ፈልግ

 በቤላሩስ ውስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋት እንዲቀረፍ የጸሎት ስነ ስረዓት ተካሂዶ ነበር በቤላሩስ ውስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋት እንዲቀረፍ የጸሎት ስነ ስረዓት ተካሂዶ ነበር 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለሊባኖስ እና ለቤላሩስ ሕዝቦች ጸሎት ማድረጋቸውን እንደ ሚቀጥሉ ገለጹ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በነሐሴ 10/2012 ዓ.ም በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እንደ ተለመደው እና ዘወትር እሁድ እለት እንደሚያደርጉት  የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ግብርኤል ጸሎት ከደገሙ በኋላ ለዓለም ያስተላለፉት ሳማንታዊ መልእክት በቅርቡ በሊባኖስ ዋና ከተማ በቤሩት በሚገኘው በአንድ ወደብ አቅራቢያ በተከሰተው ፍንዳታ በርካታ ሰዎች መሞታቸው እና መቁሰላቸው፣ እንዲሁም በከተማይቷ ላይ ከፍተኛ የሆነ ውድመት መድረሱን የሚታወስ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባስተላለፉት መልእክት “እኔ ለሊባኖስ እና በዓለም ዙሪያ በሚከሰቱ አስቃቂ ክስተቶች ምክንያት እየተሰቃዩ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ መጸለዬን እቀጥላለሁ” ብለዋል።

“ሀሳቤም ወደ ተወደደው የቤላሩስ ሕዝብ ይሄዳል። በዚያ ሀገር ውስጥ ከድህረ ምርጫ በኋላ ያለውን ሁኔታ በጥብቅ እየተከተልኩ ስለሆነ ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ፣ ሁከት እንዲወገድ፣ የፍትህ እና የህግ የበላይነት ይሰፍን ዘንድ” ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል፣ አክለውም ሁሉንም ቤላሩስያን የሰላም ንግሥት የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥበቃ እንዲያገኙ እጸልያለሁ ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክታቸውን በቀጠሉበት ወቅት በስፍራው እርሳቸው በእለቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ለመከታተል የተገኙ ምዕመናን አመስግነው እና ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

16 August 2020, 10:36