ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዩክሬይን በተደረገው የተኩስ አቁም መደሰታቸውን ገለጹ! ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዩክሬይን በተደረገው የተኩስ አቁም መደሰታቸውን ገለጹ! 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዩክሬይን በተደረገው የተኩስ አቁም መደሰታቸውን ገለጹ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሐምሌ 19/2012 ዓ.ም በእለቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እንደ ተለመደው እና ዘወትር እሁድ እለት እንደሚያደርጉት  የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ግብርኤል ጸሎት ከደገሙ በኋላ ለዓለም ያስተላለፉት ሳማንታዊ መልእክት በቅርቡ በዩክሬይን በተፈረመው የተኩስ አቁም እጅግ መደሰታቸውን የገለጹ ሲሆን በዩክሬይን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚቻለው የታጠቁ ኃይሎች መሳሪያቸውን ሲፈቱ እና የተቀበሩ ፍንጂዎች ከአከባቢው ሲፀዱ መሆኑን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ስምምነቱ በዶኔትስያን ህዝብ ሪፖብሊክ እና በዩክሬን ጦር ኃይሎች መካከል የተፈጸመ ስምምነት ሲሆን አሁን ባለው የተኩስ አቁም ተግባር ላይ ተጨማሪ ስምምነቶችን መፈጸም እና የፀደቁ ስምምነቶችን ተግባራዊ የሆኑ እርምጃዎችን በመውሰድ ተገቢውን ሰላም በአከባቢው ማስፈን እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን ከማጠቃለላቸው በፊት በስፍራው ለተገኙት ምዕመናን ሰላምታ አቅርበው እና ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ከሰጡ በኋላ ሳምንታዊ መልእክታቸው አጠናቀዋል።

26 July 2020, 10:23