ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የዘረኝነት ተግባር ተቀባይነት የለውም፣ ሁከት አስፈላጊ አይደለም አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ ዕለት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደምያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በግንቦት 26/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ቤት ውስጥ ከሚገኘው ቤተ መጸሐፍት ውስጥ ሳምንታዊ የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካደረጉ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በቅርቡ በአሜሪካ በአንድ ፖሊስ አማካይነት ሕይወቱ ያለፈው ጆርጅ ፍሎይድ ላይ የተፈጸመው ተግባር በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን የገለጹ ሲሆን የእያንዳንዱ ሰው ሕይወት የተቀደሰ በመሆኑ የተነሳ በማነኛውም መንገድ ሊከበር ይገባዋል እንጂ ዓይናችንን በዘረኝነት መንፈስ መሸፈን እና ሰዎችን ማግለል ተገቢ እንዳልሆነ ቅዱስነታቸው አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

በፖሊስ ቁጥጥር ሥር በነበረበት ወቅት እ.አ.አ በግንቦት 25/2020 ዓ.ም ፖሊሱ በአንገቱ ላይ ለበርካታ ደቂቃዎች ያህል በእግሩ በመጫኑ የተነሳ ለህልፈተ ሕይወት ለተዳረገው የ46 ዓመቱ ጆርጅ ፍሎይድ ቅዱስነታቸው ጸሎት ያደረጉ ሲሆን ማንኛውንም ዓይነት ዘረኝነት ቅዱስነታቸው እንደ ሚያወግዙ የገለጹ ሲሆን በተለያዩ የአሜርካ ግዛቶች ውስጥ ህውከት እየተቀጣጠለ እንደ ሚገኝ ይታወቃል፣ ቅዱስነታቸው ሁከት አስፈላጊ ያልሆነ ተግባር ነው ብለዋል። ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን በቀጠሉበት ወቅት የሚከተለውን ብለዋል . . .

በአሜሪካ የምትገኙ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶች፣ ጆርጅ ፍሎይድ አሰቃቂ ሞት ከሞተ በኋላ በእነዚህ ቀናት ውስጥ በአገራችው ውስጥ የተከሰተ የሚገኘውን አሰቃቂ ማህበራዊ አለመረጋጋት በታላቅ ጭንቀት እየተከታተልኩኝ እገኛለሁ። ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ማንኛውንም ዓይነት ዘረኝነትን ወይም ማግለል በየትኛውም የሰው ልጅ ሕይወት እንዲከሰቱ መፍቀድ እና ዓይናችንን መጨፈን እና መታገስ በፍጹም አይኖርብንም፣ የሰው ነፍስ የተቀደሰች ናትና። በተመሳሳይ ጊዜ ​​እኛ “ባለፉት ቀናት የተከሰቱት ጥቃቶች እና ሁከቶች ራስን የሚያጠፉ እና እራሳን የሚጎዳ ተግባራት መሆናቸውን ልገልጽ እወዳለሁ። ከግጭት ጥፋትን እንጂ ሌላ የምናተርፈው ነገር የለንም።  ዛሬ የጆርጅ ፍሎይድ ነፍስ እና ለሌሎች በዘረኝነት ኃጢያት ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች ለመጸለይ በቅዱስ ጳውሎስ እና በሚኒሶታ ቤተክርስቲያን እና እንዲሁም በመላው አሜሪካን ሀገር ከሚደርገው ጽሎት ጋር በመንፈስ አብሬ መሆኔን ላረጋግጥ እወዳለሁ። ለቤተሰቦቹ እና ለልብ ወዳጆቹ መጽናናት ያገኙ ዘንድ እየጽለይኩኝ እንዲሁም ብሄራዊ እርቅ እንዲፈጠር እና የምንናፍቀውን ሰላም እግዚአብሔር እንዲሰጠን እንፀልይ። የአሜሪካ አህጉር ጠባቂ የሆነችው የጓዳሉፔ እማቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለም ውስጥ ለሰላም እና ለፍትህ ለሚሰሩ ሰዎች እንድታማልዳቸው እንጸልያለን።

03 June 2020, 13:32