ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ንፉግነት እንደ የልብ በሽታ እኛን የሚጎዳ ነገር ነው ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት ከቫቲካን ሆነው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደሚያደርጉ ይታወቃል። በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በጥር 15/2016 ዓ.ም ያደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም በአዲስ መልክ ክፉ እና በጎ ስነ-ምግባር በሚል ዓብይ አርዕስት ጀምረውት ከነበረው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቀጣይና “ንፉግነት” በሚል አርዕስት ባደረጉት የክፍል 5 የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ንፉግነት እንደ የልብ በሽታ ነው፤ ሐብታችን ከእኛ ጋር ወደ መቀበሪያ ሳጥናችን ውስጥ አብሮን የማይገባ ነገር ነው ማለታቸው ተገለጽ!

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በእለቱ የተነበበው የእግዚአብሔር ቃል

ነገር ግን ምግብና ልብስ ካለን፣ ያ ይበቃናል። ባለጠጋ ለመሆን የሚፈልጉ ግን ወደ ፈተናና ወደ ወጥመድ፣ እንዲሁም ሰዎችን ወደ መፍረስና ወደ ጥፋት ወደሚያዘቅጠው ወደ ብዙ ከንቱና ክፉ ምኞት ይወድቃሉ። ምክንያቱም የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነው። አንዳንዶች ባለጠጋ ለመሆን ካላቸው ጕጕት የተነሣ ከእምነት መንገድ ስተው ሄደዋል፤ ራሳቸውንም በብዙ ሥቃይ ወግተዋል (1ጢሞትዮስ 6፡8-10)።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በእለቱ ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ክፉ እና በጎ ሥነ-ምግባር በሚል አርዕስት ከእዚህ ቀደም የጀመረነውን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ዛሬም በመቀጠል ዛሬ ደግሞ ንፉግነት በሚለው አርዕስት ዙሪያ ላይ እንነጋገራለን፣ ያም ከገንዘብ ጋር በተያያዘ መልኩ የሰው ልጅ የልግስና ተግባሩን እንዳያከናውን ያደረገዋል።

ብዙ ንብረት ያላቸውን ሰዎች ብቻ የሚመለከት ኃጢአት አይደለም፣ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ በባንክ ካለን ቀሪ ገንዘብ ባሻገር የሚሄድ ክፉ የሆነ ባህሪይ ሲሆን ይህም ከኪስ ቦርሳችን ጋር የሚሄድ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ከልብ በሽታ ጋር የተቆራኘ ነገር ነው።

የበረሃ አባቶች ይህንን እኩይ ወይም ክፉ ተግባር ሲተነተኑ መነኮሳትን እንኳን በእዚህ ረገድ እንዴት ንፉግ እንዲሆኑ የሚያደርግ ጨካኝ የሆነ ክፉ ስነ-ምግባር እንደሆነ ያሳያሉ፣ ምንም እንኳን እነርሱ ብዙ የእዚህ ዓለም ነገሮችን ትተው እና ንቀው በምንኩስና የሚኖሩ ቢሆንም ንፉግነት እነርሱንም እንደምያጠቃ እናያለን። እነርሱም  ራሳቸውን ለመስጠት ፈቃደኞች እንዳይሆኑ ሊያደርጋቸው ይችላል። ከእነዚያ ነገሮች ራሳቸውን ማላቀቅ የማይችሉበት አስማተኛ የሆነ ጉዳይ ይሆንባቸዋል። አሻንጉሊታቸውን የሚጨብጡ ህፃናት ሁኔታ በሚመስል መልኩ "የእኔ ነው! የእኔ ነው!" እንዲሉ ያደርጋቸዋል። በዚህ የይገባኛል ጥያቄ ውስጥ ከእውነታው ጋር የተዛባ ግንኙነት አለ ፣ ይህም የግዴታ የገነዘብ ክምችትን እና የተለያዩ በሽታዎች ክምችቶችን ያስከትላል።

ከዚህ በሽታ ለመዳን መነኮሳቱ ከባድ ነገር ግን በጣም ውጤታማ ዘዴን አቅርበዋል - በሞት ላይ ማሰላሰል። አንድ ሰው በዚህ ዓለም ውስጥ ምንም ያህል ዕቃ ቢያከማች፣ አንድ ነገር ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ መሆን እንችላለን፡ ከእኛ ጋር ወደ ሬሳ ሳጥን ውስጥ አይገቡም፣ ምንም ነገር ከእኛ ጋር አይቀበርም። እዚህ ላይ የዚህ እኩይ ወይም ክፉ ተግባር ትርጉም የለሽነት ይገለጣል። ከቁሳቁስ ጋር የምንፈጥረው የባለቤትነት ማሰሪያ የሚታየው ብቻ ነው፣ ምክንያቱም እኛ የዓለም ጌቶች አይደለንም፤ የምንወዳት ይህች ምድር በእውነት የእኛ አይደለችም፣ እንደ እንግዶችና ተጓዦች እንቀሳቀሳለን (ዘሌ. 25፡23)።

እነዚህ ቀላል ህሳቤዎች የንፉግነትን ባህሪይ ሞኝነት እንድንገነዘብ ያስችሉናል ነገር ግን በውስጡ ያለውን ውስጣዊ ምክንያትም ጭምር የምያሳየን ነው። ይህ የሞት ፍርሃትን ለማስወገድ የሚደረግ ሙከራ ነው፡ በእጃችን በያዝናቸው ቅጽበት በእውነቱ የሚፈርሱ ወይም ጊዜያዊ የሆኑ ደህንነቶችን እንፈልጋለን። የሰነፍ ሰው ምሳሌ እናስታውስ፣ መሬቱ ብዙ ምርት የሰጠችውን ሰው ምሳሌ ማለት ነው፣ እናም ጎተራውን እንዴት እንደሚያሰፋ በማሰብ ራሱን አማከረ። ሰውዬው ሁሉንም ነገር ያሰላል፣ ለወደፊቱ የምያደርገውን ነገር ያቅዳል። እሱ ግን በህይወት ውስጥ ትክክለኛውን ተለዋዋጭ ነገር ማለትም ሞትን አላሰበም። “ሞኝ!” ይላል ቅዱስ ወንጌል። “ነፍሴንም፣ “ነፍሴ ሆይ፤ ለብዙ ዘመን የሚበቃሽ ሀብት አከማችቼልሻለሁ፤ እንግዲህ ዕረፊ፤ ብዪ፤ ጠጪ፤ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ “እግዚአብሔር ግን፣ ‘አንተ ሞኝ፤ ነፍስህን በዚህች ሌሊት ከአንተ ሊውስዱ ይፈልጓታል፤ እንግዲህ፣ ለራስህ ያከማቸኸው ለማን ይሆናል?’ አለው። “ስለዚህ ለራሱ ሀብት የሚያከማች፣ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሀብታም ያልሆነ ሰው መጨረሻው ይኸው ነው” (ሉቃስ 12፡19-21)።

በሌሎች ሁኔታዎች ይህንን አገልግሎት ለእኛ የሚሰጡን ሌቦች ናቸው። በቅዱስ በወንጌል ውስጥ እንኳን ጥሩ ቁጥር ያላቸው ገለጻዎች ስለሌቦች ይናገራሉ። እናም ምንም እንኳን ሥራቸው የሚያስነቅፍ ቢሆንም ሰላም የሚሰጥ ምክር ሊሆን ይችላል። ስለዚህም ኢየሱስ በተራራ ስብከቱ ላይ እንዲህ ሲል ሰበከ:- “ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በሚችልበት በዚህ ምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ። ነገር ግን ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በማይችልበት በዚያ በሰማይ ለራሳችሁ ሀብት አከማቹ (ማቴ 6፡19-20)። ዳግመኛም በበረሃው አባቶች ታሪክ ውስጥ መነኩሴው በእንቅልፍ ላይ እያለ በመገረም በክፍሉ ውስጥ ያስቀመጠውን ጥቂት ንብረት የሰረቀ የአንድ ሌባ ታሪክ ይናገራል። መነኩሴው ከእንቅልፉ ሲነቃ በሆነው ነገር ምንም ስይደናገጥ የሌባውን ዱካ ተከትሎ በመሄድ ሌባውን ካገኘው በኋላ የተሰረቀውን ዕቃ ከመጠየቅ ይልቅ የቀሩትን ጥቂት ነገሮች አስረክቦ እነዚህን ዕቃዎችን “ረስተሃል” ብሎ ቀሪ ነገሮችን ይሰጠዋል። እነዚህንም ውሰድ!" ብሎ ጨምሮ የሰጠዋል።

እኛ የያዝናቸው እቃዎች ጌቶች ልንሆን እንችላለን፣ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ተቃራኒው ይከሰታል፡ በመጨረሻ ይወስዳሉ። አንዳንድ ሀብታሞች አሁን ነፃ አይደሉም፣ ለማረፍ እንኳ ጊዜ አያገኙም፣ ትከሻቸውን መመልከት አለባቸው ምክንያቱም የሸቀጦች መከማቸት ደህንነታቸውን መጠበቅ አለባቸው። ሁልጊዜም ይጨነቃሉ ምክንያቱም ንበረታቸው በብዙ ላብ የተገኘ ነውና፣  ነገር ግን በአፍታ ሊጠፋ ይችላል። የራሳቸው ሀብት ኃጢአት ነው ብሎ የሚናግረውን የቅዱስ  ወንጌል ስብከትን ይረሳሉ፣ ነገር ግን በእርግጥ ተጠያቂ ናቸው። እግዚአብሔር ድሃ አይደለም፡ እርሱ የሁሉ ጌታ ነው፡ ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ “ሀብታም ሳለ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ” (2ኛ ቆሮ. 8፡9) በማለት ጽፏል።

ምስኪኑ ያልተረዳው ይህን ነው። ለብዙዎች የበረከት ምንጭ ሊሆን ይችል ነበር፣ ነገር ግን በምትኩ በጭፍን የመከራ ጎዳና ውስጥ ገብቷል።

24 January 2024, 11:07