ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሚያዚያ 05/2012 ዓ.ም በቫቲካን “የሰማይ ንግሥት ሆይ” የሚለውን ጸሎት ባደረጉበት ወቅት። ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሚያዚያ 05/2012 ዓ.ም በቫቲካን “የሰማይ ንግሥት ሆይ” የሚለውን ጸሎት ባደረጉበት ወቅት። 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ሁሌም ወደ ፊት መራመድ እንድንችል ጌታ የሴቶችን ድፍረት ይሰጠን” አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሚያዚያ 05/2012 ዓ.ም  ረፋዱ ላይ በላቲን ቋንቋ Urbi et Orbi በአማሪኛው ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም  ሕዝቦች ሁሉ ካስተላለፉት መልእክት በኋላ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመስጠት ከሚደገሙ ጸሎቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውና በተለይም ክርስቶስ ከሙታን ከተነሳበት የትንሳኤ በዓል ጀምሮ እስከ በዓለ ሃምሳ ድረስ የሚደገመውን “የሰማይ ንግስት ሆይ ደስ ይበልሽ” የሚለውን ጸሎት በስፍራው ከተገኙ ምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል፣ ተከታተሉን።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን 

የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች

ሴቶቹ (ማርያም እና መቅደላዊት ማርያም) የኢየሱስን ከሙታን መነሳት የሚገልጸውን መልእክት ለሐዋርያቱ እንደተናገሩ ሰምተናል። ዛሬ  በእዚህ አስቸኳይ የሆነ የጤና እክል በገጠመን ወቅት በሕክምናው ዘረፍ ብዙ ሰዎችን በመንከባከብ ላይ የሚገኙትን ሴት ሐኪሞች ፣ ነርሶች ፣ ሥርዓት አስከባሪ ኃይሎች፣በወህኒ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ ሴቶች፣ መሰረታዊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ በየሱቆች ውስጥ የሚሰሩ ሴቶች፣ በቤት ውስጥ ተቆልፈው የሚገኙትን አያቶቻቸውን፣ አዛውንቶችን፣ የአካል ጉዳተኞችን እና ልጆችን በመንከባከብ ላይ የሚገኙ እህቶች እና እናቶች ዛሬ ላስታውሳችሁ እፈልጋለሁ። በጣም ከባድ ሸክም ስለሚበዛባቸው አንዳንድ ጊዜ ለጥቃት እና ለአደጋ ተጋላጭ ናቸው። ጌታ ብርታት እንዲሰጣቸው እና ማህበረሰባችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድነት እንዲደግፉቸው ስለ እነሱ እንጸልይ። ሁልጊዜ ወደፊት መራመድ እንድንችል ጌታ የሴቶችን ድፍረት ይስጠን።

በዚህ የፋሲካ ሳምንት በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ አገራትን በሙሉ በበሽታው የተያዙና የሞቱን በተለይም ይህ ወረርሽኝ በስፋት የተከሰተባቸው ጣሊያን፣ አሜሪካ፣ ስፔን ፣ ፈረንሣይ ... ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ነው፣ ስለ ሁሉም እፀልያለሁ።  እናም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ ስለ እናንተ እንደሚፀልይ አትዘንጉ፣ እርሱ በመንፈስ ለእናንተ ቅርብ ነው።

ከልብ በመነጨ መልኩ በድጋሚ እንኳን ለፋሲካ በዓል አደረሳችሁ እላለሁ። እንደ ወንድማማቾች እርስ በእርሳችን በመተባበር በጸሎት አንድ ሆነን እንቆይ።

13 April 2020, 18:44