ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ደቡባዊ ኢጣሊያ ባሪ ከተማ ከሚገኘው የኤፍ ሚዩሊ ሆስፒታል የልዑካን ቡድን ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ደቡባዊ ኢጣሊያ ባሪ ከተማ ከሚገኘው የኤፍ ሚዩሊ ሆስፒታል የልዑካን ቡድን ጋር በተገናኙበት ወቅት  (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጤና አጠባበቅ የሰውን ልጅ ማዕከል ማድረግ አለበት አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከኢጣሊያ ባሪ ከተማ ከመጡ የሆስፒታል ሰራተኞች ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፣ እና ለስደተኞች ጤና አጠባበቅ እና ለህክምና ተማሪዎች ስልጠና ለመስጠት የሚያደርጉትን ጥረት አወድሰዋል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በደቡባዊ ኢጣሊያ ባሪ ከተማ ከሚገኘው የኤፍ ሚዩሊ ሆስፒታል የልዑካን ቡድን ጋር ሰኞ ታኅሳስ 08/2016 ዓ.ም በቫቲካን ተገናኝተው ነበር።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው ውስጥ የጤና አጠባበቅ ተቋማት ሁል ጊዜ ሊገነዘቡት የሚገቡባቸውን ሁለት አስፈላጊ ገጽታዎች የሆኑትን "ሰውን ማዕከላዊ ያደረገ እና ሳይንሳዊ ምርምርን ማሳደግ" እንደ ሚገባ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

በጤና እንክብካቤ ውስጥ የሰዎች ማዕከላዊነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስለ ሰው ልጅ ማዕከላዊነት ሲናገሩ ከ 900 ዓመታት በፊት ሥራ የጀመረውን የኤፍ ሚዩሊ ሆስፒታል የምስረታ መርሆውን አስታውሰዋል ይህም - "ለታመሙ ድሆች የሚሆን ሆስፒታል" ነው የሚለው እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው አውስተዋል።

የሆስፒታሉ ሰራተኞች ለተቸገሩ ሰዎች “ተቀባይነት ያለው እና መጠጊያ የሚያገኙበት ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ” እንዲያቀርቡ መርዳት አለባቸው ብለዋል ።

ለታካሚዎች የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ብዙ ጊዜ የምትሰጡትን እንክብካቤ እና የሆስፒታሉን ህንጻ የምታደስበት መንገድ መፈለግ በየጊዜው እያደገ ያለ ተለዋዋጭ እውነታ መመከት ይቻላል” ብለዋል።  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅርቡ ለተከፈተው የስደተኞች ክሊኒክ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፣ይህም ከባሪ-ቢቶንቶ የእርዳታ ሰጪ ተቋም ከአገረ ስብከቱ ጋር በመተባበር የተደረገ መሆኑን አወድሰዋል።  

ጥሩ የምርምር እና እንክብካቤ ዑደቶችን መፍጠር

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሚዩሊ ሆስፒታል ከተለያዩ የጣሊያን ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ለሳይንሳዊ ምርምር ያደረገውን ጥረት አወድሰዋል።

ሆስፒታሉ የወደፊት ሀኪሞችን እና ነርሶችን የማሰልጠን ስራ "ምርጥ የሀገር ውስጥ ተሰጥኦዎች እንዳይሰደዱ እድል ይፈጥራል" ሲሉም "ስደት መሬታችንን የሚያደኸይ ችግር ነው" ብለዋል።

እንዲሁም “ሌሎች ከፍተኛ ባለሙያዎች ወደ ጣሊያን መጥተው እንዲሰሩ፣ በሰፊው አድማስ ላይ የበለጸገ የክህሎት ልውውጥ እንዲያደርጉ” ለማበረታታት ያደረጉትን ጥረት አወድሷል።

በማጠቃለያው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በባሪ የሚገኘው የኤፍ ሚዩሊ ሆስፒታል ሠራተኞች ለፈጠሯቸው “መልካም ዑደት” እና እርዳታቸውን ለሚሹ ብዙ ሰዎች የተሻለውን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በመፈለጋቸው አመስግነዋል።

18 December 2023, 12:48