ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ቅዱስ ቁርባን ሌሎችን እንድናገለግል ብርታት ይሰጠናል” ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሐምሌ 26/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እርሳቸው ዘወትር እሁድ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የሚያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ለመከታተል በስፍራው ለተገኙ ምዕመናን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉት አስተንትኖ በማቴዎስ ወንጌል  (ማቴ 14፡13-21)  ላይ በተጠቀሰው ኢየሱስም አምስት ሺህ ሰዎችን በታምር መመገቡን”  በሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “የኢየሱስ ኃይል አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን በማደረግ ላይ ብቻ ትኩረቱን ያደረገ ሳይሆን ለችግረኞች በርኅራኄ የሚገልጸ ኃይል ጭምር ነው፣ ቅዱስ ቁርባን ሌሎችን እንድናገለግል ብርታት ይሰጠናል” ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእለቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳቹ!

የዚህ እለተ ሰንበት ቅዱስ ወንጌል ኢየሱስ በአምስት ዓሳ እና በሁለት እንጀራ አምስት ሺህ ሰዎችን የመገበበትን ተዓምርን ያቀርብልናል (ማቴ 14፡13 - 21 ተመልከቱ። ትዕይንቱ የተከናወነው ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ገለልተኛ ወደ ነበረ ወደ አንድ በረሃማ ስፍራ በሄደበት ወቅት ነበር። ነገር ግን ህዝቡ እሱን ለመስማት እና ለመፈወስ ፈልገው ስለነበረ ወደ እርሱ ይሄዳሉ፣ በእርግጥም የእርሱ ቃል እና ተግባር ተስፋሳቸው እንዲለመልም አድርጎ ነበር። ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ አሁንም ሕዝቡ ተሰብስቦ የነበረ ሲሆን ደቀመዛሙርቱ ሕዝቡ ወደ አቅራቢያ መንደሮች ሂደው የሚበላ ነገር ለራሳቸው እንዲፈልጉ ኢየሱስ ሕዝቡን ያሰናብት ዘንድ ይጠይቁታል። እርሱ ግን መልሶ “የሚበሉት ነገር እናንተው ስጧቸው” (ቁ. 16) በማለት ይመልስላቸዋል። የደቀ መዛሙርቱን ፊት መገመት እንችላለን! ኢየሱስ ሊያደርገው ስላሰበው ነገር ጠንቅቆ ያውቃል፣ ነገር ግን “ለራሳቸው ምግብ ይፈልጉ ዘንድ አሰናብታቸው” የሚለውን የደቀ መዛሙርቱን አመለካከት  ለመለወጥ ፈለጎ እና መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት የሚያስገኘውን ጸጋ ለመግለጽ በማሰብ፣ እንዲሁም ኢየሱስ ይህንን የጓደኞቹን ፣ በዚያን ጊዜ እና አሁን ለሚገኙ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር አመክንዮ ማለትም ለሌሎች ሀላፊነት የመውሰድ አመክንዮ ለማስተማር ይህንን ሁኔታ ሊጠቀም ይፈልጋል።

ከአስራ ሁለቱ አንዱ እንደተናገረው በእውነቱ “እኛ እዚህ አምስት ዳቦና ሁለት ዓሣ ብቻ ነው ያለን” ብሎ ሲናገር ኢየሱስ “እስቲ ያለውን ወደ እኔ አምጡልኝ” (ማቴ 14፡17-18) በማለት ይመልስላቸዋል። እሱም አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ዓይኑን ወደ ሰማይ በማቅናት አመስግኖና ባርኮ እንጀራውን ቈረሰ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ሰጠ፤ እነርሱም ለሕዝቡ ሰጡ። እነዚያም እንጀራዎች እና ዓሦች ለሕዝቡ አላነሷቸውም ነበር፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በልተው ከጠገቡ በኋላ ብዙ ምግብ ተርፎ ነበር።

በዚህ ተግባሩ ኢየሱስ ኃይሉን ይገልጣል፣ አስደናቂ በሆነ መንገድ ሳይሆን እንደ አንድ አባት የልግስና ምልክት በማሳየት ለደከሙ እና ለተቸገሩ ልጆቹ እግዚአብሔር አብ የሚያሳየውን ተግባር ይገልጻል። እሱ በሕዝቡ ሕይወት ውስጥ ገብቷል እናም ድካማቸውን እና አቅማቸውን ይረዳል፣ ነገር ግን እሱ ማንም እንዲያጣ ወይም እንዲጠፋ አይፈቅድም፣ እርሱ በቃሉ እና አስፈላጊውን እርዳታ በማደረግ ሕዝቡን ይንከባከባል።

ይህ የቅዱስ ወንጌል ክፍል በግልፅ የሚያመለክተው ቅዱስ ቁርባንን ሲሆን በተለይም የበረከት መግለጫ የሆነውን እንጀራ የመቁረስ ስነ ስረዓት፣ ለደቀመዛሙርቱ መስጠትና ለሕዝቡ መሰራጨትን ያመለክታል። ዘለአለማዊ ምግብ በሆነው በቅዱስ ቁርባን እና ለምድራዊ ሕይወት አስፈላጊ በሆነውን ዕለታዊ እንጀራ መካከል ያለው ትስስር ትኩረት የሚስብ ነው። ራሱን እንደ የሚያድን እንጀራ አድርጎ ከመስጠቱ በፊት ኢየሱስ እርሱን ለሚከተሉት እና ከእሱ ጋር ለመሆን የሚፈልጉ ሰዎች በቂ የሆነ ምግብ እንዳላቸው ለማረጋገጥ ይፈልጋል። አንዳንድ ጊዜ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ነገሮች እርስ በእርሳቸው ሲገጫጩ እናያለን፣ ነገር ግን በእውነቱ መንፈሳዊነት ፣ ልክ እንደ ፍቅረ ንዋይ ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተለየ ነው።

የዕለት ተዕለት ምግባችንን በየቀኑ እንድንጠይቅ ኢየሱስ አስተምሮናል - ለመኖር በሚያስፈልገው እንጀራ እና በቅዱስ ቁርባን እንጀራ መካከል አንዳች ተቃውሞ የለም። በተቃራኒው የወንድሞቻችን እና የእሕቶቻችንን ፍላጎቶች በመዘንጋት ወደ ቅዱስ ቁርባን ስነ ስረዓት በምንቀርብበት ጊዜ አዎን ይህ ተቃውሞ ያስነሳል። ኢየሱስ ለሕዝቡ ያሳየው ርህራሄ እና ምሕረት ስሜታዊነት አይደለም፣ ነገር ግን የሰዎች ፍላጎቶች የሚያሳስበው መሆኑን የሚያሳይ ተጨባጭ መገለጫ ነው። ቅዱስ ቁርባንን ለመቅበል ወደ መነበረ ታቦቱ በምንቀርብበት ወቅት ይህንን የመሰለ የኢየሱስ ባሕሪይ ተላብሰን ሊሆን ይገባል፣  ለሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች ርህራሄ በማሳየት በአብ በተገለጠው ፍቅር መታመን እና በድፍረት ለሌሎች ማጋራት ይኖርብናል።

እመቤታችን ቅድስት ማርያም በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ ጌታ ያሳየንን መንገድ እንድንጓዝ ትርዳን። ይህ የዓለምን ድህነት እና መከራን ለመጋፈጥ እጅግ አስፈላጊ የሆነውና ከዓለም ባሻገር የሚጠቅመንን የወንድማማችነት ጉዞ ሲሆን ምክንያቱም በእግዚአብሔር የሚጀመርና ወደ እግዚአብሔር የሚመለስ ጉዞ ነው።

02 August 2020, 16:25