ፈልግ

World Youth Day Lisbon 2023

ክርስቶስ ሕያው ነው! ተስፋችን እርሱ ነው! ሕልሞች እና ራዕዮች

የኢዩኤል ትንቢት ይህንን በማረ ሁኔታ ይገልጸዋል" “መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ" ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ" ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ" ጎልማሶቻችሁ ራዕይ ያያሉ” (ኢዩ 2:28 ፣ሐዋ 2:17) ወጣቶችና ሽማግሌዎች ሁለቱም በመንፈስ ቅዱስ ሆነው" ድንቅ ውህደት ይፈጥራሉ” ሽማግሌዎች ሕልምን ያልማሉ" ወጣቶች ራዕይ ያያሉ እንዴት ነው አንዱ ሌላውን የሚደግፈው?

ሽማግሌዎች የረጂም ዘመን ተሞክሯቸው ምልክት ያለበት በትውስታዎችና ምስሎች የተገነቡ ሕልሞችን ያልማሉ “ወጣቶች በእነዚያ ሕልሞች ውስጥ ሥራቸውን ቢሰድዱ" የወደፊቱን ማየት ይችላሉ፣ አድማሳቸውን የሚያሰፋ እና አዳዲስ ጎዳናን የሚያሳያቸው ራዕይ ይኖራቸዋል “ሽማግሌዎች ግን የማያልሙ ከሆነ" ወጣቶች ግልጽ የሆነ የአድማስ ዕይታ አይኖራቸውም።

ምናልባት ወላጆቻችን" አያቶቻችን ስለ እኛ ያለሙትን ሕልም እንድናስበው እንዲረዳን ብለው ያቆዩን ትውስታ ይኖር ይሆናል$ ሁላችንም" ከመወለዳችን በፊት እንኳን" ከአያቶቻችን እንደ በረከት" በፍቅርና በተሰፋ የተሞላ ሕልም" የተሻለ ሕይወት ሕልም ተቀብለናል$ አያቶቻችን እንኳን ባይሆኑ ቅድመ አያቶቻችን ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን ሲያሰላስሉ ያንን የደስታ ሕልም አልመዋል$ የዚህ ሁሉ ሕልም የመጀመሪያው የሆነው የእግዚአብሔር ሕልም" የሚቀድምና ከልጆቹ ሁሉ ሕይወት ጋር የሚሆን ነው፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፈው የዚህን በረከት ትውስታ" ለማስተላለፍ እንድንችል በሕይወት ልናቆየው የሚገባን ውድ የሆነ ውርስ ነው።

ለዚያም ነው በዕድሜ የበለጸጉ ሰዎች ረጃጂም ታሪኮቻቸውን እንዲያጫውቱን መፍቀድ; አንዳንድ ጊዜ አፈ ታሪክ ወይም ምናባዊ የሚመስሉ ቢሆንም - የሽማግሌዎች ሕልሞች ናቸው - ሆኖም ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ" ገላጭ ምልክቶች “ድብቅ መልእክቶችን ያዘሉ የበለጸጉ ተሞክሮዎች ናቸው” እነዚህ ታሪኮች ለመነገር ጊዜ ይወስዳሉ" ምንም እንኳን በማኅበራዊ ሚዲያ ከተለማመድናቸው ታሪኮች የሚረዝሙ ቢሆኑም" በውስጣቸው ለመመስጥና በትዕግሥት ለማዳመጥ ዝግጁ መሆን አለብን” ለሕይወት አስፈላጊው ጥበብ መሸሸጊያ ካደረግናቸው ከአሁኑ ጊዜ የመገናኛ ብዙኀን ምንጮች የሚልቁ መሆናቸውን መገንዘብ ይኖርብናል።

የጊዜውን ጥበብ መጋራት ከተባለው መጽሐፍ "አንዳንድ አሳቦችን በጥያቄ መልክ እገልጻለሁ” “ራሴን አብሬ ከምቆጥራቸው የዕድሜ ባለጸጎች ምን እጠይቃለሁ? እኔ “እኛን የምጠራው የትውስታ ጠባቂዎች ብዬ ነው” እኛ የወንድና የሴት አያቶች ኳየር ማቋቋም ያስፈልገናል “ እኔ አዛውንቶችን እንደ የመንፈሣዊ መጠለያ ቋሚ ኳየር" በሕይወት መስክ የሚለፋና የሚታገለውን ሠፊውን ማኅበረሰብ የሚደግፉበት" የልመና ጸሎቶችና የምሥጋና መዘሙሮች እንደ እንደሆኑ አድርጌ ነው የማያቸው” እንዲህ ሲሆን በጣም ውብ ነው" “ወጣት ወንዶችና ደናግል" አረጋውያንና ልጆች ያመስግኑት” (መዝ 148: 12-13)።

እኛ በዕድሜ የበለጸግን ሰዎች ለወጣቱ ምን ልንሰጠው እንችላለን? “የራሳቸው የሆነ የጀግንነት ምኞትና ሥጋት ያለባቸውን የዛሬዎቹን ወጣቶች " ሕይወት ያለ ፍቅር ደረቅ መሆኑን እናሳስባቸዋለን” ምን ልንነግራቸው እንችላለን? “ወደፊት የሚሆነውን በማሰብ በጭንቀት ውስጥ የሚኖሩትን" መውጣት ይቻላል ልንላቸው እንችላለን” ምን ልናስተምራቸው እንቸላለን? “አንዳንድ ጊዜ በራሳቸው ላይ ብቻ ትኩረት የሚያደርጉትን" ከመቀበል ይልቅ ይበልጥ ደስታ በመስጠት ውስጥ መኖሩን" ፍቅር በቃላት ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን በድርጊት የሚታይ መሆኑን ልናስተምራቸው እንችላለን”። 

የሚመጡ ችግሮችን አብሮ መቀበል

ለጋሥ የሆነ ፍቅር" የመጣውን የሚቀበልና ርምጃ የሚወስድ" አንዳንድ ጊዜ ስሕተት ውስጥ ሊወድቅ ይችላል” እዚህ ጋ ልክ ልጇን ከተገላገለች በኋላ አባቷን በሞት ያጣችውን የማሪያ ጋብሪኤላ ፔሪን ምስክርነት ልናገኝ እንችላለን;ብዙም ባልቆየ ግንኙነት" ነገር ግን ለእናትና አሁን ደግሞ ለአያትነት ያበቃት ሁኔታ" በሕይወቷ ላይ ተጽእኖ እንዳሳረፈ ትናገራለች “እኔ የማውቀው እግዚአብሔር ታሪክ ሠሪ መሆኑን ነው” በማስተዋሉና በምሕረቱ" ውድቀቶቻችንና ድሎቻችንን ይወስድና በምጸት የሞላባቸው ውብ ስጋጃዎች አድርጎ ይጠልፋቸዋል$ የተሠራው ስጋጃ ከጀርባው ሲመለከቱት ክሮቹ የተበጠሱበት የተቋጠሩበት ምናምን ስለሚባዘው የተዝረከረከ ይመስላል- የሕይወታችን ሁኔታዎች - ምናልባትም ጥርጣሬ ሲገባን መኖሪያችን በዚህኛው በኩል - ማለትም ድብዳብ በሚመስለው በስተጀርባው ባለው በኩል ሊሆን ይችላል “ነገር ግን ስጋጃው በፊትለፊቱ ያለው ገጽታ

አጅግ አስደናቂ ታሪክ ነው" እግዚአብሔርም የሚያየው ይህኛውን ገጽታ ነው” በዕድሜ የበለጸጉ ሰዎች ሕይወትን ጠጋ ብለው ሲመለከቱት" በደመነፍስም የሚያውቁት ከስጋጃው ጀርባ ማን እንዳለ ነው" እግዚአብሔር ከስህተቶቻችን ውስጥ ምን መልካም ነገር እንደሚያወጣ ያወቃሉ።

ወጣት" አረጋዊ" ሁላችንም አብረን ብንጓዝ" በአሁኑ ውስጥ ሥር ሰድደን እንተከላለን" ከዚህም ተነሥተን ያለፈውን እንደገና ጎብኝተን የወደፊቱን መመልከት እንችላለን$ ከታሪክ ለመማርና አንዳንድ ጊዜ የሚያስቸግሩንን ያረጁ ቁስሎች ያለፈውን እንደገና መጎብኘት “የወደፊቱን መመልከት" ሕልሞች እንዲወለዱ" ትንቢቶች እንዲነቃቁ እና ተስፋ እንዲለመልም" ጥረታችንን ማበልጸግ$ በጋራ ሆነን አንዳችን ከሌላችን እንማራለን" ልቦቻችንን እናሞቃለን" አስተሳሰቦችን በብርሃን ወንጌል እናነሣሣለን" ለእጆቻችን አዲስ ጥንካሬን ለማዋስ እንችላለን።

ሥሮች" ካለፈው ጋር የሚቸነክሩ " የአሁኑን እንዳንጋፈጥ እና አዲስ ነገር እንዳንፈጥር የሚከለክሉ መልህቆች አይደሉም$ ይልቁንም" የምናድግባቸውና አዳዲስ ተግዳሮቶችንም የምንጋፈጥባቸው የማይነቃነቁ ነጥቦች ናቸው$ “እንዲያው ቁጭ ብለን ያለፈውን መናፈቅ ምንም አይፈይድልንም; ባሕላችንን በተጨባጭ እና በፍቅር መያዝና በፍቅር መሙላት ነው “ዛሬ የኢየሱስን የምሥራች ለአዲስ ትውልድ ልናውጅ ተልከናል” ይህንን ጊዜ" ካሉት ዕድሎችና አደጋዎች ሁሉ ጋር" ካሉት ደስታዎች እና ሐዘኖች" ብልጽግናውና ጉደለቶቹ" ውድቀቶቹና ስኬቶቹ ጋር ልንወደው ይገባናል”።

 በሲኖዱ ወቅት" ከስሞዋን ደሴቶች የመጣ ወጣት ሲገልጽ" ቤተ ክርስትያን እንደ ታንኳ ነች አለ" ጎበዛዝት ሲቀዝፉ ከፊታቸው ምን እንደሚገጥማቸው እያሰቡ " አረጋውያን የከዋክብትን አቅጣጫ በማየት ወደየት አቅጣጫ መቀዘፍ እንዳለበት የሚናገሩበት ነው$ የዕድሜ ባለጸጎች" ምንም ትርጉም የለሌው ኀላፊ ግዜን የሚወክሉ ናቸው ብለው የሚያስቡ ወጣቶችን; እንዲሁም ደግሞ ወጣቶች እንዴት መሆን እንዳለባቸው የምናውቀው እኛ ነን ብለው የሚያስቡትን የዕድሜ ባለጸጎች ወደ ትክክለኛው አስተሳሰብ እንምራቸው” ይልቁንም" ሁላችንም በዚያው በአንድ ታንኳ ላይ እንሳፈር" ያለማቋረጥ እንደገና በሚያድሰው የመንፈስ ቅዱስ ጊዜ" ለተሻለ ዓለም አብረን እንሥራ።

ምንጭ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለወጣቶች እና ለተቃላልው ለእግዚአብሔር ሕዝብ ክርስቶስ ሕያው ነው፣ ተስፋችን ነው በሚል አርዕስት ከጻፉት ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ ከአንቀጽ 198-201 ላይ የተወሰደ።

 

29 December 2023, 15:03