ፈልግ

2024.01.14  Preghiera

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ወደ ኢዮቤልዩ የሚመራውን የጸሎት ዓመት አስታውቀዋል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጥር 12/2016 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ሰዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ካደርጉ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት እ.አ.አ በመጪው 2025 ዓ.ም ከሚከበረው ኢዮቤልዩ ዓመት በፊት “የጸሎት ዓመት”ን አስታውቀዋል፣ እናም ምእመናን ለክርስቲያናዊ አንድነት እና ለዓለም ሰላም እንዲጸልዩ ጋብዘዋል። ባለፈው ሳምንት በሄይቲ ታግተው የነበሩ በርካታ መነኮሳትን ጨምሮ የተወሰኑ ሰዎች እንዲፈቱ ቅዱስ አባታችን ጥሪ አቅርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ ከ2025 ኢዮቤልዩ በፊት የጸሎት አመት መርቀዋል፣ ምእመናን “ይህንን የጸጋ ክስተት በጥሩ ሁኔታ እንድንኖር እና የእግዚአብሔርን ተስፋ ኃይል እንድንለማመድ እንድንዘጋጅ ጸሎት እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ቅዱስ አባታችን በእሁድ ዕለት ባስተላለፉት መልእክት የጸሎት ዓመት “ጸሎትን በግል ሕይወት ውስጥ ማድረግ ፣ በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ፣ በዓለም ውስጥ ያለውን ጸሎት ታላቅ ዋጋ እና ፍፁም ፍላጎትን እንደገና ለማግኘት” የተሰጠ መሆኑን ገልጿል።

በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው እና የቅዱስ ወንጌልን ተልዕኮ በዓለም ዙሪያ ለማሰራጨት የሚሰራው ጳጳሳዊ ጽ/ቤት የጸሎት አመቱን ለማክበር የሚረዱ ቁሳቁሶችን በማዘጋጀት እንደሚሰራም አክለው ገልጸዋል።

ጸሎት ለክርስቲያናዊ አንድነት ለዓለም ሰላም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ክርስቲያኖች በተለይ ለክርስቲያናዊ አንድነት እንዲጸልዩ እና “በዩክሬን፣ በእስራኤል እና በፍልስጤም እና በሌሎች በርካታ የዓለም ክፍሎች ጌታ ሰላምን ያመጣ ዘንድ  እርሱን መጥራት እንዳይታክቱ” ኢኳዶርን ጨምሮ  በማለት ምዕመናን ጋብዟቸዋል።

አሁንም በሰላም እጦት የሚሰቃዩት በመካከላችን በጣም ደካሞች መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥቷል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ትንንሾቹን አስባለሁ ፣ የተጎዱትን እና የተገደሉትን ፣ ፍቅር የተነፈጉ ፣ ህልማቸውን እና የወደፊት እድላቸውን የተነፈጉትን ብዙ ልጆች አስባለሁ” ሲሉ በቁጭት ተናግረዋል።

"ሁላችንም የመጸለይ እና ለእነሱ ሰላም የመገንባ ሀላፊነታችንን እንወቅ!" ብለዋል።

በሄይቲ ውስጥ አፈናዎች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በካሪቢያን ሀገር በሄይቲ ላይ ያተኮሩ ሲሆን፥ “በሄይቲ ውስጥ ስድስት ደናግላን ሲስተሮችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች የመታገታቸውን የአፈና ዜና ሰምቻለሁ” ብለዋል።

አፈናው የተፈፀመው አርብ ዕለት በሄይቲ ዋና ከተማ ፖርት-አው ፕሪንስ ሲሆን የታጠቁ ሰዎች ሚኒባስ አስቁመው ተሳፋሪዎችን ባገቱበት ወቅት ነበር።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በእሁድ እለት በሰጡት አስተያየት በአገሪቱ ውስጥ "ማህበራዊ ስምምነት" እንዲሰፍን ሲጸልዩ ሁሉም ታጋቾች እንዲፈቱ "ከልብ" ጥሪ አቅርበዋል።  “በዚያ ውድ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ስቃይ የሚያስከትል ሁከት እንዲቆም ለሁሉም ሰው ጥሪዬን አቀርባለሁ” ብሏል።

22 January 2024, 10:56