ፈልግ

በኮሎምቢያ እየተካሄድ የሚገኘው ሰላማዊ ሰልፍ በኮሎምቢያ እየተካሄድ የሚገኘው ሰላማዊ ሰልፍ  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በኮሎምቢያ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በግንቦት 15/2013 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት በኮሎንቢያ እየተከሰተ በሚገኘው ቀውስ ይፈታ ዘንድ ውይይት ማድረግ እንደ ሚገባ የገለጹ ሲሆን ውይይት ወደ ሰላምና ወደ ፍትህ የሚወስድ መንገድ መሆኑን መግለጻቸው ተዘግቧል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁድ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በኮሎምቢያ እየተከሰተ በሚገኘው ቀውስ ሁኔታ ያላቸውን ሥጋት በመግለጽ ምእመናን በእዚህ ቀውስ ውስጥ ለሚገኙ እና እየተሰቃዩ ለሚገኙ ሰዎች ጸሎት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት “የተወደደው የኮሎምቢያ ህዝብ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታዎች እንዲያገኝ እፀልያለሁ፣ እንዲሁም በጥልቀት በሚደረጉ ውይይቶች አማካይነት ለተፈጠሩት በርካታ ችግሮች መፍትሄ እንዲገኝላቸው ፣ በተለይም በወረርሽኙ ሳቢያ በድህነት ለሚሰቃዩት ሰዎች እንጸልይ” ማለታቸው ተገልጿል።

ቅዱስ አባታችን አክለው እንደ ገለጹት ሕዝቡ በሰላማዊ መንገድ የመሰለፍ መብታቸው ሊጠበቅ እንደ ሚገባ የገለጹ ሲሆን “በሰብአዊ ምክንያቶች” የተነሳ ለሁሉም ጤንነት አደገኛ ከሆኑ ባህሪዎች ሕዝቡ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

23 May 2021, 12:21