ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ‘በደካማ እንክብካቤ የሚደረግ ጤና ለችግር ይዳርጋል’ ማለታቸው ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "ሥነ ምግባር በጤና አስተዳደር" ላይ በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ሴሚናር ላይ ከተሳታፊዎች ጋር ሐሙስ ኅዳር 20/2016 ዓ.ም ተገናኝተው ንግግር አድርገዋል።
ቅዱስነታቸው በወቅቱ በሰጡት አስተያየት በራሳቸው ጤንነት ላይ ለማሰላሰል እድሉን የተጠቀሙበት ሲሆን “እንደምታየው እኔ በሕይወት አለሁኝ ” ሲሉ ቀልድ ቢጤ የተናገሩ ሲሆን “ዶክተሩ ዱባይ እንድሄድ አልፈቀደልኝም። ምክንያቱ እዚያ በጣም ሞቃት ስለሆነ ከቀዝቃዛ አየር ወደ ሞቃት አየር ወዳለበት አገር መሄድ በዚህ ብሮንካይተስ ሁኔታ ውስጥ ምቹ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተጨማሪም ህመሙ የሳንባ ምች ስላልሆነ “በጣም አጣዳፊና ተላላፊ ብሮንካይተስ” አይደለም ያሉ ሲሆን "ከእንግዲህ ትኩሳት የለብኝም፣ ነገር ግን አንቲባዮቲክ እና እንደዚህ ያሉ መድኃኒቶችን መውሰድ አሁንም ቀጥያለሁ” ብለዋል።
ጥንካሬ እና ደካማነት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል ወደ ጤና ጉዳይ በአጠቃላይ እና ስለ እንክብካቤ አስፈላጊነት የተናገሩ ሲሆን "ጤና ጠንካራ እና ደካማ ነው" ብሏል። "'እኚህ ሰው ምን አይነት ጤና አላቸው፣ ምን ያህል ጠንካራ፣ ምን ያህል ጠንካራ ናቸው፣ ግን ደግሞ ደካማም ጭምር ናቸው። ደካማ እንክብካቤ-ጤና ወደ ደካማነት ይሸጋገራል ሲሉ ተናግረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አክለውም የመከላከያ መድሃኒት ዋጋ እንደሚመለከቱ ተናግረዋል ምክንያቱም "ክስተቶች ከመከሰታቸው በፊት ይከላከላል" ያሉ ሲሆን ለሴሚናሩ ርዕስ አድናቆታቸውን ገልፀው ሁሉም ሲታመሙ የህክምና መፍትሄ መፈለግ እና ሲታመሙ ጤናቸውን መጠበቅ አለባቸው ብለዋል።
"የህክምና እና የመድሃኒት መፍትሄዎችን መፈለግ ብቻ ሳይሆን ጤናን መንከባከብ፣ ስለ ጤና ጥሩነት ማሰብ እና ያንን ጥሩ ነገር እንዴት ማቆየት እንደሚቻል ማሰብ ይገባል፣ ማከም ብቻ ሳይሆን ማዳን ይገባል" ብለዋል።
የጳጳሱ የጤና ሁኔታ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጉንፋን ምልክቶች መካከል ያለውን የጤና ሁኔታ በትክክል ለመገምገም የሲቲ ስካን ምርመራ ካደረጉበት ቅዳሜ ጀምሮ ከሳንባ እብጠት በሽታ እያገገሙ ነው።