ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ “የእግዚአብሔር ጸጋ በመንፈሳዊ ውጊያ ድልን እንድንቀዳጅ ያግዘናል!”

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ እኩይ ምግባር እና በጎ ምግባር በሚሉ ርዕሦች ዙሪያ አዲስ በጀመሩት ሳምንታዊ የጠቅላላ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸው፥ የእግዚአብሔር ጸጋ በመንፈሳዊ ውጊያ ድል እንድንቀዳጅ እንደሚረዳን አስገንዝበዋል። ቅዱስነታቸው ረቡዕ ታኅሳስ 24/2016 ዓ. ም. በጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ውስጥ ለተገኙት ታዳሚዎች ባቀረቡት ሳምንታዊ አስተምህሮ፣ የክርስትና ሕይወት መንፈሳዊ ተጋድሎዎችን ወደ ጸጋ ጊዜያት ለመለወጥ በሚያስችሉ ዕድሎች የተሞላ መሆኑንም አስታውሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመንፈሳዊ ፍልሚያ ላይ በማተኮር ባቀረቡት ጠቅላላ አስተምህሮ፥ ስለ እኩይ ምግባር እና በጎ ምግባር በማብራራት፥ የክርስትና ሕይወታችን መቼም ቢሆን ቀጥተኛ እና ከትግል የጸዳ ሳይሆን ነገር ግን የማያቋርጥ ውጊያ ያለበት መሆኑን አስረድተዋል። ክርስቲያኖች በጥምቀት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚቀቡበት ቅብዓ ቅዱስ ሕይወት ተጋድሎ ያለበት መሆኑን ለመግለጽ መዓዛ የለውም ሲሉ ተናግረዋል።

ቅብዓ ቅዱስ አንድ ክርስቲያን ከትግል የማያመልጥ መሆኑን ወዲያው ግልጽ ያደርገዋል ሲል ተናግረው፣ ሕይወት ከፈተና እና ከመከራ በኋላ የሚገኝ በመሆኑ የእኛ ህልውና እንደ ማንኛውም ሌላ ሰው ይህን መንገድ ማለፍ መግባት አለበት ብለዋል።

የሕይወት ፈተናዎች እና ጸጋዎች

የተለያዩ ፈተናዎች በእውነት የእግዚአብሔር ጸጋ በእኛ ውስጥ እንዲሠራ ዕድል የሚሰጥ ነው ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ የመጀመሪያው አበው ቅዱስ አንጦንዮስ “ፈተናዎችን ከሌሉ ማንም ሊድን አይችልም” ማለቱንም አስታውሰዋል። ከኃጢአታቸው እራሳቸውን ነጻ ለማድረግ የሚሞክሩ ክርስቲያኖች መልካሙን ከክፉ መለየት የማይችሉ በመሆናቸው ጨለማ ውስጥ የመኖር ስጋት አለባቸው ብለዋል።

ወሰን ለሌለው የእግዚአብሔር አብ ምሕረቱ የትኛውም ኃጢአት ከባድ እንደማይሆን በልባችን እርግጠኞች ሆነን፥ ሁላችንም ለውጥ የምንፈልግ ኃጢአተኞች መሆናችንን የምንገነዘብበትን ጸጋ እግዚአብሔር እንዲሰጠን በጸሎት ልንጠይቀው ይገባል ብለዋል።

የሕይወት ፈተናዎች እና የእግዚአብሔር ምሕረት

ኢየሱስ ክርስቶስ ከኃጢአት ነፃ ቢሆንም ለጥምቀት ራሱን ያቀረበ በመሆኑ እኛም የእርሱን ምሳሌ በመከተል የእግዚአብሔርን ምሕረት ለመጠየቅ ፈጽሞ መፍራት እንደሌለብን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አሳስበዋል።

ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ በሰይጣን ወደሚፈተንበት ምድረ በዳ መሄዱን ቅዱስነታቸው አስታውሰው፥ እርሱም ቢሆን እኛ ለመጋፈጥ ዘወትር የምንዘጋጅበት ፈተና አጋጥሞታል ብለዋል። "ሕይወት በውጣውረዶች፣ በፈተናዎች፣ በመስቀለኛ መንገዶች፣ በተቃራኒ ዕይታዎች፣ በተደበቁ ማባበያዎች እና እርስ በራሱ በሚቃረኑ ድምፆች የተራች ናት” ብለዋል።

መንፈሳዊ ውጊያ እና የመንፈስ ቅዱስ ዕገዛ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ ክርስቲያኖች በየዕለቱ “ትሕትናን በሚቃረ ትዕቢት፣ ልግስናን በሚቃወም ጥላቻ፣ እውነተኛ የደስታ መንፈስን በሚቃወም ሐዘን፣ ከምሕረት ይልቅ በልብ እልከኝነት በተገመደች ቀጭን ገመድ እንዲራመዱ ጋብዘዋል።

ቅዱስነታቸው በማከልም፥ በእኩይ ምግባራት እና በበጎነት ላይ በማሰላሰል ባቀረቡት የጠቅላላ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸው፥ በእኩይ ተግባር እና በመልካም ሥነ ምግባር መካከል የሆነውን የደበዘዘ ትርጉም የለሽ ባሕላችንን ማሸነፍ እንችላለን ብለዋል። እንደዚሁም፥ በክፉ እና በጎነት ላይ የምናደርገው አስተንትኖ፥

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአስተምህሮአቸው ማጠቃለያ ላይ፥ “መንፈሳዊ ውጊያ፥ ክፉ ድርጊቶቻችንን በቅርበት እንድንመለከታቸው፣ በእግዚአብሔር ጸጋ እንድንመላለስ፣ ከመንፈስ ቅዱስ የሚፈልቅ ምንጭ ወደ ሕይወታችን እንዲፈስ እና በውስጣችን ሊያብቡ ወደሚችሉ በጎ ምግባሮች ይመራናል” በማለት አስገንዝበዋል።

 

04 January 2024, 13:12