ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ‘በጸሎት ላይ የተመሰረተ የሕብረት ክርስቲያናዊ ጉዞ’ አስፈላጊ ነው አሉ!

ከጥር 9-16/2016 ዓ. ም. ሲከበር በቆየው የክርስቲያኖች ሕብረት የጸሎት ሳምንት ትላንት መጠናቀቁ የሚታወቅ ሲሆን ለእዚህ ዓመት ለዓመታዊው የክርስቲያኖች ሕብረት የጸሎት ሳምንት መሪ ቃል እንዲሆን የተመረጠው “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኀይልህና በፍጹም ሐሳብህ ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ” (ሉቃስ 10፡27) የሚለው እንደ ነበረም ይታወሳል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ለክርስቲያኖች ሕበረት የተደረገው የአንድ ሣምንት የጸሎት ወቅት ትላንት ጥር 16/2016 ዓ.ም በተጠናቀቀበት ወቅት በሮም ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ በተካሄደው የጸሎት ሥነ-ሥረዓት ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጸሎት ዝግጅቱን በመምራት እና ሁሉም ክርስቲያኖች በጸሎት እና ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ አገልግሎት የዲያብሎስን የመለያየት ወጥመድ እንዲያስወግዱ ጋብዘዋል።

“የተለያዩ ክርስቲያኖችን የሚያቀራርበው ኢየሱስ ያስተማረው እና ያቀፈው ፍቅር ብቻ ያለምክንያት አገልግሎት የሚሰጥ ፍቅር ብቻ ነው” ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ውስጥ በተካሄደው የሐይማኖቶች ሕብረት የጸሎት ሳምንት ማብቅያ የጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ ሐሙስ አመሻሽ ላይ ያቀረቡትን ጥሪ ነበር።

ለክርስቲያን አንድነት የጸሎት ሳምንት ማጠቃለያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ቤተ ክርስቲያንን በመወከል የኢጣሊያ ሜትሮፖሊታን ፖሊካርፕን ጨምሮ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎችን እና ተወካዮችን ተቀላቅለዋል።

የክርስቲያን ሕብረት ምልክት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ እና የአንግሊካን ሕብረት መሪ ሊቀ ጳጳስ ጀስቲን ዌልቢ በሥፍረው እንደ ተገኙ እና የጸሎት ሥነ-ሥረዓቱ እንደ ታደሙ ተገልጿል። ጳጳሳቱ በሮም እና ካንተርበሪ በተካሄደው “በአንድነት ማደግ” በመባል በሚታወቀው የማኅበረ ቅዱሳን ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ሲሆን በጳጳሱ እና በሊቀ ጳጳሱ “እግዚአብሔር በየክልላቸው ላሉት ቤተክርስቲያኑ የፈቀደውን ሕብረት መመስከርን እንዲቀጥሉ” ተልእኮ ተሰጥቷቸዋል።

የባልንጀራ ፍቅር

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በስብከታቸው ወቅት መለያየት ከዲያቢሎስ እንጂ በፍጹም ከእግዚአብሔር እንደማይመጣ አስታውሰዋል።

በሉቃስ ወንጌል (10፡25-37) ላይ አንድ የህግ ምሁር ኢየሱስን የዘላለምን ሕይወት ለመውረስ ምን ማድረግ እንዳለበት በጠየቀው ክፍል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ያደረጉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሰውየው እግዚአብሔርን እና ባልንጀራን የመውደድ አስፈላጊነትን በተመለከተ ኢየሱስ ለሰጠው ማረጋገጫ ቀጣይ ጥያቄ ጠየቀ፡- “ባልንጀራዬስ ማን ነው?” ብሎ ጥያቄ ማንሳቱን የገለጹት ቅዱስነታቸው በደጉ ሳምራዊ ምሳሌ፣ ኢየሱስ የሰውየውን ከፋፋይ ጥያቄ ወደ ጎን በመተው ካህኑና ሌዋዊው ለቆሰለው ሰው እርዳታ መስጠት ባለመቻላቸው እንደ መናፍቅ ይቆጠሩ እንደነበር ጠቁመዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን በተመለከተ እንዲህ ብለዋል:- “ለመራቅ ወይም ጣት ለመቀሰር የማይፈልገው ፍቅር ብቻ ነው፣ “በአምላክ ስም ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን የራሳችንን ሃይማኖታዊ መዋቅር በብረት ለበስ መከላከል የማያውቅ ፍቅር ብቻ ነው” ብለዋል።

ኢየሱስ እውነተኛ ርስታችን ነው።

ባልንጀራችን ማን እንደሆነ ከመጠየቅ ይልቅ “እንደ ባልንጀራ ተግባሬን እወጣለሁ ወይ?” ብለን መጠየቅ አለብን ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዚህ ዓለም ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ናቸው ብለዋል።

ክርስቲያኖች የግልም ሆነ የጋራ መንፈሳዊነታቸው ከራስ ወዳድነት ወይም ከሰብዓዊ ወንድማማችነት እና ከክርስቶስ አካል ጋር ባለው አንድነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን እንዲያስቡ ጋብዟቸዋል።

የሕግ መምህሩን የመጀመሪያ ጥያቄ ወደ ሰጠው ኢየሱስ ዘወር በማለት - “የዘላለም ሕይወትን ለመውረስ ምን ማድረግ አለብኝ?” ብለን መጠየቅ ይኖርብናል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቅዱስ ጳውሎስ በተለወጠበት ጊዜ “ጌታ ሆይ ምን ላድርግ?” ብሎ በቀላሉ ጥያቄ ማንሳቱን አውስተዋል።

በዚያን ጊዜ ጳውሎስ ስለ ውርስ ጉዳይ ጥያቄውን ተወው ምክንያቱም ኢየሱስ ብቸኛው እውነተኛ ርስቱ መሆኑን ስለሚያውቅ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው “እግዚአብሔር ሀብታችን ከሆነ፣ የእኛ የቤተክርስቲያን የድርጊት እቅዳችን በእርግጥ ፈቃዱን በመፈጸም፣ ፍላጎቶቹን በመፈጸም ውስጥ መሆን አለበት” ብለዋል ጳጳሱ።

ስለ አንድነት እና ሰላም ጸሎት

ወደ ክርስቲያናዊ አንድነት ለመጓዝ የምናደርገው ጥረት የቅዱስ ጳውሎስን መንገድ በመከተል ከራሳችን ሃሳብ በመራቅ እግዚአብሔር ልባችንን እንዲመልስ ተነሳሽነቱን እንዲወስድ ቦታ መስጠት አለበት በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው “ይህ በፊታችን ያለው መንገድ ነው፡ በአንድነት መጓዝ እና በአንድነት ማገልገል፣ ለጸሎት ቦታ ቅድሚያ በመስጠት” ያሉ ሲሆን "ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን እና ባልንጀራዎቻቸውን ሲያገለግሉ እኛ ደግሞ እርስ በርስ በመረዳዳት እናድጋለን" ብለዋል።

ስለ አንድነት የሚደርገው ጸሎት “የተቀደሰ ኃላፊነት ነው፣ ምክንያቱም ከጌታ ጋር ኅብረት መፍጠር ማለት ነው፣ እሱም ስለ አንድነት ከሁሉ በላይ ወደ አብ ከጸለየው” ጋር አስተሳስረን መጸለይ ይኖርብናል ብሏል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጋራ ስንጸልይ ክርስቲያኖች በተለይም በዩክሬን እና በቅድስት ሀገር ጦርነቶች እንዲቆሙ መጸለይን ፈጽሞ መርሳት የለባቸውም ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ከደከመው ልማዳችን በክርስቶስ ስም ተነስተን እንደ አዲስ እንሥራ፣ እርሱ ‘ዓለም ያምን ዘንድ’ ይፈልጋልና” ብለዋል።

26 January 2024, 13:27