ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዓለም የወጣቶች ቀን ላይ የሚሳተፉ ወጣቶችን የሚያስተናግዱ ቤተሰቦችን አመስግነዋል!
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በነሐሴ ወር 2023 ዓ.ም በፖርቹጋል አገር በሊዝበን ከተማ ለሚካሄደው የዓለም የወጣቶች ቀን ላይ የሚሳተፉትን በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን በቤታቸው ተቀብለው ለሚያስተናግዱ የፖርቱጋል አገር ቤተሰቦች የቪዲዮ መልእክት መላካቸው የተገለጸ ሲሆን ለጋስ እና እንግዳ ተቀባይ መሆናቸው ለሌሎችም ግንዛቤዎች ክፍት መሆናቸውን ያሳያል ብለዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባለፈው ሳምንት በሊዝበን የአለም ወጣቶች ቀን ላይ ለመሳተፍ ለሚዘጋጁ ወጣቶች ያስተላለፉትን የቪዲዮ መልእክት ተከትሎ በዝግጅቱ ወቅት በቤታቸው ስለሚቀበሏቸው የፖርቱጋል ቤተሰቦች አመስግነዋል።
በአለም ዙሪያ ከ400,000 በላይ ወጣቶች በዚህ እ.አ.አ ከነሐሴ 1-6/2023 ዓ.ም በሚካሄደው የዓለም የወጣቶች ቀን ላይ ለመሳተፍ ተመዝግበዋል።
ለአዲስ አድማስ ክፍት መሆን
ረቡዕ ጥር 17/2015 ዓ.ም በተለቀቀ የቪዲዮ መልእክት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቤታቸው አቀባበል በማድረግ ልግስና ብቻ ሳይሆን ከሁሉም በላይ ደግሞ ለሌሎች ባህሎች እና ለአዲስ አድማስ ግልጽነት ለማሳየት ዝግጁ የሆኑትን የፖርቹጋል ቤተሰቦችን አመስግነዋል።
"እነዚህ ወጣቶች በእርግጠኝነት አንዳንድ ምቾቶቻችሁን ይነሳሉ" እናም በተጨማሪ "ለቤቶቻችሁም ተጨማሪ ሥራ ይፈጥራሉ፣ ነገር ግን የሌላውን የአመለካከት ዘር ይተዋሉ፣ እናም እያንዳንዳችሁን እና እናንተ የምታስቡትን ብዙ እርግጠኛ ያልሆናችሁበትን አጋጣሚዎች 'ያዛምዳሉ' የሌሎችን ባህልን እና ወግ እንድትመለከቱ በማድረግ በሌሎች ቦታዎች ያሉትን እውነታዎች እንድታዩ ያስችላሉ። ሁሉን አቀፍ እንድትሆኑም ሊረዷችሁ ይችላሉ ማለታቸው ተገልጿል።
“ወጣቶች የውጭ አገር ሰዎች በጣም የበለጸጉ ተሞክሮዎች የተቀበሏቸው ቤተሰቦች መሆናቸውን ይናገራሉ። እና እናንተም በተለየ መንገድ፣ ከሌላ ባህል፣ ከሌላ አመለካከት ጋር ክርስቲያን መሆን እንደምትችሉ በእርግጠኝነት ሊያግዟችሁ ይችላሉ፣ ይህ ማለት እስከ አድማስ ድረስ ክፍት የሆነ “ሁለንተናዊ” ሰዎች እንድትሆኑ ያደርጋሉ ማለት ነው” ማለታቸው ተገልጿል።
ስለዚህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የፖርቱጋል ቤተሰቦች ለጋስ መስተንግዶ አመስግነዋል፣ ጥረትን ያካትታል፣ ነገር ግን “ከአነስተኛ ድንበራችን እና ከአካባቢያችን፣ ከባህላዊ ወይም ከመንፈሳዊ ድንበሮች በላይ የሆነውን የአድማስ እይታን ይተዋል” ብለዋል።
ወደ የዓለም የወጣቶች ቀን መፋጠን
እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 2023 ዓ.ም ነሐሴ ወር ላይ ለሚከበረው የዓለም የወጣቶች ቀን የተመረጠው መሪ ቃል ከሉቃስ ወንጌል የተወሰደና "ማርያም ፈጥና ሄደች" (ሉቃስ1፡39) የሚለው ነው።
ባለፈው ዓመት መጀመሪያ ላይ የዓለም ወጣቶች ቀን ፕሬስ ቢሮ ወጣቶችን ወደ ዝግጅቱ በሚያደርጉት ጉዞ እና በጉዟቸው ወቅት የሚያጅቧቸው 13 ደጋፊ ቅዱሳን ማስተዋወቁ ይታወሳል።
የመጀመሪያው የዓለም የወጣቶች ቀን የተካሄደው እ.አ.አ በ1986 በሮም ከተማ ሲሆን በኋላም በቦነስ አይረስ (እ.አ.አ 1987)፣ ሳንቲያጎ ዴ ኮምፖስቴላ (እ.አ.አ 1989)፣ በፖላንድ ቼስቶኮቫ (እ.አ.አ 1991)፣ ዴንቨር (እ.አ.አ 1993)፣ ማኒላ ፍሊፒንስ (እ.አ.አ 1995)፣ ፓሪስ (እ.አ.አ 1997)፣ ሮም (እ.ኤ.አ.) 2000) ፣ ቶሮንቶ ካናዳ (እ.አ.አ 2002) ፣ በጀርመን ኮለን ከተማ (እ.አ.አ 2005) ፣ በአውስትራሊያ ሲድኒ (እ.አ.አ 2008) ፣ በእስፔን ማድሪድ (እ.አ.አ 2011) ፣ በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኔሮ (እ.አ.አ 2013) ፣ በፖላንድ ካርኮቫ ከተማ (እ.አ.አ 2016) እና ፓናማ (እ.አ.አ 2019) በቅደም ተከተል መከናወኑ ይታወሳል።