ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የእግዚአብሔርን መንግሥት መፈለግ ይኖርብናል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሐምሌ 19/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እርሳቸው ዘወትር እሁድ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የሚያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ለመከታተል በስፍራው ለተገኙ ምዕመናን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉት አስተንትኖ በማቴዎስ ወንጌል  (ማቴ 13፡44-43)  ላይ በተጠቀሰው “መንግሥተ ሰማይ በዕርሻ ውስጥ የተደበቀ ሀብት ትመስላለች፤ አንድ ሰው ባገኛት ጊዜ መልሶ ሸሸጋት፤ ከመደሰቱም የተነሣ ሄዶ፤ ያለውን ሁሉ በመሸጥ ያንን የዕርሻ ቦታ ገዛ፣ ንዲሁም መንግሥተ ሰማይ ውብ ዕንቍ የሚፈልግ ነጋዴ ትመስላለች፤ እጅግ ውድ የሆነ ዕንቍ ባገኘም ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጦ ገዛው። ደግሞም መንግሥተ ሰማይ ወደ ባሕር ተጥሎ የዓሣ ዓይነቶችን የያዘ መረብ ትመስላለች ” በሚለው የተደበቀ ሀብትና የዕንቍው ምሳሌ በሚገልጸው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ያለማቋረጥ የእግዚአብሔርን መንግሥት መፈለግ ይኖርብናል ማለታቸው ተገልጿል።

 የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእለቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳቹ!

በዛሬው እለተ ሰንበት የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ማቴ. 13፡44-52 ይመልከቱ) ወንጌላዊ ማቴዎስ ስለመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ያሰፈረውን ምዕራፍ የመጨረሻ ክፍል ያቀፈ ነው። ምንባቡ በጣም በአጭሩ የተገለጹ ሦስት ምሳሌዎችን ያጠቃልላል-የተደበቀ ውድ ሀብት ፣ ውድ ዕንቁ እና ወደ ባሕር የተጣለ መረብ ተካተውበታል።

መንግሥተ ሰማያት በሁለት የተለያዩ “ውድ” ዕቃዎች ማለትም በዕርሻ ውስጥ የተደበቀውን ውድ ሀብት እና ከፍተኛ ዋጋ ካለው ዕንቁ ጋር የሚነፃፀርባቸውን የመጀመሪያዎቹን ሁለቱን ምሳሌዎች እመለከታለሁ። ዕንቁውን ወይም ሀብቱን ያገኘው ሰው የሰጠው ምላሽ ተመሳሳይ ነው - ይህ ሰው እና ነጋዴው አሁን በጣም የሚወዱትን ውድ የሆነ ነገር ለመግዛት ሁሉንም ነገር ይሸጣሉ። በነዚህ ሁለት ምሳሌዎች ፣ ኢየሱስ መንግሥተ ሰማያት መገንባት ሂደት ውስጥ እኛን ለማሳተፍ ሃሳብ አቅርቧል ፣ ክርስቲያናዊ ሕይወትን ለመንግሥተ ሰማያት ሕይወት አስፈላጊ ባህርይ መሆኑን በመግለጽ ለመንግሥቱ  ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ያስገዙ እና ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች፣ መንግሥተ ሰማይ ለመግባት የተቻላቸውን ሁሉ የሚያደርጉ ቁርጠኛ የሆኑ ብርቱ የሆኑ ሰዎች እንደ ሆኑ ይገልጻል። በእርግጥም በእነዚህ ሁለት ምሳሌዎች ውስጥ ያለው ሰውም ሆነ ነጋዴ ያላቸውን ሁሉ ይሸጣሉ፣ ስለሆነም ቁሳዊ ደህንነታቸውን ይክዳሉ። ከዚህ በመነሳት መረዳት የሚቻለው የመንግሥተ ሰማይ መግባት የሚቻለው በእግዚአብሔር ፀጋ ብቻ ሳይሆን ፣ የሰውን ልጅም ንቁ ፈቃድን እና ተሳትፎ እንደ ሚጠይቅ እንመለከታለን። ሁሉም ነገር በፀጋ ነው የሚከናወነው ፣ ሁሉም ነገር! ጸጋን ለመቀበል ፈቃደኝነትን መግለጽ ይገባናል እንጂ፣ ጸጋን መቃወም አያስፈልግም።

ንብረታቸውን ሽጠው የበለጠ ውድ ሀብቶችን ለመግዛት የሚፈልገው ሰው እና ነጋዴው ወሳኝ ምልክቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን እነሱ “እንድ አቅጣጫ መንገድ የሚያመለክቱ ምልክቶች ናቸው እንጂ የደርሶ መልስ መንገድ ምልክቶች አይደሉም። በተጨማሪም  ሁለቱም በደስታ የፈለጉትን ሀብት ስላገኙ በደስታ የተሰሩ ምልክቶች ናቸው። እኛ ጤናማ በሆነ መልኩ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመፈለግ የምንቅበዘበዝ ሰዎች እንድንሆን  እነዚህ ሁለት የወንጌል ምሳሌዎችን ዝንባሌ ከግምት ውስጥ እንድናስገባ ይጠይቀናል።  መንግሥቱን እንዳንፈልግ እና እንዳንገነባ የሚያግደንን አለም የሚሰጠንን ዋስትና ከባድ ሸክም የመተው ጉዳይ ነው፣ ለንብረት መጎምጀት ፣ ለትርፍ እና ለስልጣን ጥማት እና ስለራሳችን ብቻ ማሰብ የመሳሰሉትን ነገሮች ማስወገድ ይኖርብናል።

በዘመናችን ሁላችንም እንደምናውቀው አንዳንድ የሰዎች ሕይወት በሐዘን እና በድብርት ውስጥ ሊገባ ይችላል ምክንያቱም ምናልባት እውነተኛ ሀብትን ለመፈለግ ስለማይሄዱ ይሆናል፣ ማራኪ እና ጊዜያዊ በሆኑ ነገሮች ረክተው ይኖራሉ ፡፡ ብርሃናቸው በሚያንጸባርቅ መብራቶች ተስበው እውነት መስሎዋቸው በሚገቡበት ወቅት ብርሃን አልባ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፣ ጨለማ ውስጥ እንደ ሆኑ ይረዳሉ። ይልቁንም የእግዚአብሔ መንግሥት ብርሃን እንደ ርችት አይደለም ፣ እሱ ቀላል ነው ርችቶች ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚቆዩ ናቸው፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ብርሃን በሕይወታችን ሁሉ ላይ አብሮ ይኖራል።

መንግሥተ ሰማይ ዓለም ከምታቀርባቸው አስደናቂ ነገሮች በተቃራኒ ጎራ የሚገኝ ነው፣ ከመንግስተ ሰማይ ሕይወት በተቃራኒ የሚገኝ ሕይወት ነው - ህይወትን በየቀኑ የሚያድስ እና ወደ ሰፊው አድማስ እንዲዘዋወር የሚመራው ውድ ሀብት ነው። በእርግጥ  ይህንን ውድ ሀብት ያገኘ ሰው የፈጠራ ችሎታ እና አስተዋይ ልብ አላቸው፣ ይህም ደግሞ እግዚአብሔርን እንድንወድ ፣ ሌሎችን እንድንወድ እና እራሳችንን በእውነተኛ መንገድ እንድንወድ የሚያደርጉን አዲስ ጎዳናዎችን በመፈለግ  ወደ እርሱ መንግሥት እንድናመራ ያደርገናል ማለት ነው። በዚህ በመንግሥቱ ጎዳና የሚመላለሱ ሰዎች ምልክት የፈጠራ ችሎታ ነው፣ ሁልጊዜ የበለጠ ለማድረግ መሞከርን ያጠቃልላል። የፈጠራ ችሎታ ሕይወትን የሚሰጥ ነው። ሁልጊዜ ሕይወት የሚሰጠውን ብዙ ሌሎች መንገዶችን ይፈልጋል።

የተደበቀ ውድ ሀብትና ዕንቁ የሆነው ኢየሱስ አለም በሚሰጠን ደስታ መነሳሳት ብቻ ሳይሆን የህይወትን ትርጉም በማግኘት በደስታ እና በቅድሳን ራሳችንን ለእግዚአብሔር መንግሥት እንድንሰጥ ይረዳን ዘንድ ልንማጸነው የገባል።

እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል የሰጠን ፍቅር በቃል እና በተግባር መግለጽ እንችል ዘንድ እንዲገለጽልን ሁሌም የመንግሥተ ሰማይን ውድ ሀብት ለመፈለግ እንድንችል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ ትርዳን።

26 July 2020, 17:06