ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዓለም ዙሪያ የሚካሄዱ ጦርነቶች ያበቁ ዘንድ ጥሪ አቀረቡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሐምሌ 12/2012 ዓ.ም በእለቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እንደ ተለመደው እና ዘወትር እሁድ እለት እንደሚያደርጉት  የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ግብርኤል ጸሎት ከደገሙ በኋላ ለዓለም ያስተላለፉት ሳማንታዊ መልእክት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ፍጻሜውን የሚገልጽ ምልክቶች በማይታዩበት በዚህ ዘመን በበሽታው ለሚሰቃዩ ሁሉ እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ ችግሮች ምክንያት ለሚሰቃዩ ሁሉ ቅርብ መሆኔን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ ማለታቸው ተገልጿል። በተለይም በጦርነቶች እና በግጭት ሁኔታዎች የተነሳ እየተሰቃዩ ለሚገኙ ሰዎች ሐሳቤ ከእነርሱ ጋር እንደ ሆነ ለመግልጸ እፈልጋለሁ በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት አስፈላጊውን የሰብአዊ ዕርዳታ ለመስጠት አስፈላጊ የሆኑትን ሰላምና ደህንነት ማስገኘት በሚችል መልኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ አስቸኳይ የተኩስ አቁም አማጅ እንዲተገበር በድጋሜ እጠይቃለሁ ብለዋል።

በተለይም በአርሜኒያ እና በአዘርባጃን መካከል ባለው የካውከስ ክልል ላለፉት ጥቂት ቀናት ስለተፈጠረው ውጥረት እንደ ሚያስጨንቃቸው በመልእክታቸው የተናገሩት ቅዱስነታቸው በግጭቱ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦች ጸሎት እንደ ሚያደርጉ ያረጋገጡ ሲሆን አለም አቀፍ ማህበረሰብ ይህ ችግር በውይይት ይፈታ ዘንድ እና በቀጠናው ዘላቂ የሰላም መፍትሄ እንዲመጣ የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግ ቅዱንሰታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን ከማጠቃለላቸው በፊት በስፍራው ለተገኙት ምዕመናን ሰላምታ አቅርበው እና ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ከሰጡ በኋላ ሳምንታዊ መልእክታቸው አጠናቀዋል።

19 July 2020, 11:50