ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ስለ ቡርኪናፋሶ ጽሎት አቀረቡ 'አፍሪካ ሰላም ያስፈልጋታል' አሉ! ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ስለ ቡርኪናፋሶ ጽሎት አቀረቡ 'አፍሪካ ሰላም ያስፈልጋታል' አሉ! 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ስለ ቡርኪናፋሶ ጽሎት አቀረቡ 'አፍሪካ ሰላም ያስፈልጋታል' አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቡርኪናፋሶ ውስጥ ከ 130 በላይ ሰዎች ለሞቱበት ሌላ ጥቃት የተሰማቸውን ሀዘን በግንቦት 29/2013 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ መዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ያደረጉትን አስተንትኖ ካበቁ በኋላ ባሰተላለፉት ስምንታዊ መልእክት ይገለጹ ሲሆን በተጨማሪም በቅድስት ሀገር በኢየሩሳሌም እና በማያንማር ሰላም ይሰፍን ዘንድ ለሰላም ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እሁድ ዕለት ባስተላለፉት መልእክት ባለፈው ሳምንት  አርብ እና ቅዳሜ መካከል በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር በቡርኪናፋሶ ውስጥ በምትገኝ አንድ ትንሽ ከተማ ውስጥ በተፈጸመው ጭፍጨፋ ሰለባዎች መጸለያቸውን ተናግረዋል።

በእነዚህ ተደጋጋሚ መልኩ በሚከናወኑ ጥቃቶች በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ገብተው ለሚሰቃዩት ሰዎች ሁሉና ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላው የቡርኪና ፋሶ ህዝብ ያለኝን ቅርበት ለመግለጽ እፈልጋለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው “አፍሪካ ሰላም እንጂ ሁከት አያስፈልጋትም ”ብለዋል።

ለመልአከ ሰላም ጸሎት ለተሰበሰቡ ምእመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቡርኪናፋሶ ያጋ አውራጃ ውስጥ የተቃጣውን ጥቃቶች በመልእክታቸው ያመላክቱ ሲሆን 7 ሕፃናትን ጨምሮ ቢያንስ 132 ሰዎች የተገደሉ መሆናቸውን አክለው ገልጸዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከእዚህ በታች ያለውን የማጫወቻ ቁልፍ ይጫኑ!

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በቡርኪናፋሶ ከተፈፀመው ጥቃት ውስጥ ይህ ጥቃት እጅግ የከፋ የታጣቂዎች ጥቃት መሆኑን የገለጸው መንግስት ፣ ጥቃቱን የፈፀሙትን አሸባሪዎች ብሎ በመግለፅ የ 72 ሰዓታት ብሄራዊ የሀዘን ቀን ማወጁ ተገልጿል፣  ምንም እንኳን ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን ባይኖርም ምንግሥት ጥቃት ፈጻሚዎችን አድኖ ለፍርድ እንደ ሚያቀርባቸው ገልጾ በጥቃቱ ሌሎች 40 ነዋሪዎች ቆስለዋል ተብሏል።

በኒጀር ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው በጂሃዲስቶች በተፈጠረው በሰሜናዊ ምስራቅ አከባቢ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ሌሊቱን በሙሉ የሶልሃን መንደር ከበው ጥቃቱን እንዳደረሱ ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። ቤቶችን እና የገበያ ስፍራዎችን አቃጥለዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪዎች በአከባቢው ቢኖሩም በምዕራብ አፍሪካ ሳህል አካባቢ ከአልቃኢዳ እና እስላማዊ መንግስት ለመገንባት በሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ጋር የተገናኙ ጂሃዲስቶች የሚፈጽሙትን ጥቃት አፋፍመው መቀጠላቸው የተገለጸ ሲሆን ከዓመቱ መጀመሪያ አንስቶ ጥቃቱ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ፣ በተለይም በቡርኪናፋሶ ፣ በማሊ እና በኒጀር ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ይገኛሉ። ሁከቱ በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ ከ 1.14 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን አፈናቅሏል ፤ ድሃው እና ደረቅማ የሆነችው ቡርኪናፋሶ ከጎረቤት ማሊ የመጡ ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች ትገኛለች።

በቅድስት ምድር እና በማያንማር ሰላም ይመጣ ዘንድ “የአንድ ደቂቃ የሰላም ጽሎት”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ማክሰኞ ሰኔ 01/2013 ዓ.ም በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ 8 ሰዓት ላይ ዓለም አቀፉ የካቶሊክ እንቅስቃሴ ማህበር ሁሉም ሰው የራሳቸውን ሃይማኖታዊ ባህል መሠረት ባደረገ መልኩ ለሰላም የአንድ ደቂቃ ጸሎት በማድረግ እንዲያሳልፉ የጋበዘ መሆኑን ለምእመናን ቅዱስነታቸው ተናግረዋል። በተለይም ለቅድስት ሀገር እና ለማያንማር የሰላም ጸሎት እንዲደረግ ቅዱስነታቸው አጽኖት ሰጥተው መግለጻቸው ይታወሳል።

06 June 2021, 11:24