ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የፍልሰታ ማርያም በዓል የሰው ልጆችን ተስፋ ከፍ ያደርገ በዓል ነው አሉ!
የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በነሐሴ 09/2012 ዓ.ም እምቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ እና በነፍስ ወደ ሰማይ የወጣችበት የፍልሰታ ማርያም ዓመታዊ በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። ይህ የፍልሰታ ማርያም አመታዊ በዓል በቫቲካን በተከበረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን የፍልሰታ ማርያም በዓል የሰው ልጆችን ተስፋ ከፍ ያደርገ በዓል ነው ማለታቸው ተገልጿል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእለቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!
የሰው ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ እግሩን በጨረቃ ላይ ባሳረፈበት ወቅት “ይህ ለሰው ልጅ አንድ ትንሽ እርምጃ፣ ነገር ግን አንድ ትልቅ ዝላይ ነው” የሚል አንድ እጅግ ታዋቂ የሆኖ ሀረግ መናገሩ ይታወሳል። በመሠረቱ የሰው ልጅ ታሪካዊ ግብ ላይ ደርሷል። ነገር ግን ዛሬ ማርያም ወደ ሰማይ ያረገችበት ሁኔታ የሚያመለክት እጅግ የላቀ ታላቅ ድል እናከብራለን። እናታችን ማርያም በገነት ውስጥ እግሯን አሳርፋላች፣ እርሷ ወደ አዚያ የሄደችው በመንፈስ ብቻ ሳይሆን ከስጋዋ ጭምር በሙሉ ስብዕናው ወደ ገነት ገብታለች። ይችህ ከናዝሬት የተገኘች ድንግል የደረሰችበት ደረጃ ለሰው ልጆች ትልቅ ዕጣ ፈንታ ነበር። በምድር ላይ እንደ ወንድም እና እህት ሁነን መኖር ካልቻልን በቀር ወደ ጨረቃ መሄዳችን ብዙም አይጠቅመንም። ነገር ግን እያንዳንዳችን በመንግሥተ ሰማይ ውስጥ እንደምንኖር ተስፋ ይሰጠናል ፣ እኛ ውድ እንደሆንን ፣ እንደገና ለመነሣት እንደ ተጠራን እናውቃለን። እግዚአብሔር ሰውነታችን በከንቱ እንዲጠፋ አይፈቅድም። በእግዚአብሔር ዘንድ ምንም አይጠፋም! ይህ በማርያም አማካይነት ግቡ ላይ ደርሷል እናም የምንጓዝበትን ምክንያቶች በዓይኖቻችን ፊት ተመልክተናል- ከንቱ የሆኑ በዚህ ዓለም የሚገኙትን ነገሮች ለማግኘት ሳይሆን ነገር ግን ከዚያ በላይ የሚገኘውን ዘላለማዊ የሆነ ነገር ለማሳካት እንደ ተጠራን እንገነዘባለን። እመቤታችንም የምትመራን ኮከብ ናት። መጀመሪያ እዚያ ሄዳለች። እርሷ የምክር እናት እና አሰታማሪ እንደ መሆኗ መጠን “በምድር ላይ በእንግድነት በቆየበት ጊዜ የእግዚአብሔር ሕዝብ በእርግጠኝነት የተረጋገጠ ተስፋ እና የመጽናናት ምልክት” ሆና ታበራለች።
እናታችን ምን ትመክረናለች? ዛሬ ቅዱስ ወንጌል ውስጥ እርሷ በቀዳሚነት “ነፍሴ ጌታን ታከብራለች” (ሉቃ 1፡46) በማለት ትናገራለች። እኛ እነዚህን ቃላት በተደጋጋሚ መስማት የለመድን ሰዎች ምናልባት ለእነዚህ ቃላት ትርጉም ትኩረት አንሰጥም ይሆናል። “ማክበር” የሚለው ቃል በጥሬው ትርጉም ስንመለከተው በቀጥታ “ታላቅ”፣ ማጉላት የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል። ማርያም “ጌታን ታከብራላች”: - በወቅቱ ማርያም የጎደሉባት ችግሮች ቢኖሩባትም ነገር ግን በከፍተኛ ሁኔታ ጎድሏት የነበረው ጌታ ነበር። ምን ያህል ጊዜ ነው እኛ ስለራሳችን ችግሮች የምንጨነቀው እንዲሁም በፍርሀቶች የምንዋጠው! እመቤታችን ግን እንዲህ አላደረገችም ምክንያቱም እርሷ የመጀመሪያው የህይወት ታላቅ የሆነ ነገር ለእግዚአብሔር ትሰጣለች። ከዚህ ነው እንድግዲህ ያ ታላቅ ክብር የሚመነጨው፣ ከዚህ ደስታ ተወለደ፣ የችግሮች አለመኖር ሳይሆን ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ የሚመጣ ደስታ የተወለደው ለእኛ ቅርብ ከሆነው ከእግዚአብሔር ፊት ነው። እግዚአብሔር ታላቅ ስለሆነ ነው። እናም ከሁሉም በላይ እግዚአብሔር ዝቅ ያሉ ሰዎችን ይመለከታል። እኛ ደካማች የእግዚአብሔር ፍቅር ይጎበኘናል፣ እግዚአብሔር ዝቅተኛውን ይወዳል።
ማርያም በእውነቱ ዝቅተኛ መሆኗን ትገነዘባለች እናም “ታላቅ ነገሮችን አድርጎልኛል” በማለት ከፍ አድርጋ ታመሰግናለች። ጌታ እንዳደረገላት ታምናለች። ጌታ የደረገላት ነገሮች ምንድን ናቸው? በመጀመሪያ እና ከሁሉም በላይ ያልተጠበቀ የሕይወት ስጦታ የሆነው ማርያም ድንግል ሆና ሳለ ትፀንሳለች። ኤልሳቤጥም ደግሞ በዕድሜ የገፋች ብትሆንም ልጅ በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች። ጌታ ተአምራትን የሚሠራው ዝቅተኛ ከሆኑ ሰዎች ጋር ነው፣ እነሱ ራቻቸውን ታላቅ እንደ ሆኑ አድርገው ከማይቆጥሩ ሰዎች ጋር እና በህይወታቸው ለእግዚአብሔር በቂ ስፍራ ከሰጡ ሰዎች ጋር ሆኖ ተአምራትን ይሰራል። በእርሱ ለሚታመኑት ምሕረቱን ይሰጣል፤ ትሑታንንም ከፍ ከፍ ያደርጋል። ማርያም ለዚህ ነገር እግዚአብሔርን አመሰገነች።
እናም እኛ እራሳችንን መጠየቅ እንችላለን -እግዚአብሔርን ማመስገን እናስታውሳለን? ለእኛ ለሚያደርግልን ታላላቅ ነገሮች አመስጋኞች ነን? እርሱ ሁል ጊዜ ስለሚወደን እና ይቅር ሲለምለን፣ እንዲሁም ስለ ፍቅሩ ሲል ለእኛ በእየለቱ ለሚሰጠን ቀናት አመስጋኞች ነን? በተጨማሪም እናቱን ለእኛ ስለሰጠን፣ በጉዞዋችን ወንድሞች እና እህቶችን በመንገዳችን ላይ ስላኖረለን እና መንግሥተ ሰማይን ስለከፈተልን ለእነዚህ ነገሮች እግዚአብሔርን እናመሰግናለን? መልካሙን ከረሳን ልባችን እየቀነሰ ይሄዳል። ነገር ግን እንደ ማርያም ጌታ የሚያደርጋቸውን ታላላቅ ሥራዎችን የምናስታውስ ከሆነ፣ ወደ ፊት አንድ እርምጃ መራመድ ከፈለግን ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ እሱን “ከፍ ከፍ” ማደረግ ይኖርብናል። በእየለቱ በቀን አድን ጊዜ እንኳን ሳይቀር “እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” በማለት “ጌታ የተባረከ ይሁን” በማለት አጭር የምስጋና ጸሎት ማቅረብ ይኖርብናል። ይህ እግዚአብሔርን ማመስገን ነው። በዚህ አጭር ጸሎት ልባችን ይሰፋል፣ ደስታም ይጨምራል። በየቀኑ ዓይናችንን ወደ ሰማይ ወደ እግዚአብሔር ቀና በማድረግ “አመሰግናለሁ!” ብለን በየቀኑ በመናገር የእርሱን ፀጋ እንድናገኝ እንድትረዳን የሰማይ ደጃፍ የሆነችውን የማርያምን አማላጅነት እንለምን። ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎች ለታላላቅ ሰዎች “አመሰግናለሁ” እንደሚሉት እኛም ዝቅተኛ የሆንን የእርሱ አገልጋዮች እርሱን ሁል ጊዜ እናመስገን!