ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለጋስ መሆን የእግዚአብሔር መንግሥት መገለጫ ነው አሉ!
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሰኔ 21/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እርሳቸው ዘወትር እሁድ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የሚያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ለመከታተል በስፍራው ለተገኙ ምዕመናን ባደርጉት አስተንትኖ “ከእኔ ይልቅ እናቱን ወይም አባቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባም። መስቀሉን ተሸክሞ የማይከተለኝ የእኔ ሊሆን አይገባውም። ሕይወቱን ሊያድን የሚፈልግ ያጠፋታል፤ ሕይወቱን ስለ እኔ አሳልፎ የሚሰጥ ግን ያገኛታል። “እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ያገኛል። ስለዚህ እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ከእነዚህ ከታናናሾች ለአንዱ ደቀ መዝሙሬ በመሆኑ አንድ ጽዋ ቀዝቃዛ ውሃ ቢሰጠው ዋጋውን አያጣም” (ማቴ 10፡37-42) በሚለው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ ሲሆን ለጋስ መሆን የእግዚአብሔር መንግሥት መገለጫ ነው ማለታቸው ተግልጿል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእለቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳቹ!
በዚህ እሁድ የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ማቴ 10፡37-42) ለጌታ ያለንን ታማኝነት ሙሉ በሙሉ እና ያለምንም ማመንታት እድንገልጽ ግብዣ ያቀርብልናል። ቅዱስ ወንጌልን መስበክ መስዋዕትነት እና ጥረት ቢጠይቅም ደቀመዛሙርቱ ይህንን ነገር በቁም ነገር እንዲመለከቱ ኢየሱስ ይጠይቃል።
ለተከታዮቹ የሚያቀርበው እና በመጀመሪያ ደረጃ የሚጠይቀው ጥያቄ ከቤተሰብ ፍቅር በላይ ለእርሱ ፍቅር ማሳየት እንደ ሚገባን ነው። እንዲህም አለ “አባቱን ወይም እናቱን […] ወንድሙን ወይም እህቱን ከእኔ አብልጦ የሚወድ ለእኔ የተገባ አይደለም” (ማቴ 10፡ 37) በማለት ይናገራል። ኢየሱስ ለወላጆቻችን እና ለልጆቻችን ያለንን ፍቅር አቃልለን እንድንመለከት አላሳሰበንም፣ ነገር ግን ከቤተሰብ ጋር ያለን ትስስር እጅግ በጣም የተጋነነ እና የመጀመሪያውን ቦታ ከያዘ ከእውነተኛ መንገድ ሊለየን እንደ ሚችል ስለሚያውቅ የተናገረው ንግግር ነው። ይህንን ጉዳይ በሚገባ እንመልከት፣-በመንግስት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚታዩት አንዳንድ ሙስናዎች በትክክል እየተከሰቱ የሚገኘው ለዘመድ አዛማድ ያለን ፍቅር ከትውልድ አገራችን ካለን ፍቅር እጅግ የላቀ በመሆኑ የተነሳ ዘመዶቻቸውን ለመሾም እንደ ሚገደዱ እንመለከታለን። ለኢየሱስ የምናደርገውም ተመሳሳይ ነገር ነው- (ለቤተሰብ አባላቶቻችን) ያለን ፍቅር ከእርሱ ከኢየሱስ ፍቅር የሚበልጥብን ከሆነ ተግባራችን የሚሆነው ከላይ እንደ ተጠቀሰው ነው። ሁላችንም በዚህ ረገድ ብዙ ምሳሌዎችን ማምጣት እንችላለን። የቤተሰባዊ ፍቅርውስጥ ገብተው የተደበላለቀ ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች ከወንጌል ፍቅር በተቃራኒ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ ለወላጆች እና ለልጆች ያለው ፍቅር በጌታ ፍቅር ሲዋጅ እና ሲነጻ ሙሉ ለሙሉ ፍሬያማ ይሆናል፣ እናም በቤተሰቡ ውስጥም ሆነ ከዚያ ውጭ ጥሩ ፍሬዎችን ያስገኛል። በዚህ ረገድ ኢየሱስ ይህንን ሐረግ ተናግሯል። ደግሞም ኢየሱስ “እናንተ ግን አንድ ሰው አባቱን ወይም እናቱን፣ ‘ከእኔ ማግኘት የሚገባችሁን ርዳታ ሁሉ ቍርባን ይኸውም መባ አድርጌአለሁ ቢላቸው፣ እናንተም ይህ ሰው ለአባቱም ሆነ ለእናቱ ከዚህ በኋላ ምንም ነገር እንዲያደርግ አትፈቅዱለትም። ስለዚህ ለትውልድ በምታስተላልፉት ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ ይህን የመሰለም ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ” (ማርቆስ 7፡ 8-13) በማለት የህግ መምህራንን ገስጾዋቸው ነበር! ለኢየሱስ የምናሳየው እውነተኛ ፍቅር እውነተኛ የቤተሰብ ፍቅርን ይጠይቃል፣ ነገር ግን በቅድሚያ የቤተሰብን ፍላጎት ለሟሟላት የምንፈልግ ከሆነ ይህ ሁል ጊዜ በተሳሳተ ጎዳና ይመራናል።
ከዛም በኋላ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ “መስቀሉን ተሸክሞ የማይከተለኝ ለእኔ የተገባ አይደለም” (ማቴ 10፡ 38) በማለት ይናገራል። አቋራጭ መንገዶችን ሳትፈልግ እሱ ራሱ በተከተለው መንገድ ላይ የመጓዝ ጥያቄ ነው። ያለ መስቀል እውነተኛ ፍቅር የለም ፣ ማለትም በግለሰብ ደረጃ ፍቅር የሚናገኘው ዋጋ ስንከፍል ብቻ ነው። ይህንን ብዙ እናቶች እና አባቶች የሚናገሩት ነገር ሲሆን ልጆቻቸውን ለማሳደግ እና ለማብቃት ሲሉ ብዙ መስዋዕትነት እንደ ሚከፍሉ ይታወቃል፣ ይህንንም የሚያደርጉት ልጆቻቸውን ስለሚወዱ ነው። ከኢየሱስ ጋር የምንሸከመው መስቀል አስፈሪ መስቀል አይደለም፣ ምክንያቱም እሱ እጅግ ከባድ በሆነ ፈተና ሰዓት ጥንካሬን እና ድፍረትን ለመስጠት ሁል ጊዜም ከጎናችን ነውና። በፍርሀት እና በራስ ወዳድነት ስሜት ሕይወትዎን እንኳን ለማስደሰት አይቻልም። ኢየሱስ እንዲህ ሲል ያስጠነቅቃል: - “ሕይወቱን ሊያድን የሚፈልግ ያጠፋታል፤ ሕይወቱን ስለ እኔ አሳልፎ የሚሰጥ ግን ያገኛታል” (ማቴ 10፡39)። ይህም በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የምናገኘው ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ነገር ግን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይደረሰውና ብዙ ምሳሌዎችን እናያለን። በነዚህ ወቅቶችም ውስጥ እየተመለከትነው እነገኛለን። ስንት ሰዎች ናቸው ሌሎችን ለመርዳት መስቀሎችን ተሸክመዋል! በዚህ ወረርሽኝ ወቅት የተቸገሩ ሰዎችን ለመርዳት ራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉ ብዙ ሰዎች አሉ። ሁልጊዜ ከኢየሱስ ጋር ሊከናወን ይችላል። የህይወት ሙላት እና ደስታ የሚገኘው ራስን ለቅዱስ ወንጌል በመስጠት እና እንዲሁም ለወንድም እህቶቻችን ራሳችንን ክፍት በማደረግ ስንቀበላቸው እና የደግነት ተግባር ስንፈጽም ብቻ ነው።
ይህን ስናደርግ የእግዚአብሔርን ልግስና እና ምስጋና ማየት እንችላለን። ኢየሱስ ስለዚህ ያስታውሰናል-“እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል [...] ስለዚህ እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ከእነዚህ ከታናናሾች ለአንዱ ደቀ መዝሙሬ በመሆኑ አንድ ጽዋ ቀዝቃዛ ውሃ ቢሰጠው ዋጋውን አያጣም” (ማቴ 10፡40፣ 41)። የእግዚአብሔር አብ ልግስና ምስጋና ለወንድሞች የሚደረገውን አነስተኛውን የፍቅር እና የአገልግሎት መግለጫውን እንኳን ግምት ውስጥ ያስገባል። በእነዚያ ቀናት አንድ ልጅ ወደ ቤተክርስቲያን መጥቶ ወደ አንድ ቄስ ቀርቦ የተናገረውን ልብ የሚነካ ንግግር ሰማሁ “አባቴ እነዚህ እኔ የቆጠብኳቸው ትንሽዬ ስንቲሞች ናቸው፣ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች፣ በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት ድሃ ለሆኑ ሰዎች ይስጡልኝ” በማለት እንደ ተናገረ ሰምቻለሁ። ትንሽ ነገር፣ ነገር ግን ትልቅ ነገር! ይህም በሁላችን ውስጥ በመረርሽኝ መልክ ሊፈጠር የሚገባው የልግስና ተግባር ነው፣ አንድ ሰው አገልግሎት ሲሰጠን ፣ ሁሉም ነገር በእኛ በኩል ነው ብለን ማሰብ የለብንም። የለም ብዙ አገልግሎቶች በነፃ ይሰጣሉ። የበጎ ፈቃድ ስራን ያስቡ ፣ ይህ የጣሊያን ህብረተሰብ ካላቸው ትልቅ ነገር ውስጥ አንዱ ነው። በነጻ የበጎ ሥራ የሚያከናውኑ ብዙ ሰዎች በዚህ በወረርሽኙ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል! ይህንን ያከናወኑት ለፍቅር ሲሉ ነው። በምስጋና አገልግሎት መስጠት የጥሩ የስርዓተ ትምህር ውጤት ነው። የጥሩ ክርስትና ምልክት ነው። ቀላል እና እውነተኛ የእግዚአብሔር መንግሥት ምልክት ነው ፣ እርሱም የማይለወጡ እና አመስጋኝ የሆነ መንግሥት ነው።
ኢየሱስን ከህይወቷ የበለጠ የምትወደው እና ወደ መስቀሉ የተከተለች እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ሁል ጊዜ እራሳችንን በተከፈተ ልብ በእግዚአብሔር ፊት አስቀድመን እንድናስቀምጥ፣ የእርሱ ቃል ባህሪያችን እና ምርጫዎቻችን እንዲማራ ትረዳን ዘንድ አማላጅነቷን እንማጸናለን።