያቢሎስ ወይም ክፉ መንፈስ አቅዶት የነበረውን ክፋት አላስወገደም፣ ይልቁንም ክፋታችን በመልካም ነገር እስከ መጨረሻ በሚወደው ፍቅር እንዲሸነፍ በመከራው ጊዜ አበረታቶታል።

ጌታ እኛን ያገለገለን እጅግ በጣም የስቃይ ሁኔታዎችን በመጋፈጥ ሲሆን እርሱ ይወዳቸው በነበሩ ሰዎች ክህደት እና መገለል ደርሶበት ነበር።

ክህደት! ኢየሱስ እርሱን አሳልፎ በመስጠት በሸጠው ደቀመዝሙርና በካደው ደቀመዝሙሩ ምክንያት  ክህደት ደርሶበታል። ለእርሱ ሆሳዕና በማለት የዘመሩለት ሰዎች ትንሽ ቆይተው ደግሞ “ስቀለው!” ብለው በሚጮኹ (ማቴዎስ 27፡22) ሰዎች ክህደት ይደርስበታል። እሱ ፍትህ በጎደለው ድርጊት የተነሳ ሞት በፈረዱበት የሐይማኖት ተቋማት እና እጁን በመታጠብ ንጽሕናውን በገለጸው የፖለቲካ ተቋም ተክዱዋል። በህይወት ሂደት ውስጥ ያጋጠሙንን ትናንሽ ወይም ታላላቅ ክህደቶችን ሁሉ ማሰብ እንችላለን። ጥብቅ የሆነ እምነት በጣልንበት ነገር ክህደት እንደደረሰብን ማወቁ በጣም አሳዛኝ ነው። በልባችን ውስጥ ሕይወት እንኳ ትርጉም የለሽ እንዲመስል ሊያደርግ የሚችል አንድ ብስጭት ይቀሰቅሳል። ይህ የሚከሰትበት ምክንያት ደግሞ እኛ የተወለድነው ለመወደድ እና ብሎም ለመውደድ በመሆኑ ይተነሳ ሲሆን በእዚህ መሰረት በጣም የሚያበሳጨን እና የሚያስቃየን ነገር ደግሞ እኛ ታማኝ አድርገን በቆጠርናቸው እና ለእኛ ቅርብ በሆኑ ሰዎች መካድ ነው። ፍቅር ለሆነው እግዚአብሔር ምን ያህል ስቃይ እንደነበረ እንኳን ከእዚህ በመነሳት ለመገመት እንችላለን።

ወደ ውስጥ እንመልከተው። ለእራሳችን ታማኝ ከሆንን ክህደቶቻችንን ማየት እንችላለን። ስንት ውሸቶች፣ ግብዞነቶች እና መንታ የሆነ ሕይወት እንዳለን ልንምለከት እንችላለን። ስንት ጥሩ የነበሩ ዓላማዎች ተክደዋል! ስንት የተጨናገፉ ተስፋዎች አሉን! ስንት መፍትሄ ሳያገኙ የቀሩ ጉዳዮች እንዳሉ ልንገነዘብ እንችላለን። ጌታ ልባችንን ከእኛ በተሻለ ሁኔታ ያውቀዋል። ምን ያህል ደካማ እና እንከን ያለን መሆናችንን፣ ስንት ጊዜ እንደምንወድቅ ፣ መነሳት ለእኛ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እና አንዳንድ ቁስሎችን ለመፈወስ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያውቃል። እኛን ለመርዳት እና እኛን ለማገዝ ምን ዓይነት አገልግሎት ሰጠን፣ ምንስ አደረገ? በነቢዩ በኩል “ዓመፃቸውን እፈውሳለሁ፥ በገዛ ፈቃዴ እወድዳቸዋለሁ” (ሆሴ 14፡4) በማለት ተናግሩዋል። አለመታመናችንን እና ክህደቶቻችንን በራሱ ላይ ወስዶ እና ክህደታችንን በማስወገድ እኛን ፈውሷል። ውድቀታችን የተነሳ በመፍራት ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ አሁን የተሰቀለበትን መስቀል በመመልከት በእርሱ እቅፍ ውስጥ በመግባት “እነሆ ፣ የእኔን አለማመን ኢየሱስ ሆይ ከእኔ ውሰድ። እጆችህን ለእኔ ከፍተህ በፍቅርህ አገልግለኝ፣ ለእኔን የምታደርገውን ድጋፍ ቀጥል። እናም በእዚህ ምክንያት  እኔ አንተን ማመስገኔን እቀጥላለሁኝ።  

ብቻውን መቀረቱ! የዛሬ (መጋቢት 27/2012 ዓ.ም) ቅዱስ ወንጌል ኢየሱስ “አምላኬ ፣ አምላኬ ፣ ለምን ተውኸኝ?” (ማቴ 27፡46) በማለት ከመስቀል ላይ ሆኖ የተናገረውን አንድ ቃል እናገኛለን። እነዚህ ኃይለኛ ቃላት ናቸው። ኢየሱስ እርሱን ብቻውን ጥለውት በሄዱ ሰዎች ምክንያት መከራ ደርሶበታል። ነገር ግን አባቱ አብ ከእርሱ ጋር እሰከመጨረሻ ነበረ። አሁን በብቸኝነት ጥልቁ ውስጥ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ “እግዚአብሔር” በማለት አባቱን በተለምዶ ስሙ ጠራው። እናም “በታላቅ ድምፅ” በጣም የሚገርም ጥያቄ በማንሳት “ለምን”፣ ለምን እኔን ተውከኝ?” በማለት ይጠይቃል። እነዚህ ቃላት በእውነቱ የመዝሙረ ዳዊት ቃላት ናቸው (መዝሙር 22፡2)፤ ኢየሱስ በእዚህ ጸሎት እጅግ የከፋ ውድቀት ሊያስከትል የሚችል ተሞክሮ እንዳመጣበት ያሳያል። ነገር ግን እውነታው እርሱ ራሱ በእዚህ ስቃይ ውስጥ እንደ ገባ ያሳያል፣ ከፍተኛ የሆነ የብቸኝነት ስሜት ውስጥ እንደ ገባ ያሳያል፣ ይህንን በተመለከተ ቅዱስ ወንጌል በዋቢነት ሲጠቅስ “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም። አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? (ማቴ 27፡46) በማለት እንደ ተናገረ ይገልጻል።

ይህ ሁሉ ለምን ተከናወነ? የተከናወነው ለእኛ ነው፣ እኛን ለማገልገል የተደረገ ነው። ስለዚህ ጀርባችን ከግድግዳ ጋር የተላተመ ሲመስለን፣ ሕይወታችን በሞት ጫፍ ላይ የሚገኝ ሆኖ ሲሰማን፣ ምንም ብርሃን በሌለበት እና ማምለጫ መንገድ በሌለው በሞት ጎዳና ላይ ስንገኝ፣ እግዚአብሔር ራሱ መልስ የማይሰጥ በሚመስልበት ጊዜ ብቻችንን እንዳልሆንን መዘንጋት የለብንም። በሁሉም ነገር ከእኛ ጋር ለመሆን ኢየሱስ ከዚህ በፊት አጋጥሞት የሚያውቀውን የብቸኝነት ስሜት ተመክሮ በሚገባ ስለሚረዳው እኛን ለመርዳት ፈጥኖ የመጣል። ሁኔታችንንም በሚገባ ይረዳዋል። ለእኔ እና ለእናተም ጭምር “በፍጹም እንዳትፈሩ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ፣ የብቸኝነት መንፈስ ተመክሮ ውስጥ ገብቼ ስለነበረ ሁኔታውን በጥልቀት በመረዳት ለእናተ ይበልጥ ቅርብ ለመሆን ነው” ይለናል። ኢየሱስ እኛን የሚያገለግለው በእዚሁ ሁኔታ ነው፣ እርሱ ጥልቅ ወደ ሆነው ስቃያችን ውስጥ በመግባት ክህደት እና መገለል ደርሶበት ነበር። ስለእዚህ እኛንም ጥልቅ የሆነ ክህደት እና ብቸኝነት በሚያጋጥመን ወቅት እርሱ ሁሌም ከእኛ ጋር ነው። ዛሬ ወረርሽኙ በተከሰተበት አሳዛኝ ሁኔታ ፣ በአሁኑ ጊዜ በከበቡን በርካታ የሐሰት ደህንነቶች ፊት ለፊት፣ እጅግ ብዙ የተስፋ መቁረጥ ስሜቶች በሚታዩበት በአሁኑ ወቅት፣ ብቻችንን በመሆናችን የተነሳ በልባችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና በሚደርስበት በአሁኑ ወቅት ኢየሱስ እያንዳንዳችንን እንዲህ ይላል “አይዞህ ፣ ልብህን ለፍቅሬ ክፈተው። የሚደግፋችሁ የእግዚአብሔር የመጽናኛ ቃል ይሰማችኋል” ይለናል።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች ፣ እስከ ክህደት እና ብቸኛ እስከመሆን ድረስ ካገለገለን እግዚአብሔር ጋር ሲነፃፀር ምን ማድረግ አለብን? የተፈጠርነው ለእርሱ በመሆኑ የተነሳ እርሱን መካድ የለብንም፣ እንዲሁም በሕይወታችን ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች መካድ የለብንም። ወደ እዚህ ምድር የመጣነው እሱን እና ጎረቤቶቻችንን እንድንወድ  ነው። የተቀረው ሁሉ ያልፋል፣ ቋሚ ሆኖ የሚቀረው ይህ ብቻ ነው። እያጋጠመን ያለውን አሳዛኝ ነገር አሳሳቢ የሆኑ ጉዳዮችን በቁም ነገር እንድንወስድ እና በአሳሳቢ ጉዳዮች ላይ እንድናተኩር ይጋብዘናል፣ ሌሎችን ለማገልገል ካልተጠቀምንበት ሕይወት ምንም ፋይዳ እንደሌለው እንደገና ለመረዳት እንችላለን። ሕይወት የሚለካው በፍቅር ነው። ስለዚህ በእነዚህ በሕማማት ሳምንት ውስጥ በሚገኙ ቅዱሳን በሆኑ ቀናት ውስጥ በየቤታችን ውስጥ በተሰቀሉ መስቀሎች ፊት እንቁም፣ በእዚያ ስፊ የሆን የእግዚአብሔር ፍቅር እንደተገለጸ እንረዳለን፣ ልኬት የሌለውን የእግዚአብሔር ሙሉ ፍቅር እንደረዳለን፣ ራሱን አሳልፎ እስከመስጠት ድረስ ያገለገለን አምላክ እንዳለን እንረዳለን፣ በእዚህ መስቀል ሥር ቆመን እኛም ለማገልገል መኖር እንችል ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጠን እንለምነው። መከራ ለደረሰባቸው እና በጣም ችግር ላይ ላሉት ሰዎች እንድንደርስላቸው እንዲረዳን እንጠይቀው። ለጎደለን ነገር በጣም መጨነቅ የለብንም፣ ነገር ግን ለሌሎች መልካም ነገር ማድረግ እንችል ዘንድ እንዲረዳን እንጠይቀው።

እኔ የምደግፈው አገልጋዬን እነሆ! ኢየሱስን በፍቅር ውስጥ ደግፎ ያቆየው አባት እኛ ለማገልገል በምናደርገው ጥረትም ይደግፈናል። መውደድ፣ መጸለይ ይቅርታ ማደረግ፣ በቤተሰብ ውስጥ እና በህብረተሰቡ ውስጥ ሌሎችን መንከባከብ-ይህ ሁሉ በእርግጠኝነት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። እንደ የመስቀል መንገድ ሆኖ ሊሰማን ይችል ይሆናል። የአገልግሎት መንገድ ግን የዳንበት አሸናፊ እና አጓጊ መንገድ ነው። በተለይ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ለወጣቶች ይህንን ለማለት እፈልጋለሁ። ውድ ጓደኞቼ ፣ በዚህ ቀናት ውስጥ ወደ ብርሃን የሚመጡትን እውነተኛ ጀግኖች ተመልከቱ -እነሱ ታዋቂ ፣ ሀብታም እና የተሳካላቸው ሰዎች አይደሉም። ይልቁንም እነሱ ሌሎችን ለማገልገል ራሳቸውን የሚሰጡት ናቸው። ህይወታችሁን መስመር ላይ ለማስቀመጥ እንደተጠራችሁ ሆኖ ይሰማችሁ። ህይወታችሁን ለእግዚአብሔር እና ለሌሎች ለመስጠት አትፍሩ ፣ ተመልሶ ይከፈላችኋልና! ሕይወታችን ስጦታ በመሆኑ የተነሳ ሕይወታችንን መልሰን የምናገኘው በስጦታ መልክ ስናቀርባት ብቻ ነው፣ እናም ጥልቅ የሆነ ደስታችን የሚመጣው እንዲህ ቢሆንስ ኖሮ፣ ነገር ግን እንዲያ ባይሆንስ ኖሮ ሳንል ለፍቅር አዎናትዊ ምላሽ ስንሰጥ ብቻ ነው። ኢየሱስ ለእኛ እንዳደረገው!

05 April 2020, 14:27